No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ - ነገረ ፈጅ ወልደማርቆስ በጋሻው ተጠሪ፡- ወ/ር ሙለታ ገዲ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች ተጠሪ በልላ መስሪያ ቤት በትርፍ ሰአት ተቀጥሮ መስራቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እንደተሻሻለ እና በአመልካች የሰራተኞች መተዲደሪያ ደንብ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል በቂ ምክንያት ባለመሆኑ አመልካች ተጠሪን ከስራ ያሰናበተው አላግባብ ነው በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ሐምል 19 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቀ ነው። አመልካች ተጠሪ ያለ አሰሪው ፈቃድና እና እውቅና በልላ መስሪያ ቤት ተቀጥሮ መገኘቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ አንቀጽ 27 ንኡስ አንቀጽ 1/ሐ/ እና በሰራተኛ መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ያለ ማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚችል ምክንያት ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ጥፊቱ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል አይደለም ብለው መወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል ተጠሪ በበኩላቸው በትርፍ ሰአት ላላ ስራ ለመስራት የአሰሪው ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልግም። በአመልካች ሰራተኛ መተዲደሪያ ደንብ ውስጥ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል ጥፊት ስለመሆኑ አልተደነገገም። የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት በጽሐፍ ተከራክሯል። ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪን ከስራ ለማሰናበት የሰጠው ምክንያት በትርፍ ሰአት ላላ መስሪያ ቤት መስራቱ ሰራተኛውን ያለ ማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የሚያስችል ጥፊት ስለመሆኑ በአመልካች የሰራተኛ መተዲደሪያ ደንብ ውስጥ ያልተደነገገ መሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የሰራተኛ መተዲደሪያ ደንብ በማስቅረብ አረጋግጠዋል። አመልካች ተጠሪን ለማሰናበት የሰጠው ምክንያት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 በግልጽ የተደነገገ ምክንያት አይደለም። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅና የአመልካችን የሰራተኞች መተዲደሪያ ደንብ ሲተረጉሙ የፈጸሙት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያላገኘን በመሆኑ በፍታብሓር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 348 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት አጽንተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.