No summary available.
ታህሣሥ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወል ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገረፈጅ እሸቱ በቀለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ዓለምፀሐይ አያና - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በኦሮሚያ ክልል የጊንቢ ወረዲ ፍርድ ቤትና የምእራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ሐምል 21 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ በወረዲው ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርባ ሐምል 23 ቀን 1984 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ወደ ተላላኪነት የሥራ መደብ አሳድጏኝ ደመወዝና የማነቃቂያ አበል ከፍልኝ ከጉሉሶ ወደ ጊንቢ ሲያዛውረኝ የቤት ኪራይ አበልና የዝውውር አበል በህብረት ስምምነቱ መሰረት ሉከፍለኝ ሲገባ ያልከፈለኝ በመሆኑ ከተዛወርኩበት ጊዜ ጀምሮ እንዱከፍል ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልካች ላይ ያቀረበችው ክስ ነው አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ የተጠሪ ክስ በይርጋ ይቋረጣል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ጉዲይ ደረጃ ተጠሪ በራሷ ፍላጏትና ጥያቄ ከጉሉሶ ወደ ጊንቢ የተዛወረች በመሆኑ የቤት አበልና የዝውውር አበል የማግኘት መብት የላትም። አመልካች ለተጠሪ ከምትሰራበት ቦታ በመዛወሯ ምክንያት (disturbance allowance) ብር 300/ሦስት መቶ/ተከፍሎል። ከዚህ ውጭ ያቀረበችው ጥያቄ በሕግም ሆነ በህብረት ስምምነቱ መሰረት የቀረበ አይደለም በማለት የበኩለን ክርክርና ማስረጃ አቅርቧል። የወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ የካቲት 12 ቀን 1995 የተፃፈ ማስጠንቀቂያ የሰጣት በመሆኑ ይርጋው በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1853 መሰረት በተጠሪ ላይ አይቆጠርባትም በማለት የወሰነ ሲሆን ተጠሪ ያቀረበችውን የጥቅማ ጥቅም በተመለከተ ከየካቲት 12 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች እንዱከፈላት በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የወረዲውን ፍርድ ቤት ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች የወረዲውና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። የተጠሪ ጥያቄ ከአስራ አምስት ዓመት በኋላ የቀረበ ሆኖ አያለ ጥቄው በይርጋ አይታገድም ብለው አግባብነት የላላቸውን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር በመጥቀስ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። ከዚህ በተጨማሪ አንድ ሰራተኛ በራሱ ጠያቂነት ከአንድ ከተማ ወደ ላላ ከተማ ከተዛወረ ከእቃ ማጓጓዣያ ወጭ በስተቀር ላላ ነገር እንደማይከፈለው በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 20(16) እና(17) ተደንግጏ እያለ ለተጠሪ የዝውውር አበልና የቤት አበል እንዱከፈላት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩሎ የበታች ፍርድ ቤቶች ይርጋው የተቋረጠ መሆኑን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1852 እና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1853 ድንጋጌዎች በመጥቀስ መወሰናቸው ተገቢ ነው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት በጠበቃዋ በኩል የቃል ክርክር አቅርባለች።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የተጠሪ ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ወይስ አይሆንም? የተጠሪ ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ከሆነ እስከ መቼ ድረስ ያለው ጥያቄዋ ነው በይርጋ የሚታገደው? የሚለውና አመልካች ለተጠሪ የቤትና የዝውውር አበል የመክፈል ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም? የሚለት ጭብጦች ውሳኔ ማግኘት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
በመሰረቱ የወረዲውና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የይርጋው መቋረጥ በምክንያትነት ያቀረቡት አመልካች ተጠሪ የቤትና የዝውውር አበል የማይገባት መሆኑን በመግለጽ የካቲት 12 ቀን 1995 ዓ.ም የፃፈውን የማስጠንቀቂያ ደብዲቤ ነው። ይህ ደብዲቤ አመልካች ተጠሪ የቤትና የዝውውር አበል ያላት መሆኑን በሙለም ሆነ በከፉል በማመን የፃፈው ደብዲቤ ባለመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 164 ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት ይርጋውን ለማቋረጥ የሚችል አይደለም። የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ይርጋውን ሉያቋርጥ የሚችልና በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ አንቀጽ 164 ድንጋጌዎች የሚሸፈን ምክንያት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሣይቀርብላቸው በጥቅለ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1852 በመጥቀስ ይርጋው ተቋርጧል በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል አመልካች ለተጠሪ የፃፈውን ደብዲቤ መነሻ በማድረግ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ ያላቀረበችው አመልካችን ስለፈራችና በታዣዥነት ስሜት ነው በማለት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1853 በመጥቀስ የሰጡት ውሣኔ የህጉን ድንጋጌ አቀራረጽ ይዘት መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበ ነው። በአመልካችና በተጠሪ መካከል ላለው ግንኙነት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1853 ድንጋጌ አግባብነትና ተፈፃሚነት የላለው ድንጋጌ በመሆኑ የወረዲው ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንን ድንጋጌ አላግባብ በመጥቀስ አመልካች ከየካቲት 12 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ የቤትና የዝውውር አበል እንዱከፍል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ የጠየቁት ቀጣይነት ያለውና ተከታታይነት ባለው ጊዜ ውስጥ ሉከፈላቸው የሚገባ የቤትና የዝውውር አበል ነው። ተጠሪ ለወረዲው ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት የካቲት 6 ቀን 1999 ዓ.ም መሆኑ ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። ይህ በመሆኑ ተጠሪ ከነሐሴ 6 ቀን 1998 ዓ.ም በፉት አመልካች የቤት አበልና የዝውውር አበል እንዱከፈላት ያቀረበችው ጥያቄ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ አንቀጽ 163 ንኡስ አንቀጽ 3 በይርጋ ቀሪ የሚሆን በመሆኑ የወረዲው ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ከየካቲት 12 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 5 ቀን 1998 ዓ.ም ለተጠሪ የቤትና የዝውውር አበል እንዱከፍል የወሰኑት የይርጋ የጊዜ ገደቡ ያለፈበትን ጥያቄ አላግባብ ተቀብለው በመሆኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም ከነሐሴ 6 ቀን 1998 ዓ.ም በፉት ያለው የቤት አበልና የዝውውር አበል ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ የወረዲውና የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን የይርጋ ክርክር ውድቅ በማድረግና የሕብረት ስምምነቱ የተዛባ ትርጉም በመስጠት አመልካች ለተጠሪ ከየካቲት 6 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ የቤትና የዝውውር አበል እንዱከፍል የሰጡት ውሣኔ ከላይ የተዘረዘሩትን የሕግ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የጊንቢ ወረዲ ፍርድ ቤትና የምእራብ ወለጋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ ለሙለ ተሽሯል።
አመልካች ለተጠሪ የቤትና የዝውውር አበል የመክፈል ኃላፉነት የለበትም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.