No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 4441ዐ ኀዲር ዐ1 ቀን 2ዐዐ2 ዳኞች፡- አቶ ሐጎስ ወልደ ወ/ት ሑሩት መለሰ አቶ ታፈሰ ይርጋ አቶ አልማው ወላ አቶ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ላይላ ረዱ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ድሬ ኢንደስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማኀበር - በላለበት የሚታይ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበራቸው የሥራ ውል ከሕግ ውጪ መቋረጡን ገልፀው የካሣ ክፍያ፣ የስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ክፍያ የዘገየበት ክፍያ፣ የታህሣሥ ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም. ደመወዝ፣ ያልተጠቀሙት የ29 ቀናት የዓመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ እንዱከፈላቸው እንዱሁም የሥራ ልምድ ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ ተጠሪም በተከሳሽነቱ ቀርቦ አመልካች በታህሣሥ ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም. ለ28 ቀናት በመደዲው ቀርተው ማስረጃ ባለማቅረባቸው ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑን፣ ወደ ሥራም በሀዘኔታ የመለሳቸው መሆኑን፣ ጥር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. አመልካች ለተጠሪ የስንብት ደብዲቤ ጽፈው ሥራቸውን በራሳቸው ፈቃድ ለቀው መሄዲቸውንና በዚህም ምክንያት ሉከፈላቸው የሚገባ ካሣ አለመኖሩን፣ የሥራ ስንብት ክፍያም አገልግልታቸው ከአምስት ዓመት በታች በመሆኑ ሉያገኙ እንደማይችለ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያም በገዛ ፈቃዲቸው ሥራውን ስለለቀቁ እንደማይገባቸው፣ የዓመት እረፍትም በወቅቱ መውሰዲቸውንና ያልወሰደት ካለም ቀርበው መተሳሰብ እንደሚችለ ክፍያው ለዘገየበት ለተባለው ሉከፈላቸው የሚገባ ክፍያ ኖሮ ያልተከፈላቸው ባለመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት እንደላለው፣ እንዱሁም የሥራ ልምድ ምስክር ወረቀት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ የአመልካች ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን የቃል እና የጽሁፍ ክርክር መርምሮ አመልካች ስራቸውን በፈቃዲቸው መልቀቃቸው ተረጋግጧል፣ የታህሣሥ ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም. ደመወዝም አመልካች ሥራውን ያልሰሩ መሆኑ ተረጋግጦ ከሥራ ላይ የቀረበትን ሕጋዊ ምክንያት ተገቢውን የሕክምና ማስረጃ በማቅረብ አላስረደም በማለት በአመልካች የተጠየቁትን ክፍያዎችን ውድቅ አድርጎ አመልካች ያልወሰደችው የዓመት ፈቃድ ከጥቅምት 1999 ዓ.ም. እስከ ጥር 29 ቀን 1999 ላለው ጊዜ ታስቦ በገንዘብ ተለውጦ ተጠሪ እንዱከፍላቸው፣ የሥራ ልምድ ምስክር ወረቀትም እንዱሰጣቸው ብቻ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት መጋቢት 14 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በፃፈት አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የሥር ፍርድ ጥር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተፃፈ የተባለውን ደብዲቤ ይዘቱም ባግባቡ ሳያገናዝብ አመልካች የሥራ ውላቸውን በገዛ ፈቃዲቸው መልቀቃቸው ተረግጧል ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው በስህተት በመሆኑ ታርሞ ሕጋዊ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ለሰበር ችልት ቀርቦ ላታይ ይገባዋል ተብል ለተጠሪ መጥሪያ ተልኮለት የቃል ክርክር ሉሰማ ቀነ ቀጠሮ በተያዘበት ዕለት መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የአመልካችን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው ጭብጦችንም አመልካች ሥራቸውን የለቀቁት በገዛ ፈቃዲቸው ነው /ባግባቡ ነው/? ወይስ አይደለም? አይደለም ከተባለስ አመልካች ሉከፈላቸው የሚገባቸው ክፍያዎች የትኞቹ ናቸው?
የሚለት ናቸው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ስራውን በገዛ ፈቃዲቸው መልቀቃቸው ተረጋጋጧል ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው የአመልካችን የምስክሮች ቃል እና በተጠሪ በኩል የቀረበውን አመልካች ጥር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ፃፈ የተባለውን ደብዲቤ በመመርኮዝ ስለመሆኑ መሆኑን ነው። አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩትም የምስክሮች ቃልም ሆነ የደብዲቤው ይዘት ሥራውን በገዛ ፈቃዲቸው የለቀቁ መሆኑን የማያሳይ ሳይሆን በተጠሪ ድርጅት የአመልካች የቅርብ ኃላፉያቸው በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው በደል እና ከሥራቸውም እንዱወጡ በቃል በታዘዙት ምክንያት ከሥራቸው የወጡ መሆኑን ገልፀው ተገቢ ክፍያ እንዱፈፀምላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን የሚያሳይ ነው በማለት ነው። ይህ ችልትም ጥር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በአመልካች ተፃፈ የተባለውን ደብዲቤ ይዘት ተመልክቶታል።
እንደተመለከተውም አመልካች በሥራቸው ቦታ ላይ በቅርብ ኃላፉያቸው የሚደርስባቸውን በደል በመዘርዘር የቅርብ ኃላፉያቸው በራሳቸው ፍላጎት ከሥራቸው ያስወጣቸው መሆኑ ግንዛቤ አግኝቶ ጥቅማ ጥቅማቸው ተጠብቆ የስራ ልምድ እንዱሰጣቸው ለተጠሪ ድርጅት ፏርሶኔል አሰተዲደር መፃፊቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታ የቀረበለት የተጠሪ ድርጅት የክፍለ ኃላፉም በሰራተኛው መተዲደሪያ ደንብ መሰረት እንዱስተናገደ በሚል ለድርጅቱ አስተዲደር አገልግልት ክፍል ደብዲቤውን መምራቱን የደብዲቤው ይዘት ያሳያል። እንግዱህ የደብዲቤው ይዘት አመልካች ስራቸውን የለቀቁት የቅርብ ኃላፉያቸው ከስራቸው ስለአስወጧቸው መሆኑን በመግልፅ ተገቢ ክፍያዎችን የጠየቁ መሆኑን ከሚያሳይ በስተቀር የስር ፍርድ ቤት በመዘገበው አይነት አለመሆኑን ይህ ችልት ከውሣኔው ግልባጭ አረጋግጧል። በጉዲዩ ላይ የቀረበውን ማስረጃ ይዘት ባግባቡ ባለመመዝገብ የሚደረሰው ድምዲሜ ደግሞ የማስረጃ ምዘና ሳይሆን በስነ-ስርዓቱ ሕጉ የተመለከተውን የዲኝነት አካሄድ የሚፃረር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት አመልካች ስራቸውን በገዛ ፈቃዲቸው መልቀቃቸው ተረጋግጧል በማለት የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ ተግኝቷል።
ስለሆነም ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ብለናል።
ቀጥለን የሕገ-ወጥ ስራ ስንብት ውጤት ከሆኑት ክፍያዎች መካከል ለአመልካች የሚገባቸው የትኞቹ እንደሆኑ ተመልክተናል።
አመልካች ከጠየቁት ክፍያ መካከል ካሣ አንደ ሲሆን አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43/4/ መሰረት ካሣ ሉከፈላቸው የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል። ላላው አመልካች ዲኝነት የጠየቁት የሥራ ስንብት ክፍያ ሲሆን ተጠሪ ይህንኑ ክፍያ አመልካች አይገባቸውም በማለት በሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክርክር የአመልካች አገልግልት ጊዜ አምስት ዓመት አልሞላቸውም የሚል ነው። ሆኖም የአምስት ዓመት አግልግልት እንደመመዘኛ የሚወስደው ሥራውን በገዛ ፈቃደ ለሚለቅ ሰራተኛ የስንብት ክፍያ ሲጠየቅ ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/ሸ/ ድንጋጌ መንፈስ ያስገነዝባል።
የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39/1/ለ/ ድንጋጌ ሲታይም የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሰራተኛ ሕግ ከደነገገው ውጪ በአሰሪው አነሳሽነት የሥራ ውለ ሲቋረጥ ሰራተኛው ከአሰሪው የስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ በግልጽ አስቀምጧል። በመሆኑም የአመልካች የሥራ ውል ከሕግ ውጪ መቋረጡ እና የሙከራ ጊዜያቸውን አመልካች የጨረሱ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የሥራ ስንብት ክፍያ የማያገኙበትን ሕጋዊ ምክንያት ስላላገኘን አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 4ዐ መሰረት ታስቦ ሉከፈላቸው ይገባል ብለናል። በአዋጁ አንቀጽ 41 መሰረትም የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ሉከፈላቸው ይገባል ብለናል። አመልካች በተገቢው ጊዜ ክፍያ ጥያቄ አቅርበው ያልተከፈላቸው በመሆኑ በተጠቃሹ አዋጅ አንቀጽ 38 መሰረት ሉከፈላቸው የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል። ሲጠቃለልም የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ በሚከተለው መልኩ ተሻሽል ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት ዐ6 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
ተጠሪ ለአመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43/4/፣ 4ዐ፣41 እና 38 መሰረት ካሣ፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና ክፍያው ለዘገየበት ክፍያ እንዱከፍል ወስነናል።
የሥር ፍርድ የታህሣሥ ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም. ደመወዝን፣ የዓመት እረፍት ክፍያንና የሥራ ልምድ ምስክር ወረቀትን በተመለከተ የሰጠው ውሣኔ ክፍል ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ አመልካች የራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.