No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- እነ ወ/ሮ ኤክራም መሃመድ /2 ሰዎች/ - ጠ/አብደላ አሉ ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ ዘኪ መሐመድ - አልተጠሩም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው በአፈፃፀም ጉዲይ ሉከፈል የሚገባውን የዲኝነት ገንዘብ የሚመለከት ነው።
አመልካችና ተጠሪ በነበራቸው የውርስ ንብረት ክፍፍል ክርክር ጉዲያቸው በቤተ ዘመድ ሽምግልና ጉባኤ ከተወሰነ በኋላ አፈፃፀሙን በተመለከተ በፋ/ከፍተኛ ሸሪአ ፍ/ቤት አንስቶ እስከ ፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ደርሶ ውሣኔ አግኝቷል። ነገር ግን በፍ/ቤት በተሰጠው የአፈፃፀም ውሣኔ መሰረት ሉፈፀም ባለመቻለ ግራ ቀኙ አፈፃፀሙን በተመለከተ ስምምነት አድርገው ስምምነቱን እንዱመዘግብላቸው የፋ/ከፍተኛ ሸሪአ ፍ/ቤት ጠይቀው ፍ/ቤቱ ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ የፋ/ጠቅላይ ሸሪአ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ኋላም የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ባፀናው ውሣኔ መሰረት እንዱፈፀምና የዲኝነት ብር 23,886(ሃያ ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ስድስት) እንዱከፈል ውሣኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ አመልካቾች ለፋ/ጠቅላይ ሸሪአ ፍ/ቤት ይግባኝ ጠይቀው ፍ/ቤቱም የፋ/ከፍተኛ ሸሪአ ፍ/ቤት ዕርቁን የማይመዘግብበት ምክንያት የለም በማለት ዕርቁን እንዱመዘግብ ሲወስን የዲኝነት እንዱከፈል የተሰጠውን ውሣኔ ግን አፅንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካቾች ጥያቄም በህግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 177/1945 አንቀፅ 2/ሰ/ መሰረት ግምቱ ከብር 1ዐ,ዐዐዐ(አስር ሺህ) በላይ ለሆነ አፈፃፀም ጉዲይ ዲኝነት መከፈል ያለበት ብር 25.ዐዐ(ሃያ አምስት) ብቻ ሆኖ ሣለ 23,886(ሃያ ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ስድስት) ብር እንዱከፈል መወሰኑ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው።
ይህ ችልትም ለቀረበው የአፈፃፀም ክስ እንዱከፈል የተወሰነው ገንዘብ ህግን መሰረት ያደረገ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። የቀረበው ጥያቄም የዲኝነት ገንዘብ አከፊፈልን በሚመለከት በመሆኑ ተጠሪው በተከራካሪነት መቅረብ የሚያስፈልጋቸው ሆኖ ባለመገኘቱ መዝገቡ ባለበት ሁኔታ ተመርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት እንደተረዲነው ለሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ጉዲይ የጀመረው የውርስ ንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ የግልግል ዳኞች የሰጡት ውሣኔ እንዱፈፀም በቀረበ የአፈፃፀም ክስ ነው። ስለፍ/ቤቶች ዲኝነት ገንዘብ አከፊፈል የወጣው የህግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 177/1945 አንቀፅ 2/ሰ/ እንደሚያመለክተው ከብር 1ዐ,ዐዐዐ /አስር ሺህ/ በላይ ለሆነ የአፈፃፀም ክስ ሉከፈል የሚገባው በዲኝነት ገንዘብ ብር 25.ዐዐ /ሃያ አምስት/ ብቻ መሆኑን በግልፅ ያመለክታል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ለቀረበላቸው የአፈፃፀም ክስ የፍ/ቤት ዲኝነት ገንዘብ አከፊፈል አስመልክቶ ከወጣው ህግ ውጪ ከፍተኛ ገንዘብ እንዱከፈል የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
ው ሣ ኔ
26/2ዐዐዐ በ7/11/2ዐዐዐ ዓ.ም. የዲኝነት ገንዘብ አከፊፈልን አስመልክቶ የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የአፈፃፀም ክስ ሲቀርብ የፍርድ ባለመብቱ ተገቢውን የአፈፃፀም ዲኝነት የከፈለ በመሆኑ አመልካቾች ብር 23,886 /ሃያ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ስድስት/ በድጋሚ ሉከፍለ አይገባም ብለዋል።
አመልካቾች የከፈለት በተ.ቁ. 2 ሥር የተጠቀሰው ገንዘብ ለአመልካቾች ሉመለስላቸው ይገባል። ይፃፍ።
የሥር ፍ/ቤት መዝገብ ይመለስ።
No topics extracted.