No summary available.
ታህሳስ 23 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዋሽ ተፊሰስ ባለስልጣን - ነ/ፈጅ ዘመድ ገ/አምላክ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ህያብ ገ/መድህን ብረታ ብረት ማቅለጫ ፊብሪካ - ጠበቃ ሰሞን ባርናባስ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ጨረታን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ኀዲር 04 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ የአሁኑ አመልካች የተገለገለባቸውን ብረት ነክ የሆኑ የተለያዩ ንብረቶችን ለፈላጊዎች በጨረታ አወዲድሮ ለመሸጥ በአወጣው የጨረታ ማስታወቂያ መሰረት ዝርዝር መመሪያውን በማንበብ በጨረታ የሚሸጡትን ንብረቶች በጠቅላላ የሚገዛበትን ዋጋ በማቅረብ እና ድርጅቱ በተለየ መልኩ በድርድር ንብረቶችን የመሸጥ ሐሣብ ካለው በመደራደር ለመግዛት ፍላጏት ያለው መሆኑን በመግለጽ በተጠሪ ስም በሰም በታሸገ ኢንቨልፔ ለጨረታው በተከፈተው ሣጥን ማስገባቱን ጨረታው በይፊ በተከፈተበት ቀንም በመደራደር ተጠሪ የተሻለ ዋጋና የድርድር ሃሣብ በማቅረብ ተመርጦ ከጨረታው ኮሚቴ ጋርም በመደራደር ለጨረታው የቀረቡትን ንብረቶች በብር 200.000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለመግዛት ስምምነት ተደርሶ ኮሚቴው ቃለ ጉባኤ ይዞ ግዥው ፀድቆ ለስራ አስኪያጅ ለፊርማ ከቀረበ በኋላ ጨረታው ውድቅ ነው ተብል እንደገና እንዱካሄድ በማለት ስራ አስኪያጁ የጨረታ ውጤቱን መሰረዛቸውን ዘርዝሮ የጨረታው ኮሚቴ በወሰነው መሰረት የተጫረተውን። ንብረት አመልካች እንዱሸጥና ኪሣራና ወጪ እንዱከፍል ይወሰንለት ዘንድ የዲኝነት ጥያቄ በዞን ሦስት ከፍተኛ ፍ/ቤት በአሁኑ አመልካች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም በፍ/ቤቱ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ህዲር 17 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ በዋና ዲይሬክተሩ አማካኝነት መከላከያ መልሱን አቅርቧል። በመከላከያ መልሱም በጨረታው ላይ የተከሰቱት ጉድለቶች ምን እንደሆኑ በመዘርዘር በእነዚህ ምክንያቶች ጨረታው የተሰረዘ መሆኑንና በስራ አስኪያጁ ባልፀደቀ የጨረታ ውጤት ክስ ላቀርብ የማይችልበት ስለመሆኑ ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ተጠቃሹ ፍ/ቤትም የጨረታ ኮሚቴ አባላትንና የአመልካችን መ/ቤት የሕግ ክፍል ባልደረባን በምስክረነት ከሰማ በኋላ ለጨረታ የቀረበው ንብረት ለተጠሪ በድርድር መሸጡን ኮሚቴው ገልጾ ያቀረበው የውሣኔ ሐሣብ በአመልካች መ/ቤት ስራ አስኪያጅ ባይፀድቅም ሽያጩ ተግቢነት ያለው ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል በማለት በኮሚቴው በተሰጠው የውሣኔ ሐሣብ የአሁኑ አመልካች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጠሪ ብሩን ከፍል ንብረቶችን እንዱያነሣ ወጪና ኪሣራ በድምሩ ብር 5850.50(አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ብር ከሃምሳ ሣንቲም) እንዱከፈለው ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ቅሬታውን ለአፊር ቤሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሚያዝያ 13 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚልባቸውን ምክንያቶች ዘርዝሯል። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ እንዱቀርብ ተደርጏ ግንቦት 22 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልስ ተሰጥቷል። አመልካችም ግንቦት 28 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልስ አቅርቦ የግራ ቀኙ ክርክር ተጠናቅቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የጨረታ ኮሚቴ ተጠሪን የጨረታ አሸናፉ በማድረግ የወሰኑት የውሳኔው ሐሣብ በአመልካች መ/ቤት ስራ አስኪያጅ ሣይፀድቅ እንደ በመጨረሻ ውሣኔ ተደርጏ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ የሚለው ጭብጥ ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ ተጠሪ የጨረታ ዋጋ ሣይገልጽ የጨረታው ተሣታፉ ሆነው ጨረታው በኋላ ግን ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤት የጨረታ ኮሚቴ ጋር በመደረራደር ጨረታውን በብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንደአሸነፈ ተገልጾ የጨረታው ኮሜቴ የውሣኔ ሐሣብ በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፉ ቀርቦ አለመጽቁን ነው።
በመሰረቱ ማንም ሰው ሐብቱን በሐራጅ የሚሸጥ መሆኑን ባስታወቀ ጊዜ ውል ተፈፀመ ለማለት የሚቻለው በመጨረሻው ሐራጅ ለጨረታ የቀረበው ሐብት ለዋጋ አቅራቢው የተሰጠ ጊዜ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1688/2/ የተደነገገ ሲሆን የጨረታ ሥነ ሥርአትን በሚደነግጉት የፍትሐብሕር ሕግ አንቀጽ አስራ ዘጠኝ ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መካከልም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3167/1/ አሸናፉ የሆነውን ተጫራች ለጊዜው ጽ/ቤቱ ቢመረጥ ውለ እንደተፈጸመ የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ ተመልክቷል። የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1688/2/ ድንጋጌ ከፍ/ህ/ቁ. 3168 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ ሲታይም የጨረታውን ሥርአት ያስፈፀመው ያስተዲደር መ/ቤት የጨረታውን ውጤት በመቀበል ውለን ፈጽሟል ልባል የሚችለው የማጽደቅ ሥራ ከተደረገ በኋላ ስለመሆኑ ያስገነዝባል።
No topics extracted.
በልላ በኩል አመልካች የመንግስት መ/ቤት እንደመሆኑ መጠን የግዥ፣ የሽያጭና ላልች ተያያዥነት ያላቸውን ጉዲዮችን የመንግስት የፊይናንስ አዋጅ ፣ደንብና መመሪያን መሰረት በማድረግ የሚፈጽም መሆኑ የግድ ነው።
የመንግስትን የፊይናንስ አዋጅ ደንብና መመሪያ መሰረት አድርጏ ተፈፀመ የሚባል የግዥም ሆነ የሺያጭ ስራ ስራውን እንዱያከናውን የተቋቋመው ኮሜቴ የራሱን የውሳኔ ሐሳብ ገልጾ ለመ/ቤቱ የበላይ አላፉ አቅርቦ ተገቢ ከማስወሰን ባለፈ የጨረታን ውጤቱን በተመለከተ የመጨረሻ ውሣኔ መስጠት አይችልም። የጨረታውን ውጤት በተመለከተ የመጨረሻ ውሣኔ የመስጠት ሕጋዊ ስልጣን የመ/ቤቱ የበላይ ሐላፉ ነው። የጨረታ ኮሚቴ የሚያቀርበው የውሣኔ ሐሣብ በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፉ ሉሰረዝ፣ ሉሻሻል ወይም ሉፀድቅ ይችላል። በመሆኑም የኮሚቴው የውሣኔ ሐሣብ ውል እንደተፈፀመበት የሚቆጠረው በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፉ ተቀባይነትን አግኝቶ አሸናፉው ተጫራች ተለይቶ ሲጸድቅ ብቻ ነው። ህግም ጥበቃ የሚያደርገው በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፉ የፀደቀውን የጨረታ ውጤት እንጂ የኮሚቴውን የውሳኔ ሐሣብ አይደለም።
የኮሚቴው የውሣኔ ሐሣብ በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፉ ከመጽደቁ በፉት ለጊዜው ለተለየው አሽናፉ መብትና ጥቅም ሉያሰጥ አይችልም።
በያዝነው ጉዲይ የጨረታው ኮሚቴ ባቀረበው የውሣኔ ሐሣብ ተጠሪን የጨረታው አሸናፉ አድርጏ ተጠሪ የተመረጠበትን ምክንያት ጭምር በመግለጽ ለመ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ቢያቀርብም ሥራ አስኪያጁ በጨረታው ላይ የተከሰቱ ጉድለቶ አለ በሚል ምክንያት የኮሚቴውን የውሣኔ ሐሣብ አለማጸደቃቸው ተረጋግጧል። እንዱህ ከሆነ የስራ አስኪያጅ ስራ ተገቢ አይደለም ከተባለ ለሚመለከተው የበላይ የአስተደደር አካል ጥያቄ በማቅረብ ተገቢውን ምላሽ ከማግኘት በስተቀር መብትና ጥቅም ላሰጥ የሚችል ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ግንኙነት ሣይኖር መደበኛ ክስ በፍ/ቤት የሚቀርብበት አግባብ የለም። ሥራ አስኪያጁ በህጉ አግባብ አልሰሩም ከተባለ የመንግስት የፊይናንስ አዋጅ ደንብና መመሪያ መሰረት ተገቢውን አስተዲደራዊ መፍትሓ ከመጠየቅ በስተቀር ከወዱሁ የፍትሐብሕር ክስ የሚቀርብበት ሥርአት አለ ለማለት ስለማይቻል ተጠሪ የስራ አስኪያጁ አድራጏት ሥርአት የለሽ አሰራርን ያሰፍናል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በአጠቃላይ የጨረታው ኮሚቴ የውሣኔ ሐሣብ እንደመጨረሻ ውሣኔ ታይቶ አመልካችን ለመክሰስ የሚያስችል ከህግ ወይም ከውል የመነጨ መብት የማይሰጥ በመሆኑ በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠ ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ