No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሀጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ቦላ ክ/ከተማ የመሬትና ልማት አስተዲደር ነ/ፈ ደረጀ ቀረበ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር አንደኛ ተከሣሽ ተጠሪ ከሣሽ ነበሩ ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አንደኛ አመልካች በተጠሪዎች እና በስር ሁለተኛ ተከሣሽ ሥም ካርታ ሰርቷል ተጠሪዎች ካርታውን ለመውሰድ ሲፈርሙ የሥር ሁለተኛ ተከሣሽ ለመፈረም ፍቃደኛ አልሆኑም። በመሆኑም አመልካች ተሰርቶ የተቀመጠውን ካርታ ይስጠን፣ የሥር ሁለተኛ ተከሣሽ ቀርበው እንዱፈርሙ ይወሰንልን ሲለ ጠይቀዋል።
አንደኛ አመልካች በቀጠሮ ቀን መልሳቸውን ባለማያያዛቸው መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፍ የሥር ሁለተኛ ተከሣሽ መልስ ሲሰጡ (በፍሬ ጉዲዩ) በግላ የሰራሁት የቤት ቁጥር 2026ን በቤት ቁጥር 443 ጋር ካርታው ስለተሰራ ለመፈረም አልገደድም።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር አግባብ ካለው ሕግና ከቀረበለት ማስረጃ አንፃር መርምሮ ውሣኔ ሰጥቷል።
በውሣኔውም የሥር ሁለተኛ ተከሣሽ ቀርበው የመፈረም ግዳታ እንዲለባቸው ተጠሪዎች በማስረጃ አላቀረቡም ስለዚህ ጥያቄውን ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም።
አመልካች በሕግ ካርታ የመስጠት ሥልጣንና ግዳታ አለበት በዚህም የተነሣ ካርታ የሚጠይቀውን ወገን መብት አረጋግጦ ሲቀርብ አጣርቶ ካርታ የመስጠትም ሆነ የመከልከል ግዳታ የአመልካች ነው ተጠሪዎች የሟች ሚስትና ወራሽ መሆናቸውን በሟች ንብረት ላይ መብት እንዲላቸው አረጋግጠው ካርታ እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል። በመሆኑም አመልካች የተጠሪን ጥያቄ በመቀበል ተጠሪዎች መብት ያላቸው መሆኑን አጣርቶ ካርታ ሉሰጣቸው ወይም የማይፈቀድበትን ምክንያት በመግለፅ ውሣኔ ላሰጥ ይገባል ስለዚህ አመልካች የተጠሪዎችን ጥያቄ ተቀብል ክስ በቀረበበት ቤት ላይ መብት ካላቸው ካርታ እንዱሰጣቸው ሲል ወሰነ።
አመልካችም በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
337 መሰረት ሣይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ነው።
አመልካች ሐምል 18/2000 ባቀረበው አቤቱታ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ እና በፋዳራለ ከ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል ሲል ጠይቋል።
ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቷል። ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ላይ መብት ካላቸው አመልካች ካርታ ይሰጣቸው ተብል የመወሰኑ አግባብነት በመመርመር ነው።
በዚህም መሰረት ይህን ነጥብ የግራ ቀኙ ወገን ካሰሙት ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የጉዲዩን አመጣጥ ባጭሩ ስናይ ተጠሪዎች በተሰጣቸውና በሥር ሁለተኛ ተከሣሽ ስም በአመልካች ካርታ ተሰርቶላቸው እያለ ተጠሪዎች ካርታውን ፈርመው ለመውሰድ ፍቃደኛ ሲሆኑ የሥር ሁለተኛ ተከሣሽ ካርታው የእኔ የግላ የሆነውን ቤት አካቶ የተሰራ ስለሆነ ልፈርም አልገደድም ሲለ ፍቃደኛ ያለመሆናቸውን በመግለፃቸው ምክንያት በቀረበው ክስ የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን ካየ በኋላ ተጠሪዎች መብት ካላቸው አመልካች ካርታ ይስጣቸው በማለት ወስኗል። የከፍተኛው ፍ/ቤትም ጉድለት የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል።
በእኛም በኩል ከሥር ፍ/ቤት የውሣኔ ሐተታ ልንገነዘብ እንደቻልነው አመልካች መብታቸውን አረጋግጦ የቀረቡለትን ወገኖች በእኩል የማስተናገድና አግባብ ያለው ምላሽ ላሰጥ እንደሚገባው ገልጿል። ይህ ማለት ደግሞ አመልካች በሕግ የተቋቋመ አስተዲደራዊ ተቋም በመሆኑ በሕግ በተሰጠው ሥልጣንና ሐላፉነት መሰረት አገልግልት የሚሰጥ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።
እንግዱስ ከዚህ የአመልካች ሥልጣንና ተግባር ስንነሳ ሁለት መብት አለን ብለው የሚቀርቡለትን ወገኖች ሉያስተናግድ የሚችለው ባለው ሕጋዊ አሰራር ብቻ መሆኑን እንረዲለን በዚህ በተያዘው ጉዲይም ተጠሪዎች መብት አለን በማለት ካርታው እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል። በተነጻጻሪ የሥር ሁለተኛ ተከሣሽም በጉዲዩ መብት አላቸው። ይሁን እንጂ የተሰራው ካርታ መጠን የግላን ቤት አካቷል በማለት ቀርበው ሉቀበለ (ሉፈርሙ) ፍቃደኛ አልሆኑም በመሆኑም በአመልካች በኩል እነዚህን ወገኖች አለን በሚለት መብት ለማስተናገድ ይህ የጋራቸው የሆነውን ንብረት መቀበል የሚችለት ፈቅደው በአመልካች መ/ቤት ቀርበው ፈርመው ሲቀበለ ብቻ ነው። አመልካች እነዚህን ወገኖች አስተዲደራዊ ተግባሩን ከመወጣት ባሻገር ሉያስገድዲቸው የሚያስችለው አሰራር የላለው መሆኑን መረዲት አያዲግትም። አመልካችም በክርክሩ እንደገለፀው በውሣኔ ተለይቶ ያልቀረበለትንና ሁለት ወገኖች መብት አለን ብለው ያቀረቡለትን ጉዲይ ላላኛው ባለመብት ባልቀረበበትና ባልተስማማበት ለተጠሪዎች ብቻ አስፈርሞ መስጠቱ ላላ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ተግባር ላሆን ይችላል።
No topics extracted.
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት የሥር ሁለተኛ ተከሣሽን መብት ሣያገናዝቡ ተጠሪዎች መብት ካላቸው ካርታ ይሰጣቸው በማለት አመልካችን ማስገደደ እና የፋ.ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን ሣያርመው ማለፈ የአመልካችን አስተዲደራዊ ሥራ ላይ ጫና መፍጠር ነው።
ባጠቃላይ ፍ/ቤቱም በጉዲዩ ስልጣን የለኝም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 231 መሰረት መዝገቡን መዝጋት ነበረበት።
በመሆኑም የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. በቀን 27/5/2000 እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ቀን 24/08/2000 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ፍ/ቤቶች አመልካችን ካርታ እንዱሰጥ ሉያስገድደ የሚችለበት ሥልጣን የላቸውም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ይቻቻለ መዘገቡ ወደ መዘገብ ቤት ተመልሷል።