No summary available.
6/4/2002 ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላአመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ እላኒ እሸቱ ተጠሪ፡-
ይህ ጉዲይ ከሥራ ውል ጋር በተያያዘ የካሳ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን አንደኛ ተጠሪ በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች ባለቤቴ አቶ አሸንጋ ዩታ በተከሳሽ ድርጅት ከሰኔ 24 ቀን 1974 ዓ.ም ጀምሮ ተቀጥረው ሲሰሩ ታህሳስ 1 ቀን 2000 ዓ.ም በመ/ቤቱ የሥራ ሰዓት ለድርጅቱ ሰፕርት ክለብ ውጤት መሳካት ሲባል የስፕርት ልምምድ እንዱያደርጉ ታዘው በልምምድ የተነሳ ወድቀው እራሳቸውን የሳቱ በመሆኑ ሕይወታቸው ሉያልፍ ችሎል። የባለቤቴ ሕይወት በስፕርት ልምምድ እንዲለ በመውደቃቸው ምክንያት ሉያልፍ እንደቻለ የመ/ቤቱ ኃላፉዎች በጽሁፍና በቃል በነገሩኝ መሰረት የሕይወት ካሳ እንዱከፈለኝ የጠየቅሁ ቢሆንም ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆኑም።
ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የሕይወት ካሳ፣ የቀብር ሥነ -ሥርዓት ማስፈጸሚያ እና ከዚሁ ጋር ተያያዠነት ያላቸው ክፍያዎች እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተከሳሽ ቀርቦም በሰጠው መልስ ተከሳሽ ድርጅት በሰራተኛች ላይ ለሚደርስ ጉዲት ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት የመድን ዋስትና ሽፊን የገባ ስለሆነ መድን ሰጭው ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ይታዘዝልን በማለት አመልክቷል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅትም የአሁን አመልካች በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ተደርጎ በሰጠው መልስ የሟች ሕይወት ያለፈው በነበረባቸው አጣዲፉ የልብ ሕመም ምክንያት ስለመሆኑ በአስከሬን ምርመራ ተረጋግጧል። ይህም ሟች የሞቱት በበሽታ እንጂ በሥራ ላይ በመጣ አደጋ እንዲልሆነ የሚያሳይ ነው። የሟች ሥራም ስፕርተኛ ሳይሆን ጽዲት የነበረ ሲሆን በትርፍ ሰዓታቸው በስፕርት ሜዲ ተገኝተው ከሆነም የነበረባቸው ሕመም ለሞት አበቃቸው እንጂ በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው አላለፈም። ይህ ከሆነ ደግሞ በኃላፉነት ልንጠየቅ ስለማይገባ ክሱ ከበቂ ኪሳራ ጋር ሉሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ ከዲግማዊ ምኒሉክ ሆስፑታል የቀረበው የሟች አስከሬን ምርመራ ውጤት ሟችን ለሞት ያበቃቸው አጣዲፉ የሆነ የልብ ጡንቻ ቁስለት እንደሆነ ያሰረዲል። ከሳሽ ሟች የሞቱት በመ/ቤቱ የሥራ ሰዓት ለድርጅቱ ስፕርት ክለብ ውጤት መሳካት ሲባል የስፕርት ልምምድ እንዱያደርጉ ታዘው በልምምድ ላይ እንዲለ ወድቀው እራሳቸውን ስተው ሞተዋል ቢለም በዚህ አካኋን ሟች ስለመሞታቸው ያላሰረደ ከመሆኑም በላይ ሟች በተከሳሽ ድርጅት የፅዲት ሰራተኛ እንጂ ሰፕርተኛ አይደለም። ስለሆነም ሟች የሞቱት በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሳይሆን በተፈጥሮ ምክንያት እንደሆነ ከቀረበው የሐኪም ማስረጃ መረዲት የተቻለ ስለሆነ ከሳሽ ሟች ባለቤቴ በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው አልፎል በማለት ያቀረቡት ክስ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 97 ሥር የሚሸፈን ባለመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ተከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ የሥር ተከሳሽ አንደኛ መ/ሰጭ ለሁለተኛ መ/ሰጭ በጻፈው ደብዲቤ ሟች በሥራ ላይ ከድርጅቱ ስፕርተኞች ጋር ልምምድ ሲያደርጉ ሕይወታቸው ማለፈን ጠቅሶ በመድን ውለ መሰረት የካሳ ክፍያ እንዱፈጽምላቸው የጠየቀ ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 95/2/ መሰረት በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዲት ማለት በሥራ ላይ የሚደርሰ አደጋ ወይም በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ማለት እንደሆነ የተመለከተ ስለሆነ ሟችም ከድርጅቱ ስፕርተኞች ጋር ሥልጠና ሲወስደ ስለሞቱ ይህም በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት እንደሞቱ ስለሚያረጋግጥ የሥር ፍ/ቤት ተከሳሽ ለደረሰው አደጋ ኃላፉ አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የለውም በማለት ውሳኔውን በመሻር አንደኛ እና ሁለተኛ መ/ሰጭዎች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ ስለሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110/1/ /ሀ/ እና /ለ/ እንደዚሁም በንዐስ አንቀጽ /2/ መሰረት ካሳ ሉከፈለ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በአመልካች በኩል የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ችልቱም አቤቱታውን መርምሮ የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት የሞቱት በሥራ ላይ እንዲለ በደረሰባቸው አደጋ ምክንያት ነው ተብል ካሳ ሉከፈላቸው ይገባል በማለት የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ አግባብነቱን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ይቅረብ ብል ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥና ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኝት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥ የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት የሞቱት በሥራ ላይ በደረሰባቸው አደጋ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለው ነው።
በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 95/2/ መሰረት በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዲት ማለት በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ /occupational injury/ ወይም በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ /occupational disease/ እንደሆነ ተመልክቷል።
በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ ማለት ደግሞ በአንቀጽ 97 ላይ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን ማንኛውም ሰራተኛ ሥራውን በማከናወን ላይ ሳለ ወይም ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሱ ውጭ በሆነ ምክንያት ወይም ሥራውን ለማከናወን ባደረገው ጥረት ምክንያት በአካለ ወይም በአካለ ማንኛውም ክፍል ተፈጥሮዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት ጉዲት በሚደርስበት ጊዜ እንደሆነ ተመልክቷል።
በዚህ የአዋጁ ድንጋጌ መሰረት የካሳ ክፍያ ጥያቄ የሚያቀርበው ወገን ጉዲቱ የደረሰው በአንቀጽ 97 በተመለከተው አኳኋን በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት መሆኑንና እንደዚሁም በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ቅርብና ቀጥተኛ የሆነ የምክንያትና የውጤት ግንኙነት መኖሩን /proximate cause and effect relation ship/ ማስረዲት እንደሚጠበቅበት ይታመናል።
በልላ በኩልም የአሰሪው ኃላፉነት በጥፊት ያልተመሰረተ ጥብቅ /strict/ ስለሆነ ካሳ ጠያቂው ወገን ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ማሳየት ብቻ እንጂ ከዚህ አልፍ የጉዲት አድራሹን ወይንም የአሰሪውን የአእምሮ ሁኔታ /state of mind/ ማስረዲት እንደማይጠበቅበት ከአንቀጽ 96 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
ከላይ በተገለፀው አኳኋን አንደኛ ተጠሪም ሟች ባለቤታቸው ሕይወታቸው ያለፈው በአንቀጽ 97 በተመለከተው መሰረት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳለ ወይንም ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሳቸው ውጭ በሆነ ምክንያት በድንገት በደረሰባቸው ጉዲት ሳቢያ ሕይወታቸው ማለፈን ማስረዲት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። አንደኛ ተጠሪ ሟች ባለቤቴ ሕይወታቸው ሉያልፍ የቻለው ለድርጅቱ ስፕርት ክለብ ውጤት መሳካት የስፕርት ልምምድ እንዱያደርጉ በአሰሪው ታዘው ልምምድ ሲያደርጉ ወድቀው ሕይወታቸው ያለፈ ስለሆነ ይህም በሥራ ላይ የደረሰ አደጋ ስለሆነ ካሳ ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ሆኖም ግን ሟች የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት የተቀጠሩበት የሥራ መደብ በስፕርተኛነት ሳይሆን በፅዲት ሰራተኛነት የሥራ መደብ እንደሆነ ከመረጋገጡም በላይ አንደኛ ተጠሪ እንደሚለትም በአሰሪው በኩል ለድርጅቱ ስፕርት ክለብ ውጤት መሳካት ሲባል የስፕርት ልምምድ እንዱያደርጉ በአሰሪው ታዘው የስፕርት ልምምደን ሲያደርጉ ሕይወታቸው ስለማለፈም አላሰረደም።
ከዚህም ላላ ሟች የስፕርት ልምምድ እንዱያደርጉ በአሰሪው ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር ቢባል እንኳን በስፕርት ልምምድ ላይ እንዲለ ሕይወታቸው ማለፈ በአንቀጽ 97 ላይ እንደተመለከተው በስራ ላይ በደረሰባቸው አደጋ /accident/ ሳቢያ ሕይወታቸው እንዲለፈ የሚያረጋግጥ አይደለም። ምክንያቱም የአዋጁ አንቀጽ 95/2/ እና 97 ድንጋጌዎች በጣምራ ሲተረጎም በሥራ ላይ ጉዲት ደርሷል ለማለት በአደጋ ምክንያት በሰራተኛው አካል ላይ ጉዲት መድረሱ መረጋገጥ እንደሚገባው መገንዘብ ስለሚቻል ነው። በዚህ መልኩም በሟች ላይ በአደጋ ምክንያት ጉዲት የደረሰ ስለመሆኑ ያልተረጋገጠ ሲሆን ይልቁንም የቀረበው የሟች አስከሬን ምርመራ ውጤት ሟች ለሕልፈት የበቁት አጣዲፉ በሆነ የልብ ጡንቻ ቁስለት ምክንያት መሆኑን ስለሚያረጋግጥ ሟች በሥራ ላይ እንዲለ በደረሰባቸው አደጋ ምክንያት ለሞት እንዲልበቁና በተፈጥሮ ምክንያት /Natural cause/ እንደሞቱ የሚያሳይ ነው።
ሲጠቃለልም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 95 እና 97 በተደነገገው አግባብ አንደኛ ተጠሪ ሟች ባለቤታቸው በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት ሰለመሞታቸው በማስረዲት የካሳ ክፍያ ጥያቄውን ማቅረብ ሲጠበቅባቸው ይህንን የማስረዲት ግዳታቸውን ባልተወጡበት ሁኔታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሟች ለሞት የበቁት በሥራ ምክንያት በተፈጠረ አደጋ ነው በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር የሥር ተከሳሹ /ሁለተኛ ተጠሪ/ ለጉዲቱ ኃላፉ ነው ብል በክስ የተጠየቀውን ካሳ ተከሳሹና ጣልቃ ገቡ የአሁን አመልካች ሉከፍለ ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 75634 ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የፋዳራል መጀመሪያ ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13539 በ6/4/2001 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ አጽንተናል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
3.መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.