No summary available.
ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ጊጋ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር - ሰላማዊት አስደግድግ ተጠሪዎች፡-
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የተነሳውን የስራ ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በተጀመረበት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሾች የነበሩት ተጠሪዎች ናቸው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት አመልካች በሚያካሂደው የሕንፃ (ኮንስትራክሽን) ስራ በአናፂነት፣ በብረት ስራ እና በፋራዮ ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው አመልካች ከሕግ አግባብ ውጪ የስራ ውላቸው ስላቋረጠባቸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው በመጠየቅ ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የስራ ውለ የተቋረጠው በአገሪቱ ባጋጠመው የግንባታ እቃዎች (ብረትና ሲሚንቶ) እጥረት መሆኑን በመግለጽ ተከራክሮአል። ተጠሪዎችን ሲያሰናብት የጥሬ እቃው ሲገኝ ተመልሰው እንዱሰሩ በማስታወቂያ በመግለጽ እንደሆነም በመልሱ ላይ አመልክቶአል። በልላ በኩል ደግሞ ስንብቱ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 30 መሰረት የሚደገፍ እንደሆነ ገልጾ መከራከሩን ተገንዝበናል።
ክሱን የሰማው ፍ/ቤት የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ፣የግንባታ እቃዎች እጥረት አጋጥሞአል በሚል የተደረገ ስንብት በመሆኑ እርምጃው ሕገ-ወጥ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ተጠሪዎች የጠየቁትን ክፍያ በሙለ እንዱያገኙ ወስኗል። ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ህዲር 11 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የቀረቡት አንደኛ፣ሁለተኛ፣ ሦስተኛ እና ስድስተኛ ተጠሪዎች በተገኙበት ክርክሩን ሰምተናል።
አራተኛ እና አምስተኛ ተጠሪዎች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ክርክሩ እነሱ በላለበት ተሰምቶአል።
አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ አግባብ ውጪ በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው።
በግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እንደተገለጸው አመልካች የስራ ውለን ያቋረጠው ተጠሪዎች የተቀጠሩበት ስራ ተጠናቆአል በሚል ሳይሆን፣ለህንፃው ስራ አስፈላጊ የሆኑት የግንባታ እቃዎች እጥረት አጋጥሞአል በማለት ነው።
ምክንያቱ ይህ በመሆኑም የግንባታ እቃዎቹ ተሟልተው ሲገኙ ተጠሪዎች ተመልሰው ሉሰሩ እንደሚችለ በማስታወቂያ የገለጸላቸው ስለመሆኑ ተመልክቶአል። በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የግራ ቀኝ ወገኖች ምስክሮች የተሰሙ ሲሆን፣ምስክሮቹ በሰጡት ቃልም በእርግጥ የተባለት የግንባታ እቃዎች እጥረት ስለማጋጠሙ ተረጋግጦአል። በመሆኑም እዚህ ላይ ሉነሳ የሚገባው ነጥብ ይህን መሰል ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ አሰሪ ሰራተኞችን ቢያሰናብት እርምጃው ሕገ-ወጥ ነው የሚባልበት አግባብ ምንድነው? የሚለው ነው።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው አምልካች የስንብት እርምጃ የወሰደው ከህንፃው ስራ ጠባይ በመነሳት የተወሰኑ ስራዎች ተጠናቅቀዋል በሚል አይደለም። ይህም ሆኖ ግን የህንፃውን ስራ ለማስቀጠል የማይችልበት ደረጃ ላይ ስለመገኘቱ አልተካደም (አላከራከረም)። በመሆኑም ስንብቱ በአዋጁ አንቀጽ 30 በተመለተው ድንጋጌ የሚሸፈን ነው የሚለው የአመልካቹ ክርክር መቀበል የሚቻል ባይሆንም፤ስራው በእርግጥ የለም(ቆሞአል) እየተባለ አመልካች የስንብቱን እርምጃ መውሰድ አልነበረበትም? የሚለው በስር ፍ/ቤቶች የተደረሰው ድምዲሜ ግን ላታይ የሚገባው ነው።
በአሰሪ አነሳሽነት ስለሚደረግ የስራ ውል መቋረጥ በሚመለከት በአዋጁ ከአንቀጽ 26 እስከ 30 ባለት ድንጋጌዎች በዝርዝር ተመልክቶአል። አሰሪው ማስጠንቀቂያ በመስጠት የስራ ውለን የሚያቋርጥባቸው ሁኔታዎች በአንቀጽ 28 የተቀመጡ ሲሆን፣ከእነዚህም ውስጥ ከድርጅቱ ድርጅትዊ አቋም ወይም የስራ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የተቀመጠ ንኡስ አንቀጽ /2/ ይጠቅሳል። ሰራተኞች የተሰማሩባቸውን ስራዎች በከፉልም ሆነ በሙለ በቀጥታና ለዘላቄታው የሚያስቆም የሰራተኞች ቅነሳ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት አሰሪው በማስጠንቀቂያ የስራ ውለን ማቋረጥ እንደሚችል (ሁኔታው የስራ ውለን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ተደርጏ እንደሚወሰድ) በተጠቀሰው ንኡስ አንቀጽ/2/ /ሀ/ ተደንግጓል። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው አመልካች ባጋጠመው የግንባታ እቃዎች እጥረት የተነሣ የጀመረው የህንፃ ስራ ማስቀጠል አልቻለም።
ይህ ማለት ደግሞ በአናፂነት፣በብረት እና በፋራዮ ስራ ቀጥሮ ሲያሰራቸው የነበሩትን ተጠሪዎችን ይዞ የሚጓዝበት ሁኔታ የለም ማለት ነው። ከዚህ የተነሣም ያለውን ብቸኛ አማራጭ ማለትም የስራ ውለን የማቋረጥ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል። እርምጃውን መውሰድ ያለበት ግን በሕጉ የተቀመጠውን ግልጽ ስርዓት መሰረት በማድረግ ነው። ሥርአቱ አስቀድሞ ማስጠንቀቅያ መስጠት ሲሆን፣አመልካች ግን ለተጠሪዎች ማስጠንቀቂያ አልሰጠም። ስለዚህም አመልካች የስራ ውለን ማቋረጡ ተገቢ ቢሆንም፤ማስጠንቀቂያ ባለመስጠቱ የተነሣ ሉኖርበት ከሚገባ ሐላፉነት ግን የሚድን አይደለም።
ሲጠቃለል አመልካች አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠት ከነበረበት የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ የግንባታ እቃዎች እጥረት አጋጥሞአል በሚል የተደረገ የስራ ስንብት ሕገ ወጥ ነው የሚለው የስር ፍ/ቤቶች ድምዲሜ ግን ሕጉን ያላገናዘበ በመሆኑ በዚህ ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል ለማለት ችለናል።
348/1/ መሰረት ተሻሽለዋል።
አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የነበረው የሥራ ውል ያቋረጠው በአግባቡ ነው ብለናል።
አመልካች ማስጠንቀቂያ ባለመስጠቱ እንዱከፍል የተወሰነበት ገንዘብ ይክፈል። ላልቹን ክፍያዎች ግን አይከፍልም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ ወገኖች የራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.