No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 15 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996“ን” መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ ሕዲር 20 ቀን 2000 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ ላልተወሰነ ጊዜ ተቀጥረን ስንሰራ ላልች ሰራተኞች የሚያገኙትን የበረሃ አበል፣ ቦነስ፣ የሳምንት ዕረፍት ቀን ክፍያ፣ የኤላክትሪክ ፍጆታ በነፃ መጠቀም፣ የዝናብ ልብስ፣ ጥቅማ ጥቅም የማግኘት መብት እንዱከበርላቸው እና የደመወዝ እርከንና ማሻሻያ ከላልች ጋር እኩል እንዱደረግላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካችም በተከሳሽነቱ ቀርቦ የተጠሪዎች ጥያቄ በይርጋ የታገደ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የተደረገው ውል ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ በሚል የተፈረመ ሆኖ አመልካች ግዳታውን እየተወጣ የቆየ መሆኑን፣ ተጠሪዎች በሳምንት የሚሰሩት የስራ ሰዓት ብዛትም በቀን ከስምንት ሰዓት በታች የሚሰሩ መሆኑን፣ የሚያሳይ በመሆኑ የሳምንት የእረፍት ጊዜ ክፍያ ተቀባይነት እንደላለው ለቋሚ ሰራተኞች የሚከፈለ ክፍያዎችም ለተጠሪዎች ሉከፈለ እንደማይገባ ገልጾ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም በአመልካች በኩል የቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችን ውድቅ ካደረገና የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ የስራ ውለ ላልተወሰነ ጊዜ አንደተደረገ የሚቆጠር ነው በማለት አመልካች ለተጠሪዎች የሣምንት እረፍት ቀን ክፍያ፣ የበረሃ አበል ክፍያ፣ ነጻ የኤላክትሪክ፣ ቦነስ ይከፈላቸው ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይኸው ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ አፅንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ሐምል 08 ቀን 2001 ዓ.ም በአምስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሁነው እያለና ቋሚ እንሁን የሚለው ጥያቄም የክስ ምክንያት የላለው መሆኑ እየታወቀ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠሩ ይቆጠራል ተብል ለቋሚ ሰራተኞች የሚገባቸው ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች እንዱከፈላቸው መወሰኑ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን የቅጥር ውል፣ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 10(1/ሀ)“ን”፣ የድርጅቱን የህብረት ስምምነት እና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ የሰጠውን አስገዲጅ ውሳኔ ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪዎች በጡረታ የተገለለና ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ መሆኑ እየታወቀ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠሩ ይቆጠራል በማለት አመልካች ድርጅት ለተጠሪዎች ቋሚ ሰራተኞች የሚያገኛቸውን ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ይክፈላቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር መስከረም 20 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ሉመረመር ይገባል ተብል ሲታዘዝ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች ድርጅት አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው በማለት ነው።
ለዚህም መሰረት የሚያደርገው ተጠሪዎች በጡረታ የተገለለና የስራ ውለ በጊዜ ተገድቦ በግራ ቀኙ መካከል ውል የተፈፀመበትን ሰነድ ነው። ተጠሪዎች በበኩላቸው በጡረታ ተገልለው የቆዩ መሆኑን ሳይክደ በአመልካች ድርጅት ሥራ የጀመሩት የጡረታ ደብተሩን በመመለስና በማስያዝ ስለመሆኑና ይህም በስር ፍርድ ቤት በሚመለከታቸው አካላት የተረጋገጠ መሆኑን፣ እንዱሁም የስራ ውለ በየጊዜው እየታደሰ ለበርካታ አመታት በአመልካች ድርጅት ሲሰሩ መቆየታቸው የስራ ውለ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ያስቆጥራል በሚል ነው።
በመሰረቱ የቅጥር ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ለአንድ አመት እየተባለ ጊዜው ሲያልቅ እንደገና እየታደሰ እንደ አዱስ የሚታይ መሆኑ ይታመናል። በዚህም መሰረት ጊዜው ሲያልቅ ውለን ማቋረጥ የሚቻል መሆኑን ይህ ሰበር ችልት በሰ/መ/ አግባብነት ያላቸውን የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ ድንጋጌዎችን በመመርመር አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ነው። በዚህም መሰረት አንድ ሰራተኛ ከአሰሪ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቆጠረ ሉቆጠር እንደሚገባ ሕጉ ግምት እንደሚወስድ፣ በዚህ የሕግ ግምት የስራ ውለ ያልተወሰነ ጊዜ የስራ ውል ነው በማለት የሚከራከረው ሰራተኛ ተጠቃሚ በሆኑ ይህን ክርክሩን የሚደግፍለት ማስረጃ በቅድሚያ ያቀርብ ዘንድ እንደማይጠበቅበት፣ ይልቁንም በሕግ በተወሰደለት ግምት ክርክሩን ከማስረዲቱ ግዳታው ነፃ እንዱሆን እንደሚያደርገው፣ በውጤቱም በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም የስራ ውለ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሥራ የተደረጉ ውልች በአንቀፅ 10 ስር የሚሸፈኑ ናቸው ሲል በሚከራከር በአሰሪው ላይ የሚወድቅ መሆኑን በመዘርዘር ትርጉም ሰጥቶበታል።
ከእዚህ የሰበር ችልት ውሳኔ መገንዘብ የሚቻለው ሰራተኛው በየዓመቱ ውለ እየታደሰ ሲሰራ መቆየቱና የሰራተኛው የቅጥር ውል በጊዜ የተገደበ መሆኑ ብቻውን ሰራተኛን ለተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠረ ሉወሰድ የማይገባ መሆኑን ነው። ዋናው ሰራተኛው የተቀጠረበት ሥራ ቀጣይነት ያለው መሆኑ ነው። አሰሪው ይህንኑ ለማስተባበል የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 10 ስር የተመለከቱት ምክንያቶች የስራ ውለ መፈፀሙን በማስረዲት ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ለማሳያነት ያቀረበው ማስረጃ በሦስተኛ ተጠሪና በአመልካች መካከል የተደረገ የስራ ውል ሆኖ ውለ ከሀምላ 01 ቀን 1998 ዓ.ም እስከ ሀምላ 01 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ስለመሆኑ የሚያሳይ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 10 ስር በተመለከተው ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ለጥበቃ ሥራ የተቀጠሩ መሆኑን በመግለፅ የተፈፀመ ነው።
ተጠሪዎች ሁለም ለአንድ አይነት ሥራ የተቀጠሩ አለመሆናቸውንም የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ቢያሳይም የቅጥሩ ዓይነት ለተወሰነ ጊዜ መሆኑን ግን ተጠሪዎችም ያልካደት ጉዲይ ነው። በመሆኑም አመልካች የስራ ውለ ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ስለመሆኑ የማስረዲት ግዳታውን የተወጣ ሆኖ ተገኝቷል።
ከዚህም በተጨማሪ አመልካች ተጠሪዎች በጡረታ የተገለለ ሆነው በቋሚነት ሉቀጠሩ አይችለም በማለት ያቀረበው ክርክርም ተጠሪዎች በዕድሜ ጣሪያ በጡረታ የወጡ መሆኑን በዚህ ችልት በተደረገው የክርክር ሂደት አረጋግጠዋል። ተጠሪዎች የሚከራከሩት የጡረታ ደብተራቸውን በመያዝ የመብቱ ተጠቃሚ ሆነው እያለ በአመልካች ድርጅት በመስራት ላይ የሚገኙ ባለመሆኑ ቅጥሩ እንደቋሚ የሚቆጠር፤ ሕጋዊ ነው በማለት ነው። ይሁን እንጂ አንድ አሰሪ በጡረታ የተገለለን ሰራተኛ በድጋሚ ላልተወሰነ ጊዜ ቀጥሮ ያሰራል ለማለት የማይቻል መሆኑን ይህ ሰበር ችልት በመዝገብ አስገዲጅ የሆነ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ከመሆናቸውም በላይ እድሜያቸው በጡረታ ደርሶ ከስራ ከተሰናበቱ በኋላ በአመልካች ድርጅት ውስጥ የተቀጠሩ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ሆኖ አግኝተናል። እንዱህ ከሆነ ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት እንዱወሰኑላቸው ያቀረቧቸው የክፍያ ጥያቄዎች ለቋሚ ሰራተኞች የሚሰጡ መሆኑን ተጠሪዎችም በክርክራቸው ገልፀው የሚከራከሩት ነጥብ በመሆኑ ተጠሪዎች ቋሚ ሰራተኞች ካልሆኑ ክፍያዎቹ የሚገባቸው አይሆንም። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በጡረታ የተገለለና ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ መሆኑ እየታወቀ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠሩ ይቆጠራል በማለት አመልካች የተጠሪዎች ቋሚ ሰራተኞች የሚያገኛቸውን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችን ይክፈላቸው በማለት መወሰኑ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 10“ን” የአመልካች ድርጅት የሕብረት ስምምነትንና ከላይ የተጠቀሱትን የሰበር ችልት ውሳኔዎችን ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.