No summary available.
መ/ ህዲር 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996“ን” መሰረት ያደረገ የደመወዝ ማስተካከያ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ናቸው። የተጠሪ ክስ ይዘት፤ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ የሚጠይቅ በሙለ ስታትስቲሺያን የሥራ መደብ ተቀጥረው በወር ብር 1971.00 (አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ብር) ደመወዝ እየተከፈላቸው በመስራት ላይ የሚገኙ መሆኑን፣ አነስተኛ የሥራ ልምድ ያላቸው እና ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ ላልች ሰራተኞች ከፍ ያለ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው ገልፀው ድርጊቱ ለአንድ ሥራ እኩል ክፍያ የሚለውን መርህ የሚጥስ በመሆኑ አመልካች የወር ደመወዙን ብር 2366.00(ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ ስድስት ብር) እንዱያደርግላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካችም በተከሳሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም የላላቸው መሆኑንና ጥያቄአቸውም በይርጋ የታገደ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት፣ በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ የደመወዝ ልዩነት የተደረገው መመሪያውን መሰረት በማድረግ ነው በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 14(1/ረ) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በዋቢነት በመጥቀስ የአመልካች አሰራር ህገ-ወጥ ነው በማለት ለተጠሪ የደመወዝ ማስተካከያ በማድረግ በፓሮል ላይ ሉተክል ይገባል ሲል ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ጥር 19 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የስር ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የአዋጅ ቁጥር 337/96 አንቀፅ 14(1/ረ) አሰሪው መመሪያውን መሰረት በማድረግ ለፈፀመው ተግባር አግባብነት የላለው በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የስር ፍርድ ቤት አመልካች መስሪያ ቤት ከዘረጋው የእድገት አሰጣጥ ሥርዓት አልፍ ለተጠሪ የወሰነው የደመወዝ መጠን መነሻን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ ጉዲዩ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ ሐምል 22 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በተመሳሳይ ደረጃ በሚገኙ ሰራተኞች መካከል የሚፈጠር የደመወዝ ልዩነት (Equal Pay Discrimination) የተከለከለ ነው የሚለውንና ኢትዮጵያ ያፀደቀችውን ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንን መሰረት ያደረገ ስለሆነ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለውም በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች ነገረ ፈጅ በበኩላቸው ነሐሴ 11 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ቀርቦ ሉመረመር ይገባዋል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካች ድርጅት በስታትስቲሽያንነት ተቀጥረው የሚሰሩ መሆኑን፣ ቅጥሩም በሙለ ስታትስቲሽያን የስራ የማዕረግ መፈፀሙን በተጠሪና በላልች ሰራተኛች መካከል የደመወዝ ልዩነት የተፈጠረው እነዚህ ሰራተኞች ምንም የስራ ልምድ በማይጠይቅ በመለስተኛ ስታትሺያን የስራ መደብ ተቀጥረው ከቆዩ በኋላ በዚህ የስራ መደብ የተቀጠሩ የዱግሪ ምሩቃን ሰራተኞች ወደሚቀጥለው የስራ መደብ የሚያድጉበትን ሁኔታ አመልካች በመመሪያ መወሰኑንና በዚህ መመሪያ መሰረትም ከተጠሪ ጋር ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ የዱግሪ ምሩቃን ከተጠሪ የተለየ ደመወዝ የሚከፈላቸው መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ሴቶች ሰራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 42(1/መ) ድንጋጌ የሚያሳይ ሲሆን ኢትዮጵያ የተቀበለችው አለም አቀፍ ኮንቬንሽንም ይህንኑ ያስገነዝባል።
የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ሲያደርግ መሰረት ያደረገው የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 14(1/ረ) ሲሆን የዚህ ድንጋጌ ይዘት ሲታይ በብሓረሰብ፣ በጾታ፣ በሐይማኖት፣ በፕለቲካ አመለካከት እና በላልችም ሁኔታ በሰራተኞች መካከል ልዩነት ማድረግ ለማንኛውም አሰሪ ሕገወጥ ድርጊት ነው የሚል ነው። የድንጋጌው እንግሉዘኛ ትርጉሙም “discriminate between workers on the basis of nationality, sex, religion, political outlook, or any other conditions shall be unlawful for an employer.” በሚል ተቀምጧል።
ከድንጋጌው ውስጥ “…በላልችም ሁኔታ…” ወይም “…. Any other conditions….” የሚለው ሐረግ ጠቅላላ ቃል መሆኑ ግልጽ ሲሆን እንዱህ በሆነ ጊዜ ቃለን ህግ አውጪው የተጠቀመው ምንን ለማመላከት ነው የሚለው ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ ሲሆን የህግ አተረጓጎም መርሆዎችን መሰረት በማድረግም ምላሹን ማግኘት ይቻላል። በዚህም መሰረት ከጠቅላላው ቃል በፉት የተዘረዘሩት የቃላት ዝርያ የሚያሳዩትን ሁኔታ በመመልከት ጠቅላላ ቃል ላልች ያልተዘረዘሩትን ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸውን ቃላት ለመጠቀም ታስቦ የተቀመጠ ነው በሚል እንደሚተረጎም ተቀባይነት ያላቸው የህግ አተረጓጎም መርሆዎች ያስገነዝባለ። በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 14(1/ረ) ድንጋጌ ስር “በላልች ሁኔታም” የሚለው ቃል ከቃለ በፉት የተቀመጡትን የልዩነት ማድረጊያ ድርጊቶችን ዓይነት የሚመለከት እንጂ አሰሪው የእድገት አሰጣጥ ሥርዓቱን በመመሪያ ዘርግቶ መስፈርቱን ለሚያሟለ ሰራተኞች መስፈርቱን ካላሟለ ሰራተኞች የተለየ ክፍያ እንዱከፈል የሚያደርግበትን አሰራር የሚመለከት አይደለም። መመሪያው በሕገ-መንግስቱ፣ በዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 14(1/ረ) ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ በተጠሪና በላልች ሰራተኞች መካከል የደመወዝ ልዩነት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም። መመሪያው መድልን ለመከላከል የማያስችል ነው ልባል የሚችልበትን ሕጋዊ ምክንያትም አላገኘንም። ሲጠቃለልም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ከላይ በተመለከቱት ህጋዊ ምክንያቶች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 28 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በተጠሪና በላልች ሰራተኞች መካከል ለተመሳሳይ ሥራ የደመወዝ ልዩነት ያደረገው በሕግ የተከለከለ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ባለመሆኑ ለተጠሪ ብር 2366.00 /ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ ስድስት ብር/ በፓሮል እንዱተክል የሚገደድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.