No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 4ዐ133 ሐምል 2 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት - አቶ ግሩም ሙላት - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- በሶማላ ብ/ክ/መንግሥት የፉልቱ ወረዲ ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ገቢዎች ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ አሉኑር አቤከር - ቀርበዋል።
ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ይህ የሰበር ክርክር ላቀርብ የቻለው አመልካች ሰኔ 2ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ አቤቱታው የሶማላ ብሓራዊ ክልልዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. 145/99 ግንቦት 26/2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ የሉበን ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. M105/02/07/99፣ ሰኔ 18/1999 ዓ.ም. የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተቀብል በማጽደቁ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለፈፀመ ፍርድ ይሻርልኝ በማለቱ ነው።
በሥር ፍ/ቤቱ በተካደው ክርክር የአሁኑ ተጠሪ ከሣሽ፣ የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ የነበሩ ሲሆን፣ ሥር ከሣሹ ያቀረበው ክስ አጭር ይዘቱ ተከሣሹ በፉደልቱ መጠጥ ውሀ ፔሮጀክት ስለሚያካሂደው ሥራ መክፈል የነበረበት ብር 183,744 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ አርባ አራት ብር/ የሥራ ግብርና ላልች ተቀናናሽ ክፍያዎች ባለ መክፈለ የልማት መስተጓጎል በማድረሱ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን እንዱከፍል ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን በማስረጃነትም ተከሣሹ ቀደም ብል የተጠቀሰው የግብር አይነት ለወረዲው እየከፈለ እንደነበር የሚያሳዩ ደረሰኞች አቅርቧል። ሥር ተከሣሹም በበኩለ በሰጠው መልስ የተጠቀሰው የግብር ዓይነት ለወረዲው /ለከሳሹ/ እየከፈለ ቢቆይም የፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ ለክልለ ባስተላለፈው ትእዛዝ መሰረት ግብሩን መክፈል ያለብኝ ለአገር ውስጥ ገቢ እንጂ ለከሣሽ እንዲልሆነ በማወቄ መከፈለን አቋርጫለሁ፤ ስለሆነም ከሣሽ ያቀረበብኝ ክስ በማይመለከተው ጉዲይ ሰለሆነ ውድቅ ይደረግልኝ ብሎል። ከመልሱ ጋር በማያያዝም ጉዲዩን በሚመለከት የተፃፈ የተለያዩ ደብዲቤዎችና የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅት መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ አቅርቧል።
የሥር ፍ/ቤቱም ከላይ በተቀመጠው መልኩ ለቀረበለት ክርክር እልባት ለመስጠት አከራካሪው የሥራ ግብር ለማን መከፈል አለበት የሚል ጭብጥ በመያዝ በሰጠው ፍርድ ምንም እንኳ ተከሣሹ የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅት እንደሆነና በአዋጅ ቁጥር 33/1985 አንቀጽ 5/2/ሐ/ መሰረትም የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅቶች አከራካሪውን ግብር ለአገር ውስጥ ገቢ መክፈል እንዲለባቸው ቢገልጽም ድንጋጌው በፋዳራል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 96/3/ም በአዋጅ ቁጥር 33/85 አንቀጽ 4 የተቀመጡትን መርሆዎች መሰረት ባደረገ ሁኔታ የተቀረፀ አይደለም፤ ማለትም ግብሩ ገቢ መሆን ያለበት የገቢው ምንጭ ለሆነው ወረዲ ስለሚገልጹ በአዋጅ ቁ. 33/85 አንቀጽ 5/2/ሐ/ የተመለከተው ተቀባይነት የለውም በማለት ተከሣሹ የተከሰሰበትን ጠቅላላ ብር 183,744 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ አርባ አራት ብር/ የሰራተኞች የሥራ ግብር እንዱሁም ብር 7ዐዐዐ /ሰባት ሺህ/ የዲኝነት ገንዘብ በአጠቃላይ ብር 19ዐ,744 /አንድ መቶ ዘጠና ሺህ ሰባት መቶ አርባ አራት ብር/ ለከሣሹ መክፈል እንዲለበት ወስኗል።
ሥር ተከሣሹም የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅት መሆኑ በመግለጽ የሰበሰበውን የሥራ ግብር በአዋጅ ቁ.
33/85 አንቀጽ 5 መሰረት ገቢ ማድረግ የሚገባው ለፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ መሆኑ በግልጽ እየታወቀና የሶማላ ክልል የገቢዎች ቢሮ በቁ. ኤክስኦ/ ኦኦጄ/3442/3ዐዐ2 በቀን ዐ9/5/99 ዓ.ም. የፃፈውን ደብዲቤ ወደ ጎን በመተው ተገቢ ያልሆነ ትርጉም በመስጠት ግብሩ ለከሳሹ እንድከፍል መወሰኑ ተገቢነት የለውም በማለት ለሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢልም ፍ/ቤቱ በፍ/ይ/መ/ቁ. 145/99፣ ግንቦት 26/2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ፍርድ ግብሩን እንዱከፍለ የተደረጉት የይግባኝ ባይ ሰራተኞች የሶማላ ክልል ተወላጆች በመሆናቸው፣ በጀቱም የክልለ በመሆኑ እና የሥራ ቦታውም በሶማላ ክልል ውስጥ በመሆኑ የሚለትን ምክንያቶች በማስቀመጥ አከራካሪው የሥራ ግብር ገቢ መሆን ያለበት ለፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ ሳይሆን ለክልለ /ለከሣሹ ወረዲ/ ነው በማለት የሥር ፍ/ቤቱን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቶታል።
ከላይ የሰፈረውን ፍርድ በመቃወምም አመልካች ሰኔ 2ዐ/2ዐዐዐ ዓ.ም. የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል፤
መሰረታዊ ይዘቱም አመልካች በፋዳራል የልማት ድርጅት ማቋቋሚያ ደንብ ቁ. 1ዐ9/96 የተቋቋመ የልማት ድርጅት መሆኑ እና የሰራተኞችን ደሞዝና ላልች ተቀናናሾች ግብር ለፋዳራል ሃገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የሚከፈለውን ክፈያ በሶማላ ክልላዊ መንግሥት ለፉደልቱ ወረዲ ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ገቢዎች ቢሮ ክፍያውን እንዱፈፀም የሥር ፍ/ቤቶቹ ውሣኔ መስጠታቸው የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 96/3/ እና አዋጅ ቁ. 33/85 አንቀጽ 5/2/ሐ/ ያሰፈሩትን መርህ በመፃረር ስለሆነና ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የሕግ ስህተቱን ይታረምልኝ የሚል ነው።
ይህ ፍ/ቤትም አከራካሪው የሰራተኞች ግብር መከፈል ያለበት ለማን መሆኑ አከራክሮ ለመወሰን ሲል ጉዩን ወደ ሰበር ችልት ያስቀረበው ሲሆን ግንቦት 13/2ዐዐ1 ዓ.ም. ግራ ቀኙ ወገኖች የቃል ክርክር አድርገዋል፣ በተጨማሪም ተጠሪው ግንቦት 14 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የተፃፈ የጽሁፍ መልስ እንዱያቀርብ ተደርጓል፤ አመልካቹ በቃል ክርክሩ ያሰፈረው ሃሣብ በሰበር አቤቱታው ከዘረዘረው የተለየ ባለመሆኑ ደግሞ መዘርዘር ሳያስፈልግ ታልፎል። ይሁን እንጂ ተጠሪው በቃልም ሆነ በጽሁፍ በሰጠው መልስ አመልካቹ የፋዳራል ተቋም ሰለመሆኑ ያስረዲበት ሁኔታ የለም፤ የሥር ፍ/ቤቶቹ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 96/3/ ይዘት አላዛቡም፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 97/1/ መሰረት ግብርና ቀረጡ የመሰብሰቡ ስልጣን የእኔ ነው፤ ሕገ-መንግሥቱም ሆነ አዋጅ ቁ. 33/1985 እንዱሁም መመሪያዎች ከወረዲው ሰራተኞች የተሰበሰበው የሥራ ግብር መከፈል ያለበት ለወረዲው እንደሆነ የሚደግፈ እንጂ የሚፃረሩ አይደለም፤ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 1ዐዐ/1/ እና አዋጅ ቁ. 33/85 እራስን በራስ ከማስተዲደር ትርጉምና ዓላማ ጋር ተያይዘው ሲታዩ የክልልች ሕልውና መሰረቱ የክልለን ገቢ መሰብሰብና ማስገባት በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶቹ የሰጡት ትርጉም ተገቢ ነው፤ የፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ለሶማላ ክልል፣ ለፉደልቱ ወረዲ ፊይናንስ ቢሮ አስተላለፈ የተባለው መመሪያ ሕገ-መንግሥታዊ ባለመሆኑ ፍ/ቤቱ ሉቀበለው አይገባም፤ ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶቹ ውሣኔ ይጽናልኝ በማለት ተከራክሯል።
እንግዱህ የግራ ቀኙ ወገኖች የክርክር አመጣጥ ከላይ ተዘርዝሮ የተቀመጠውን ሲመስል፣ ይህ ፍ/ቤትም፣
አመልካቹ የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅት ነው? ወይስ አይደለም?
አመልካቹ ከሰራተኞቹ የሰበሰበው የሥራ ግብር ገቢ መሆን ያለበት ለፋዳራል መንግሥት አገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ነው? ወይስ ለተጠሪው?
የሚለትን መሰረታዊ ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ ተጠሪው በዚህ ሰበር ችልት ባደረገው ክርክር አመልካቹ የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅት መሆኑን የሚያስረዲለት ማስረጃ አላቀረበም ብሎል። ይህ ክርክር የተነሳው አሁን እንጂ በሥር ፍ/ቤቶቹ ባካሄደት ክርክር ያልተነሣ ነው፤ ይሁን እንጂ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ደንብ ቁጥር 1ዐ9/1996 አመልካቹ የፋዳራለ መንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ እንደ ተቋቋመ በግልጽ የሚታወቅ ነው፤ ስለሆነም አመልካቹ የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅት ስለመሆኑ ማስረጃ አላቀረበም በማለት ተጠሪው በዚህ ችልት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ሁለተኛው ጭብጥ በሚመለከት ደግሞ ተጠሪው በአመልካቹ ላይ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ቀደም ብል ሲያደርገው እንደነበር አመልካቹ ከሰራተኞቹ የሚሰበስበውን የሥራ ግብር ለእኔ ገቢ ሉያደርግልኝ ይገባል ሲል አመልካቹ በሰጠው መልስ ደግሞ የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅት መሆኑን በማስመር በአዋጅ ቁጥር 33/1985 አንቀጽ 5/2/ሐ/ መሰረት የሰራተኞቹ የሥራ ግብር ገቢ የማድረግ ግዳታው ለፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ እንጂ ለተጠሪው እንዲልሆነ ተከራክሯል። ተጠሪውም አዋጅ ቁጥር 33/1985 አንቀጽ 5/2/ሐ/ ከሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 97 እና 1ዐዐ ከሰፈሩት የክልልች ሥልጣንና መርሆዎች የማይጣጣም ነው በማለት በወረዲ ውስጥ ለሚከናወን የክልል ፔሮጀት እንዱሁም የወረዲው ነዋሪ ከሆኑ የአመልካቹ ሰራተኞች የሚሰበሰብ የሥራ ግብር ገቢ ማድረጉ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱና የፋዳራል ሥርዓቱ መሰረት መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል። አዋጅ ቁጥር 33/1985 አንቀጽ 5/2/ሐ/ የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅቶች ከሰራተኞቹ የሚሰበስበው የሥራ ግብር ለፋዳራል መንግሥቱ ገቢ መሆን እንዲለበት በግልጽ አስፍሯል፤ ተጠሪው በዚህ ሰበር ችልት ያደረገው ክርክር ሲታይም የዚህ አዋጅ /አንቀጽ/ ይዘት ካለመገንዘብ የሚመነጭ አይመስልም፤ የተጠቀሰው የአዋጁ አንቀጽ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ተስማሚ አይደለም የሚል እንድምታ ያለው ክርክር እንደቀረበ ነው፤ የሥር ፍ/ቤቶቹም የተጠሪውን ክርክር እንዲለ በመውሰድ አዋጁ ተጠሪው ከመልካቹ አከራካሪውን ግብር እንዲይሰበስብ የመከልከል ብቃት የለውም በማለት ወስነዋል። ይሁን እንጂ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 97 የክልልች የታክስና ግብር ስልጣን የሚመለከት ሲሆን በዚህ አንቀጽ ከሰፈሩት የክልልች ስልጣናት ውስጥ የፋዳራል መንግሥቱ የልማት ድርጅቶች ከሰራተኞቻቸው የሚሰበስቡት የሥራ ግብር ገቢ የማድረግ መብት እንዲለባቸው አላሰፈረም፤ በአንፃሩ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 96/3/ እንደደነገገው ይህ አይነቱ ገቢ የፋዳራል መንግሥት ገቢ እንደሆነ በግልጽ ተመልክቷል። የፋዳራል መንግሥት የልማት ድርጅቶች የሥራ ቦታ አድማስም የግድ የፋዳራል መንግሥቱ ከተሞች በሆኑት በአዱስ አበባና በድሬዲዋ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን እንዲግባብነቱ የሥራ አድማሱ በክልልችም ውስጥ ሉከናወን የሚችል ነው። የሚቀጥሯቸው ሰራተኞችም የግድ በተጠቀሱት ከተሞች ብቻ የሚወሰን ሳይሆን እንደ ሁኔታው በተለያዩ ክልልች ነዋሪና ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች ሉኖሯቸው እንደሚችል ነው። በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 96/3/ እና በአዋጁ ቁጥር 33/1985 አንቀጽ 5/2/ሐ/ የተመለከተው ቁልፈ ነገር ሰራተኛው በፋዳራል የልማት ድርጅቱ ውስጥ የተቀጠረ ነው? ወይስ አይደለም? ከሚል ነጥብ አኳያ መታየት ያለበት ነው። የሰራተኛው የትውልድ ወይም የነዋሪነት ቦታ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በየትኛውም ክልል ወይም ከተማ ቢሆን ሰራተኛው የፋዳራል መንግሥቱ የልማት ተቋም በሆነ አካል ተቀጣሪ ከሆነ ከዚህ ሰራተኛ የሚሰበሰበው የሥራ ግብር በአዋጅ ቁ. 33/1985 አንቀጽ 5/2/ሐ/ መሰረት ገቢ የሚደረገው ለፋዳራል መንግሥቱ እንጂ ለክልልች አይደለም። ይህ የገቢ ክፍፍል ስርዓትም በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 97 እና 1ዐዐ ከተዘረዘሩት ስልጣናት መርሆዎች የሚጋጭ አይደለም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶቹ አመልካቹ የሚያከናውነው ፔሮጀክት በተጠሪ ውስጥ በመሆኑ እና ሰራተኞቹም የወረዲው ነዋሪዎች ናቸው በማለት በአዋጅ ቁጥር 33/1985 አንቀጽ 5/2/ሐ/ የሰፈረውን ድንጋጌ በሚመለከት የሰጡት ትርጉምና የደረሱበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፤ ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የሶማላ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. 145/99፣ ግንቦት 26/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እንዱሁም የሉበን ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. M105/02/07/99 ሰኔ 18 1999 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል፤ ይፃፍ።
አመልካቹ የፋዳራለ መንግሥት የልማት ተቋም በመሆኑ ከሰራተኞቹ የሚሰበስበውን የሥራ ግብር ገቢ የማድረግ ግዳታ ያለበት ለፋዳራለ መንግሥት እንጂ ለተጠሪው አይደለም ብለናል።
ኀዲር 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በዋለው ችልት የተላለፈው እግድ ተነስቷል፣ ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ ብለናል።
ጉዲዩ ያለቀ በመሆኑ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፤ ብለናል።
No topics extracted.