No summary available.
መ/ ታህሳስ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቴላኮሙኒኬሽን ኮርፕሬሽን - ደቡብ ሪጅን
ጉዲዩ አስቀድሞ በተሰጠኝ የደረጃ እድገት መሰረት ይከፈለኝ የነበረው ተጨማሪ ደመወዝ ያለአግባብ ስለተቋረጠብኝ ይኸው ሕገ ወጥ ድርጊት ተወግድ ጭማሪው ደመወዝ እንዱከፈለኝ ይደረግልኝ በማለት ተጠሪ በመሰረተው ክስ መነሻነት የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ከአመልካች የቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ጭማሪው በእድገት ሳይሆን በስህተት ተሰጥቶ የነበረ ለመሆኑ በማስረጃ ማረጋገጡን በመግለጽ የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጎአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶአል። በመቀጠልም ፍ/ቤቱ አመልካች አንዳ የሰጠውን ውሳኔ በራሱ የሚሽርበት አግባብ የለም የሚል ምክንያት በመስጠት በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮአል። የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ግንቦት 13 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ አቤቱታ ባቀረበበት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቀርቦአል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። በመቀጠልም ግራቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
የተጠሪ የክስ ምክንያት በተሰጠኝ የደረጃ እድገት መሰረት ሲከፈለኝ የነበረው የደመወዝ ጭማሪ ያለአግባብ ተቋርጦብኛል የሚል ሲሆን፣ አመልካች ደግሞ ተጠሪ ቀደም ሲል ሲሰራበት ከነበረው የሃዋሳ ከተማ አስተዲደር ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅነት ተመሣሣይ ደረጃ ወደሆነው የሪጅን ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ነው የተዛወረው። ሁለቱም ሥራዎች እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆኑ ዝውውሩ ሲደረግ የደመወዝ ለውጥ ማዘዣው በስህተት በመሰራቱ ነው ችግሩ የተፈጠረው።
የተሰራው ስህተት እንደታወቀም የእርምት እርምጃ ተወስድአል በማለት እንደተከራከረ ከመዝገቡ ለማየት ችለናል።
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው የሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልትም አመልካች ያቀረበው የፍሬ ነገር ክርክር ትክክል ሆኖ በማግኘቱ ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረው የደመወዝና የደረጃ እድገት የተነሳው (የተሰጠው) በአግባቡ ነው እሚል መደምደሚያ ደረሶአል። የክልለ ጠ/ፍ/ቤትም በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ የሻረው በፍሬ ነገር ረገድ ያረጋገጠው የተለየ ነገር አግኝቶ ሳይሆን፣ አመልካች እራሱ የሰጠውን ውሳኔ ያለምክንያት መልሶ መለወጥ የሚችልበት አግባብ የለም፣ “እንደ ፍ/ቤት እራሱ የወሰነውን ውሳኔ መከለስ /Review of judgment/ ማድረግ የማይችል ከመሆኑም በተጨማሪ ውሳኔው የሚመረመረው ለመመርመር ስልጣን ባለው በልላ አካል በjudicial review ነው።” የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት እንደሆነ ከውሳኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
እንደምንመለከተው የከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ ቀድሞ ከነበረው የተለየ ደመወዝና ጥቅም ወደሚያስገኝ ከፍያለ ደረጃ ወዲለው ቦታ አልተዛወረም እሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ክሱን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ተጠሪ ግን አንዳ የተሰጠኝ ደመወዝ ልነጠቅ አይገባም ከማለት አልፍ በእርግጥም በኋላ የተመደበበት ቦታ ከቀድሞው የተለየ እና ከፍ ያለ ደመወዝ የሚያስገኝ ስለመሆኑ አላስረዲም። ይግባኙን የሰማው ጠ/ፍ/ቤትም አመልካች ቀደም ሲል በተጻፈው ደብዲቤ መሰረት ሲከፈል የነበረውን ደመወዝ በተገቢው የእድገት አሰጣጥ መሰረት የተገኘ አይደለም በማለት የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ይችላል ወይስ አይችልም? በሚለው ነጥብ ላይ በመወሰን ውሳኔ ከመስጠት አልፍ በከፍተኛው ፍ/ቤት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር እውነት አይደለም እሚል መደምደሚያ ላይ ሉያደርስ የሚችል ማስረጃ አግኝቻለሁ አላለም።
በመሆኑም በዚህ ሰበር ችልት ሉወሰን የሚገባው ጭብጥ አመልካች የቀድሞ ውሳኔህን መለወጥ ወይም ማረም አትችልም የሚባልበት የሕግ አግባብ አለ ወይ? የሚለው ነው።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለው ግንኙነት የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ነው። አመልካች በአሰሪነቱ ተጠሪንም ሆነ ላልች ሰራተኞቹ የሚያስተዲድረው፣ የደረጃ እድገት አሰጣጥም ሆነ የደመወዝ አከፊፈል ወይም አመዲደብ የሚወሰነው ባለው አሰራር እና ድርጅታዊ መዋቅሩ መሰረት እንደሆነ ይገመታል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ በኋላ የተመደበበት የሥራ ቦታ ቀድሞ ከነበረበት የሥራ ቦታ ተመሣሣይ በመሆኑ ተጨማሪ ደመወዝ የሚያገኝበት አግባብ እንደላለ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦአል። ይህ ማለት ደግሞ ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረው ውሳኔ የፍሬ ነገር መሰረት ስለላለው ስህተት ነው ማለት ነው። ተጠሪ ተጨማሪ ደመወዝ እንዱከፈለው የሚያዘው ደብዲቤም የተጻጻፈው በተሳሳተ ውሳኔ ላይ በመመስረት በመሆኑ አመልካች ስህተቱን በማረም ተለዋጭ ውሳኔ ከመስጠት የሚያግደው የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ምክንያት የለም። አመልካች በሥራው መሪነቱ (በአሰሪነቱ) ትክክል ነው ብል በሚያምነው መሰረት የመወሰን ሥልጣን ያለው እንደመሆኑ ስህተት መስል የታየው የራሱንም ውሳኔ ማረም ያለበት እራሱ እንጂ የተሳሳተ ውሳኔ ሰጥቻለሁና አርምልኝ ብል ለላላ አካል አቤቱታ የሚያቀርብበት የህግ አግባብ የለም። አግባብ የሚሆነው በውሳኔው ተጎድቻለሁ የሚለው ወገን (ሰራተኛ) የውሳኔ ሕጋዊነት ይታይልኝ (ይመርመርልኝ) በማለት ሥልጣን ላለው አካል አቤቱታ ሲያቀርብ ነው። ተጠሪም ያደረገው ይኸው ሲሆን፣ አመልካች ውሳኔውን ያረመው በአግባቡ ሆኖ በመገኘቱ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ክሱን በሰማው ፍ/ቤት ተወስኖአል። በመሆኑም የጠ/ፍ/ቤቱ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው የJudicial Review መርህ በመጥቀስ የሰጠው ውሳኔ ትክክል ሆኖ አላገኘነውም። ውሳኔው በሕግ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በመ. የካቲት 24 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽሮአል።
የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት በመ.ቁ 5223