No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 05 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሪት ትዕግስት ንጉሴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ኤስ.ኦ.ኤስ.ኢንፊንት ኢትዮጵያ - ነ/ፈጅ አያንቱ ግርማ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ የአሁኗ አመልካች ተጠሪ በሕገ-ወጥ መንገድ የስራ ውለን አቋርጧል በማለት የመሰረቱት ክስ ከታየ በኋላ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ እርምጃው ሕገ-ወጥ በመሆኑ አመልካችን ወደ ስራ እንዱመልሳቸው በመ/ ከወሰነላቸው በኋላ አመልካች ወደ ስራ ቢመለሱ ከተጠሪ ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት እንደማይኖራቸው ገልፀው ለሕገ-ወጥ ስንብት የሚከፈለ ክፍያዎችንና የፔሮቪደንት ፈንድ እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት የአፈፃጸም ማመልከቻ አቅርበው ፍርድ ቤቱም የካሳ፣ ስንብትና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ የፔሮቪደንትና ክፍያ ለዘገየበት ክፍያን ግን ሳይቀበለው ቀርቷል። በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘትም አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ታህሣስ 24 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት 4(አራት) ገፅ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም የፔሮቪደንት ፈንድ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገው ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ተጠሪም በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል።
እኛም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለው አመልካች በስር ፍርድ ቤት በመሰረቱት ዋና ክስ ላይ የፔሮቪደንት ፈንድ ጥያቄ ማንሳታቸውን ተጠሪ ደግሞ በድርጅቱ ውስጥ ፔሮቪደንት ፈንድ ያለመኖሩንና ከሰራተኛው ደመወዝ ላይ ለፔሮቪደንት ፈንድ የተቆረጠ ምንም ገንዘብ ያለመኖሩን በመግለፅ መከራከሩን ነው። በዚህ በግራ ቀኙ ክርክር ማስረጃ ተመርምሮ ተገቢው ዲኝነት አልተሰጠበትም፤ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ የአሳረፈው የስራ ውል መቋረጡ ሕገ-ወጥ በመሆኑ ላይ ሲሆን፤ የሰጠውም መፍትሓም (Relief) አመልካች ወደ ስራቸው እንዱመለሱ የሚል የነበረ መሆኑንም ተረድተናል።
አመልካች በፍርድ ቤቱ ውሣኔ መሰረት ወደ ስራ መመለሱን በመተው በምትኩ የተለየዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ የአፈፃፀም ማመልከቻ አቅርበዋል።
በመሰረቱ ወደ ስራ እንዱመለስ የሚል ውሣኔ ያገኘ ሰራተኛ ከዚህ ውሣኔ በኋላም ቢሆን ወደ ስራ ለመመለስ ፍላጎት ከላለው ካሣ ተከፍልት ከስራ እንዱሰናበት በማድረግ የሥራ ክርክሩን የሚወስነው አካል ሉወሰን እንደሚችል አዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 43(3) ስር አስቀምጧል። ይህ ላሆን የሚችለውም ቀድሞ የተወሰነ ውሣኔ ከመፈጸሙ በፉት ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ወደ ስራ ሉመለሱ ይገባል ተብል የተወሰነው ውሣኔ ከመፈፀሙ በፉት በምትኩ የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍለውኝ ልሰናበት የሚል የአፈፃፀም ማመልከቻ ማቅረባቸው ግራ ቀኙን ያከራከረ ነጥብ አይደለም።
አከራካሪው ነጥብ የፔሮቪደንት ክፍያ ሲሆን የስር ፍርድ ቤቶች ጥያቄውን ያልተቀበለት ወደ ስራ የመመለስ አማራጭ ቀርቶ በአዋጁ አንቀፅ 43/3/ መሰረት በካሳ ሰራተኛው እንዱሰናበት ሲደረግ በአፈፃፀም ሉጠየቅ የሚችለው በዋናው የፍሬ ነገር ክርክር ውሳኔ ያላገኘ ክፍያ አይደለም በሚል ነው። በእርግጥ በአፈፃፀም ሉጠየቅ የሚገባው ውሳኔ ያረፈበት ጉዲይ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓቱ ከቁጥር 371 ጀምሮ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። ሆኖም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43(3) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ በግልፅ ዲኝነት ተጠይቆበት ውሳኔ ሳይሰጥ ከተጠየቁት ዲኝነቶች መካከል ወደ ስራ የመመለስ ጥያቄ ላይ ብቻ ውሳኔ ከተሰጠ እና ሰራተኛው ወደ ስራ መመለስ ሳይፈልግ ሲቀር ቀድሞ ዲኝነት በጠየቀባቸው ነገር ግን ውሳኔ ባላረፈባቸው ነጥቦች ላይ ዲኝነት ሉጠይቅ እንደሚችል ያስረዲል። ይሁን እንጂ ጥያቄው ሲቀርብ በግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የቀረበ ማስረጃ በተገቢው መንገድ ታይቶ ሉወሰን የሚገባው ነው።
የአመልካች የፔሮቪደንት ፈንድ ጥያቄ በተጠሪ በኩል ክርክር የቀረበበት ነው። ወደ ስራ እንዱመለስ ለተወሰነለት ሰራተኛ የፔሮቪደንት ፈንድ እንዱከፈል የሚወሰንበት የሕግ አግባብም የለም። እንዱሁም የፔሮቪደንት ፈንድ እንደላልች ከአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የሚመነጩ የመብት ጠያቂዎች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162 ስር በተመለከቱት የይርጋ ጊዜ ገደቦች የሚታገድ ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1845 ድንጋጌ ስር በተመለከተው የአስር ዓመት የጊዜ ገደብ የሚታገድ ስለመሆኑ ይህ ችልት በሰ/መ/ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም አመልካች የፔሮቪደንት ክፍያ ጥያቄ በአፈፃፀም መዝገብ ሳይሆን ላላ የዋና ክርክር መዝገብ ከፍተው ተገቢ ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ የሚሰጥበት ነው። በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 28 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ እና በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መስከረም 10 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.