No summary available.
ታህሣሥ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የሆህተሰማይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት - ሻምበል አሰፊ ወልዳ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዱያቆን አያላው አዱሱ - ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የሥራ ውላ ከሕግ አግባብ ውጪ ተቋርጦብኛል በማለት ተጠሪ የመሰረተውን ክስ የሚመለከት ነው። ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው ከሥራዬ ያላአግባብ አግድኛል በማለት ሲሆን፣ ሲያገለግል የነበረውም በዱቁና እንደሆነ በክሱ ላይ ገልጾአል። አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ ከሥራው ሉሰናበት የቻለው የቤተክርስቲያንዋ ስሞነኛ ቁልፍ ያዥ ሆኖ በሰራበት እለት ከቤተመቅደስ ሙዲየ ምጽዋቶች ተሰብረው ተዘርፈዋል። ከዚህ የተነሣም ተጠሪ በወንጀል ተከሶአል። የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ክሱ ውድቅ እንዱደረግለት ጠይቆአል። ክሱ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩን ከሰማ በኋላ፣አመልካች ተጠሪን ወደ ሥራው እንዱመልስ በማለት ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም የሚል ምክንያት በመስጠት ይግባኙን ሰርዘናል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሐምል 27 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። በመቀጠልም ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
እንደምናየው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለው ግንኙነት ሃይማኖታዊ ግንኙነት ነው። አመልካች በኦርቶድክስ ተዋህድ ሃይማኖት መሰረት የተቋቋመ ሃይማኖታዊ ተቋም ሲሆን፣ተጠሪ ደግሞ በዚህ ተቋም ውስጥ የሃይማኖት አገልግልት እንዱሰጥ አባል ወይም ሰራተኛ የሆነ ነው። ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ሙዲየ ምጽዋቶች ተዘረፈ በተባለበት እለት ተጠሪ ቤተመቅደሱን መክፈቱንና በመቀጠልም ቅዲሴ እንደገባ በክርክሩ ገልጾአል። ይህ ላሆን የቻለውም በሐይማኖቱ ሥርአት መሰረት የሐይማኖቱ አገልጋይ በመሆኑ ነው።
ይህ የሰበር ችልት በተመሣሣይ ጉዲይ ክርክር ቀርቦለት በሰበር መ/ቁ. 18419 ግንቦት 4 ቀን 98 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ የሐይማኖት ወይም መንፈሳዊ አገልግልት የሚሰጥ ሰራተኛ ከተቋሙ ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ የሚሸፈን አለመሆኑን በመግለጽ የሕግ ትርጉም ሰጥቶአል። ከዚህ በኋላም በተመሣሣይ ጉዲዮች ቀርበው ቀደም ሲል በተሰጠው የሕግ ትርጉም እንደተሸፈኑ እየተገለጸ ሲወሰን ቆይቶአል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ ሥልጣን ሳይኖራቸው ክርክሩን ተቀብለው ማስተናገዲቸው አግባብ አልነበረም። የሰጡት ውሳኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቶአል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 27517 ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 04821 ሐምል 13 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ በአመልካች ላይ የመሰረተው ክስ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረት የሚታይ ባለመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ክርክሩን የሰሙት ስልጣን ሳይኖራቸው ነው ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ ብለናል፡ መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.