No summary available.
ጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አስመላሽ እና ልጆቹ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ዮሐንስ እሺበል - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የቀረበ የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ሲሆን፣አመልካችን የከሰሰው የሥራ ውላ ከሕግ አግባብ ውጪ አቋርጦብኛል በማለት ነው። ክሱን መሰረት በማድረግም የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈለት ጠይቆአል።
አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራበት የነበረው የህንፃ ግንባታ ተጠናቅቆአል። ይሰራ የነበረው በአናጺት ሙያ ሲሆን፣ሥራው የለም። በመሆኑም የሰራተኛ ቅነሳ ሥርአት መከተል ሳያስፈልገኝ ያለማሰጠንቀቂያ አሰናብቻዋለሁ በማለት ስለመከራከሩ ከመዝገቡ ተመልክተናል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ወገኖቹን ክርክር ከሰማ በኋላ፣የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በዚህ መሰረትም ለተጠሪ ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዱከፈለት ወስኖለታል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መስከረም 7 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 30 መሰረት የሥራ ግንኙነት በተቋረጠ ጊዜ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዳታን ያስከትላል ወይስ አያስከትልም? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም በዚህ ጭብጥ ላይ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ተጠሪ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ እንደገለጸው ተቀጥሮ ይሰራ የነበረው በአናጺነት የሥራ መደብ ላይ ነው። የአመልካች ክርክርም የተመሰረተው በዚህ ላይ ሆኖ የአናጺነት ሥራ በመጠናቀቁ የሥራ ውለ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 30 መሰረት ተቋርጦአል የሚል ምክንያት ሰጥቶአል። በፍሬ ነገር ረገድ ስለነበረው ሁኔታ አመልካች እና ተጠሪ ልዩነት የላቸውም። በመሆኑም አከራካሪው ነጥብ ውለ የተቋረጠው ሕጉ ከደነገገው ውጪ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው። ጭብጡ የሕግ በመሆኑ ሉመለስ የሚችለው ለጉዲዩ አግባብነት ካለው የአዋጁ ድንጋጌ አንፃር በማየት ነው።
አመልካች የተሰማራበት የሥራ ዘርፍ ኮንስትራክሽን ሲሆን፣ ተጠሪ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረውም አመልካች ሲያካሂደው በነበረው የህንፃ ግንባታ ነው። በህንፃው ግንባታ ሂደት የሚከናወኑ ብዙ የተለያዩ ሥራዎች (የሥራ አይነቶች) እንዲለ ይታወቃል። ተጠሪ ተመድቦበት የነበረው የሥራ አይነትም ከብዙዎች ሥራዎች አንደ በሆነው የአናጺነት ሥራ ነው። ሥራዎች ሁለ በአንድ ጊዜ የሚያልቁ እንዲልሆኑም ከሥራው ባህርይ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በዚህ መሰረትም የአናጺናነት ሥራው በመጠናቀቁ ተጠሪ ተቀንሶአል። የዚህ አይነት የሰራተኞች ቅነሳ በሚያጋጥሙበት ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆነው በአዋጁ አንቀጽ 30 የተመለከተው ድንጋጌ ነው። ድንጋጌው ልዩ ሁኔታን በማስቀመጥ አሰሪው በአዋጁ የተመለከቱትን የሰራተኞች ቅነሳ ሥነ-ሥርአት መከተል የለበትም ብልአል። ይህ ማለት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 28/2/ መሰረት ማስጠንቀቂያ እንዱሰጥ አይገደድም ማለት ነው። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን ከአንቀጽ 30 ውጪ በማየቱ አመልካች በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት ነበረበት እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በመሆኑም በዚህ ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን ውሳኔ ሰጥቶአል ለማለት ችለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 42790 ሰኔ 27 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 82438 ነሐሴ 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው ብለናል። አመልካች ማስጠንቀቂያ መስጠት አያስፈልገውም ነበር።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.