No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሙከሚል መሐመድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሚፍታህ ከድር - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ አመልካች ታህሣሥ ዐ3 ቀን 1994 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ ከአሁኑ ተጠሪ ጋር የንግድ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ በመካከላቸው የተፈጠረውን ያለመግባባትም በስምምነት ለመፍታት ተስማምተው ሽማግላዎችን መምረጣቸውንና የተመረጡት ሽማግላዎችም ህዲር ዐ8 ቀን 199ዐ ዓ.ም ውሣኔ መስጠታቸውን፣ በውሣኔው መሰረትም የጋራ ንብረት ክፍፍል ተፈጽሞ ቀሪ ብር 170,122.75 /አንድ መቶ ሰባ ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሁለት ብር ከሰባ አምስት ሣንቲም/ ከአሁኑ ተጠሪ የሚፈለግና ለአመልካች የሚከፈል መሆኑ ተገልፆ በሽማግላዎች ቢወሰንም ተጠሪ ሉከፍለ አለመቻላቸውን በመዘርዘር ተጠሪ እንደውሣኔው እንዱፈጽሙላቸውና ወጪና ኪሣራ የመጠየቅ መብታቸው እንዱጠበቅላቸው ዲኝነት ጠይቀው በተጠሪ ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት የአፈፃፀም ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በፍርድ ተከሣሽነት ቀርበው ከአመልካች ጋር በግልግል ወይም በሽምግልና ዲኝነት ለመዲኘት የተደረገ የግልግል ስምምነትም ሆነ የተሰጠ የግልግል ዲኝነት ያለመኖሩን፣ የተደረገውም ስምምነት የእርቅ ውል ስምምነት መሆኑን፣ የእርቅ ስምምነቱ ውሣኔ ከተባለም የግልግል ቃልችን በጽሐፍ ስላላረጋገጡ የማይገደደ መሆኑን፣ አስታራቂ ሽማግላዎችንም የማያውቋቸው፣ የእርቅ ስምምነቱም ጉድለት ያለበት መሆኑን እንዱሁም በ23/ዐ2/9ዐ ዓ.ም በተደረገው ስምምነት ባለጉዲዮችን ለማስታረቅና ለማግባባት ተገልፆ እያለ ወደ ግልግል ወይም የሽምግልና ዲኝነት መሄደ ሕጋዊነት የላለው መሆኑን ዘርዝረው ሉፈፀም የሚችል ውሣኔ የለም በማለት ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመርና ምስክሮችን በመስማት በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ስምምነት እርቅ /conciliation/ መሆኑንና የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3322/2/ በሚያዘው መሰረት የግልግል ቃልችን የሚያረጋግጥ የጽሐፍ ግዳታ አለመኖሩን ጠቅሶ የአፈፃፀሙን ክስ ውድቅ አድርጎ ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔን አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሰኔ 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈት 3 /ሦስት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የቤተዘመድ የሽምግልና ጉባዔው ያከናወነው ስራ በግራ ቀኙ በ23/ዐ2/9ዐ ዓ.ም በተደረገው ስምምነት መሰረት የግልግል ሁኖ እያለ የእርቅ ስራ ነው መባለ ስለእርቅና ግልግል የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ባላገናዘበ መልኩ መሆኑን የሽምግልና ዲኝነቱ የተሰጠውም የግራ ቀኛችን ማስረጃ መሰረት አድርጎ ሁኖ እያለና ይኸው አካል በጥብቅ የፍ/ቤቶችን የዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓት እንዱከተል የሚያዝ ሕግ ሣይኖር የሽምግልና ዲኝነቱ የፍ/ቤቶችን የዲኝነት አካሄድ ያልተከተለ ነው የተባለው ያላግባብ መሆኑን ዘርዝረው የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ተሽሮ በቤተዘመድ ሽምግልና ጉባዔ ውሣኔ መሰረት እንዱፈፀም ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በዋለው ችልት ተደምጧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበትና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስ ውድቅ የተደረገው ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ጥቅምት 23 ቀን 199ዐ ዓ.ም የተደረገ ስምምነት መኖሩን፣ ከዚህ ስምምነት በኋላም ህዲር ዐ8 ቀን 199ዐ ዓ.ም የቤተዘመድ ሽምግልና ጉባዔ ውሣኔ መስጠቱን ነው። ስምምነቱ መኖሩን በተመለከተ የስር ፍ/ቤትም ያረጋገጠው ጉዲይ መሆኑን ከውሣኔው ግልባጭ ተመልክተናል። የስር ፍ/ቤት የጥቅምት 23 ቀን 199ዐ ዓ.ም ስምምነት እና የህዲር ዐ8 ቀን 199ዐ ዓ.ም በሽምግልና ጉባዔ አባላት ተሰጠ የተባለ ውሣኔ መኖሩን አምኖ ለጉዲዩ እልባት የሰጠው በሽማግላዎች ተሰጠ የተባለው ውሣኔ የግልግል ስምምነት /arbitration/ ሣይሆን የግልግል እርቅ /conciliation/ ሆኖ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2322/2/ የተመለከተውን ድንጋጌ ያላሟላ ነው በሚል ምክንያት ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዳዎች ተብለው በአብዛኛው ከሚታወቁት መንገድች መካከል ድርድር /conciliation/፣እርቅ /mediation/ ግልግል /arbitration/እና ስምምነት /Negotiation/ የሚጠቀሱ ሲሆን በሀገራችን ከሚሰሩት የሽምግልና ዓይነቶች ውስጥ ድርድር፣ ግልግልና እርቅ ይገኙበታል። የስር ፍ/ቤት ለጉዲዩ እልባት ሲሰጥ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባቸው የሽምግልና ዓይነቶች ድርድር /conciliation/ እና ግልግል /arbitration/ ስለሆነ እነዚህ አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዳዎች በፍትሐብሕር ሕጉና በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ያላቸውን ትርጉምና አፈፃፀም መመልከቱ ተገቢነት አለው።
ድርድር /conciliation/ የሚባለው የሽምግልና ዘዳ 3ኛ ወገን ባለበት ግራ ቀኙ ወገኖች የሚደራደሩበት መንገድ ሲሆን 3ኛ ወገን ከመታዘብ በስተቀር በድርድሩ ጣልቃ አይገባም በፍ/ብ/ህ/ቁ. 3318 - 3324 የተመለከቱት ድንጋጌዎችም የሚገዙት ይህንኑ ነው ግልግል /arbitration/ የሚባለው የሽምግልና ዘዳ ደግሞ ግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸውን ለ3ኛ ወገን አቅርበው የግልግል ዲኛው የሚሰጠውን ውሣኔ የሚቀበለበት መንገድ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3325 - 3346 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎችና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315 - 319 እና 35ዐ - 357 የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ስለግልግል አደራረግና አፈፃፀም የሚገዙ ናቸው ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ በሕጉ አግባብ የተደረጉ የግልግል ስምምነቶች ሉፈፀሙ የሚችለ ስለመሆኑ ነው። በፍ/ብ/ህ/ቁ. 3325- 3346 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች በተለይ ሲታዩም የግልግል ስምምነቶች እንደ ልዩ ውልች ሉታዩ የሚገባ መሆኑን ያስገነዝባለ።
ስለግልግል ትርጉም የሚያስቀምጠው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3325 ግልግል ውል ስለመሆኑ ያሣያል። ውል ግዳታዎች የሚቋቋሙበት፣ የሚለወጡበት ወይም ቀሪ የሚሆኑበት ስምምነት እንደመሆኑ መጠን ውል ስለመኖሩ መሟላት የሚገባቸው ነገሮች /elements/ በግልግል ስምምነትም /arbitral submission/ ተሟልተው ሉገኙ ይገባል በመሆኑም የግራ ቀኙ ወገኖች ችልታ፣ የግልግለ ጉዲይ ሕጋዊነት እና በሕጉ የሚፈለግ ከሆነ ፍርም ተሟልተው መገኘት የግልግለን ስምምነት መኖሩን የምናረጋግጥባቸው ጉዲዮች ናቸው ስለሆነም በግልግል የሽምግልና ዘዳ ቀዲሚው እርምጃ ግራ ቀኙ በሕጉ ፉት የሚፀና /valid/ የግልግል ስምምነት ገብተው መገኘት ነው።
በሕጉ አግባብ በተደረገ የግልግል ስምምነት መሰረት የግራ ቀኙን ጉዲይ ክርክር የግልግል ዲኛ መመልከት ከጀመረ በኋላ ሉከተል የሚገባውን ሥነ ሥርዓት በተመለከተ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.3345 ድንጋጌ ያሣያል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 317/1/ ድንጋጌ ሲታይ ደግሞ የግልግል ዲኛ ክርክሩን መምራት ያለበት በተቻለ መጠን የመደበኛ ዲኝነት አካሄድን ተከትል መሆኑን ይገልፃል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ተከራካሪ ወገኖች የመስማት፣ ማስረጃዎቻቸውን የማቅረብና የመጠየቅ መብታቸው ሉጠበቅ እንደሚገባ እና የዲኝነት አሰጣጥም በዚህ ረገድ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ሉከተል የሚገባው መሆኑን እንገነዘባለን። ይሁን እንጂ የግልግል ዲኛ የዲኝነት አካሄድ የመደበኛ ፍ/ቤት የዲኝነት አካሄድን መከተል ያለበት ቢሆንም እንደ መደበኛ ፍ/ቤት የዲኝነት አካሄድ እጅጉን የጠበቀ እንዱሆን የማይጠበቅ መሆኑን የተጠቃሹ ድንጋጌ መንፈስ ያስረዲል። በግልግል ዲኛ የሚሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 35ዐ እና ተከታዮቹ መሰረት በበላይ ፍ/ቤት በይግባኝ ቀርቦ እስካልተለወጠ ድረስ በመደበኛ ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ በሚፈፀምበት ሥርዓት ቀርቦ ሉፈፀም የሚችል መሆኑንም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3345/2/ ድንጋጌ ያስገነዝባል።
በመሆኑም በግልግል ዲኛ የሚሰጥ ውሣኔ የመጨረሻ ነው የግልግል ውለም ውል እንደመሆኑ መጠን በአግባቡ እስከተቋቋመ ድረስ ተዋዋይ ወገኖችን የሕግን ያህል የሚያስገድድ፣ በቃላቸው እንዱታሰሩ የሚያደርግ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3325' ን' ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1731 ጋር አጣምረን ስንመለከት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የግልግል ውል አላደረግኩም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የላለና በግልጽ ያልተካደ ስለመሆኑና ይኸው ውል ስለመኖሩ የበታች ፍ/ቤትም ያረጋገጠው ጉዲይ ነው። የግልግል ውለ ጥቅምት 23 ቀን 199ዐ ዓ.ም ስለመደረጉና በአመልካች፣ በተጠሪና በአቶ ሱልጣን ሸኑሪ መካከል ንብረትንና ገንዘብን አስመልክቶ የተነሣውን አለመግባባት ለማስታረቅ ጉባዔዉ መቋቋሙን፣ ጉባዔው ያየውንና የወሰነውን ለመቀበል ተዋዋይ ወገኖች የተስማሙበት እንዱሁም ተዋዋይ ወገኖችና ሽማግላዎቹ ፊርማቸውን ያኖሩበት ስለመሆኑ ያሣያል። ህዲር ዐ8 ቀን 199ዐ ዓ.ም የተሰጠው የግልግል ዳኞች ውሣኔም መሰረት ያደረገው ይህንኑ ውል ሁኖ ገንዘብና ንብረትን በተመለከተ ግራ ቀኙን ተዋዋይ ወገኖች በማስተማመንና በማጣራት የተዋዋይ ወገኖች ድርሻ ተለይቶ የተወሰነ መሆኑን ይገልፃል።የስር ፍ/ቤት በ23/2/199ዐ ዓ.ም የተደረገው ሰነድ የእርቅ ስለመሆኑ አሸማጋይ የተባለት ግለሰቦች መስክረዋል በማለትና የፍ/ብ/ሕ/ቁ.
3322/2/ ስር የተመለከተውን በመጥቀስ ነው። ይሁን እንጂ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.
3318-3324 ስር በተመለከቱት የሚገዛ ሣይሆን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3325-3346 ባለት ድንጋጌዎች የሚገዛ ስለመሆኑ በ23/2/199ዐ ዓ.ም የተደረገው የግልግል ውል ይዘቱ ያሣያል። የህዲር ዐ8 ቀን 199ዐ ዓ.ም ውሣኔ የተሰጠውም ተዋዋይ ወገኖችን በማስተማመንና ተገቢው ማጣራት ተደርጎ መሆኑ የግልግል ዲኝነት በጥብቅ የፍ/ቤቶችን የዲኝነት ሥርዓት እንዱከተል ሕጉ የማይጠብቅ መሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 317 ከተመለከተው ድንጋጌ አኳያ ተዲምሮ ሲታይ ጉዲዩ በግልግል / arbitration / አልታየም ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም በአመልካችና በተጠሪ መካከል በ23/ዐ2/199ዐ ዓ.ም በተደረገው የግልግል ውል ሰነድ ላይ ግራ ቀኙ ያስሟሟቸው ሽማግላዎች የሚወስኑትን እንደሚቀበለ መስማማታቸውና ውሣኔ የማሣለፍ ሥልጣኑም ለሽማግላዎች የሰጡ መሆናቸው ተገልፆ እያለ የስር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው እርቅ /conciliation/ እንጂ ግልግል /arbitration/ አይደለም በማለት ተጠሪ በሽማግላዎቹ የተወሰነውን ገንዘብ ለአመልካች ሉከፍለ አይገደደም ሲል የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 3325- 3346 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315-319 እንዱሁም ከቁጥር 35ዐ-357 ድረስ የተመለከቱትን ለማስረጃነት ከቀረበው ሰነድ ይዘት ጋር ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐዐ136 መስከረም 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ተሰጥቶ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 6ዐ538 ሚያዝያ ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
2/ ተጠሪ በሽማግላዎቹ የተወሰነውን ገንዘብ ብር 17ዐ,122.75 /አንድ መቶ ሰባ ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሁለት ብር ከሰባ አምስት ሣንቲም/ ለአመልካች እንዱከፍለ ሉገደደ ይገባል ብለናል።
3/ የፋዳራለ መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔውን እንዱያስፈጽም ጉዲዩ ተመልሶለታል። ይፃፍ።
4/ በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።