No summary available.
ኀዲር 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ነ/ፈጅ ተካ ገ/መድህን ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አድማስ ደምሳቸው የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ታህሣሥ 15 ቀን 2000 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ከጥር 25 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ ለአመልካች በጉዲይ አስፈፃሚነት ሲያገለግለ መቆየታቸውን ገልፀው ለስንብት የሚያበቃ ምክንያት ሳይኖር ወይም ቢኖርም እንኳ ከታወቀ ከአንድ ወር በኋላ ያሰናበታቸው በመሆኑ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ተብል ወደ ስራ እንዱመለሱ ወይም የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እና የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸው እንዱሰናበቱ በጠየቁት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም በተከሳሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ስንብቱ የተፈፀመው ተጠሪ ላላ ቦታ በመስራታቸው መሆኑንና ይህንንም እንደአወቀ የስንብቱ እርምጃ መፈፀሙን በመግለጽ ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካች ተጠሪን ባሰናበተበት ጊዜ በቂ እና ሕጋዊ ምክንያት ያልነበረው መሆኑን በመግለጽ ስንብቱ ከሕግ ውጪ ነው በሚል ምክንያት ተጠሪ የስድስት ወር ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራቸው ሉመለሱ ይገባል፣መመለስ ካልፈለጉ ተገቢ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ ይደረግ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ስንብቱ የተፈፀመው ለስንብቱ ምክንያት የሆነው ድርጊት ከተፈፀመ ሰላሳ የስራ ቀናት ከአለፈ በኋላ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/3/ በይርጋ ይታገዲል፣የአመት እረፍት የሁለት ዓመቱ ለተጠሪ ሉከፈላቸው አይገባም ሲል ምክንያቱን ለውጦ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ በማሻሻል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ኀዲር 30 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ የሰበር ማመልከቻ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም፡- ስንብቱ ጊዜውን ጠብቆ የተደረገ አይደለም ተብል ሕገ-ወጥ ነው መባለ በጉዲዩ ላይ የቀረበውን ማስረጃ ባግባቡ ባለመመልከቱና ጊዜ አቆጣጠሩም ግልጽነት በላለው ሁኔታ ተሰልቶ በመሆኑ ውሳኔው ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- አመልካች ተጠሪን በመጀመሪያ ከሥራ ያሰናበተበት ምክንያቱን ተመርኩዞ ለስንብት የሚያበቃ ምክንያት የለም ተብል እና በተጨማሪም የስንብት ምክንያቱ በይርጋ ይታገዲል ተብል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለው በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች ነገረ ፈጅ በበኩላቸው ሐምል 24 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመርነው አመልካች የተጠሪን የሥራ ውል ያቋረጠው በአዋጁ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/3/ መሰረት በሰላሳ የስራ ቀናት ውስጥ አይደለም ተብል ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የአመልካች መስሪያ ቤት ሰራተኛ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት በልላ ቦታ መስራቱ ሲታወቅ አመልካች የስራ ውለን በማቋረጥ ያሰናበታቸው መሆኑንና ተጠሪም ይህንኑ ፍሬ ነገር ሳይክደ የሚከራከሩት ስንብቱ የተፈፀመው ሰላሳ የስራ ቀናት ከአለፈ በኋላ ነው በሚል መሆኑን ነው። ተጠሪም ሆነ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች የድርጊቱን መፈፀም ያወቀበት ጊዜ በማለት የሚቀበለት ነሐሴ 16 ቀን 1999 ዓ.ም ሲሆን የስንብት ደብዲቤ ተሰጠ የሚባለው ደግሞ መስከረም 21 ቀን 2000 ዓ.ም ነው። የአመልካች ነገረ ፈጅ አጥብቀው የሚከራከሩት ይህ ጊዜ ቢያዝ እንኳ የሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ አላለፈም በማለት ነው። እኛም ይህንኑ መሰረት በማድረግ ጊዜውን ስናሰላው ከነሐሴ 16 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 06 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ አስራ አምስት፣ከመስከረም 01 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ የስንብት ደብዲቤ አስከተፃፈበት እስከ መስከረም 21 ቀን 2000 ዓ.ም ድረስ ደግሞ 13 ተከታታይ የስራ ቀናት መኖራቸውን አረጋግጠናል እነዚህ ቀናት በጠቅላላው 28 ናቸው በአዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27/3 መሰረት አንድ አሰሪ ህጉ በተፈቀደው ምክንያት መሰረት የሥራ ውለን የሚያቋርጥበት ጊዜ የስራ ውለ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱ ካወቀበት ከሰላሣ የስራ ቀናት በኋላ ከሆነ በይርጋ እንደሚታገድበት ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ ግን ከላይ እንደተመለከተው ሰላሳ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከማለፊቸው በፉት አመልካች እርምጃውን ወስዶል። በመሆኑም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ድምዲሜ ጊዜውን በተመለከተ ካላንደሩን ባግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም የአመልካች እርምጃ በሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ የሚታገድበትን ህጋዊ ምክንያት አላገኘንም። ስንብቱ መሰረት ያደረገበትን ምክንያት በቂ መሆን ያለመሆኑን ስንመለከተው ተጠሪ አመልካች የማታለል ተግባር ፈጽሟል በማለት የሚያቀረበውን ክርክር ጉዲዩን አመልካች ያውቅ ነበር ከማለት ውጪ ድርጊቱ መፈፀሙን የካደት ነጥብ አይደለም። አንድ ሰራተኛ በአሰሪው ላይ የማታለል ተግባር መፈጸሙ ከተረጋገጠ አሰሪው የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ ሕጋዊ መብት ያለው መሆኑን አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሐ/ ድንጋጌ ያስገነዝባል። አሰሪ ግልጽ የሆነ ፈቃድ እስካልሰጠ ድረስ ሰራተኛው በሁለት ቦታ በተመሳሳይ ጊዜ መስራቱ ከታወቀ አድራጏቱ በስራ ላይ የተፈፀመ የማታለል ተግባር ነው ከሚባል በስተቀር ላላ ትርጉም የሚሰጠው አይሆንም። በምርትና ምርታማነት ላይም አለታዊ ተጽእኖ የሚያስከትል በመሆኑ የስራ ውለን ለማቋረጥ ሕጋዊ እና በቂ ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 13 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጠቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ኀዲር 22 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ተጠሪን ከስራ ያሰናበትው በሕጉ አግባብ ነው ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.