No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣሥ ዐ9 ቀን 2ዐዐ1 ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የሰሜን ቀጠና ጉምሩክ - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡-
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በኮንትሮባንድነት የተያዘ 71/ሰባ አንድ/ ኩንታል በአደራ ተጠምጦ ከቆየ በኋላ ባለመመለሱ ዋጋው ይከፈለኝ ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ አመልካች የአሁኑ አንደኛ ተጠሪ በመረብለኸ ወረዲ በራማ ከተማ በኮንትሮባንድ ወንጀል የተያዘ ሰባ አንድ ኩንታል ቡና በአደራ በመጋዘን ለማስቀመጥና እንዱሁም አቅርብ በተባለበት ጊዜ ለማስረከብ ካልቻለ ግን እጥፍ አድርገው 142 /አንድ መቶ አርባ ሁለት/ ኩንታል ቡና አድርገው ለመመለስ የውል ግዳታ መግባታቸውን፣ ሁለተኛ ተጠሪ በበኩላቸው ደግሞ ለአንደኛ ተጠሪ ዋስ ሆነው ተጠሪው ቡናው ካልመለሱ ሰባ አንድ ኩንታል ቡና ለመመለስ ውል መፈረማቸውን በመዘርዘር አንደኛ ተጠሪ በውለ መሰረት 142 ኩንታል ቡና ዋጋ ብር 34ዐ,8ዐዐ.00 /ሦስት መቶ አርባ ሺህ ስምንት መቶ ብር/፣ ይህንኑ መክፈል የማይችለበት ምክንያት ካለ ደግሞ ሁለተኛ ተጠሪ በገቡት የዋስትና ውል መሰረት የሰባ አንድ ኩንታል ቡና ዋጋ ብር 17ዐ,4ዐዐ.00 /አንድ መቶ ሰባ ሺህ አራት መቶ ብር/ እንዱከፍለ ይወስንለት ዘንድ ዲኝነት በመጠየቅ በተጠሪዎች ላይ በመሰረተው ክስ ነው። ተጠሪዎችም ቀርበው አለን ያለትን መከላከያ መልስ አቅርበዋል። አንደኛው ተጠሪ ባቀረቡት የመከላከያ መልስ በጉዲዩ በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡት የፊርማ ሰነድ ባለመመርመሩ እንጂ ተመስክሮባቸው አለመሆኑን፣ ውልም አለመኖሩን፣ ቡናው የላላ ሰው መጋዘን በጉምሩክ ፕሉሶች ተከራይቶ የተቀመጠ እንጂ ተጠሪ የተረከቡት አለመሆኑን በመዘርዘር የተከራከሩ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ በበኩላቸው ዋስ የሆኑት አንደኛውን ተጠሪ ለማቅረብ እንጂ ሰባ አንድ ኩንታል ቡና ለመክፈል አለመፈረማቸውን በመግለጽ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ማዕከላዊ ዞን ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር፣ የምስክሮችን ቃል ከሰማና በውለ ላይ አለ የተባለው ፊርማ የተጠሪዎች ስለመሆኑ ወይም አለመሆኑ የፍረንሲክ ምርመራ ውጤት እንዱቀርብ ከአደረገ በኋላ ተገቢ ነው ያለውን ጭብጥ ይዞ ጉዲዩን በመመርመር በመልካች በኩል የቀረበ ማስረጃ ዝቅተኛ ነው በማለት ተጠሪዎችን በነፃ አሰናብቶ ወስኖአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልትም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ሚያዝያ ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ፡- ለክርክሩ መነሻ የሆነው በኮንትሮባንድ ተያዘ የተባለው ቡና አንደኛ ተጠሪ በአደራ ስለመረከባቸው በዚሁ መሰረት መልሰው ባለማስረከባቸው በእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተብለው ተቀጥተው ያለ፣ ሁለተኛ ተጠሪ ደግሞ ዋስ ሁነው መፈረማቸውን የሚያሣዩ ሰነድች ቀርበው እያለ ተጠሪዎች ተጠያቂነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ ሉታረም ይገባል በማለት የቡናውን ዋጋ እንዱከፍለ ይወስን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪዎች ቀርበው ሰኔ 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓቱንና ጥንካሬውን በተመለከተ ምክንያቶችን በመዘርዘር ክርክሩ በበታች ፍ/ቤቶች በሚሰማበት ወቅት የቀረቡት ጭብጦችና የማስረጃዎች ሁኔታ ተጠሪዎችን ኃላፉ ለማድረግ ብቃት ያላቸው ስላልሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች ነ/ፈጅ በበኩላቸው የተጠሪዎችን የመልስ ማመልከቻ ነጥቦችን አንድ በአንድ በማንሣት ተገቢነት የላላቸው መሆኑን በመዘርዘር እና የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ሐምል 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን አቅርበዋል። ይህ ችልትም የሰነድ ማስረጃዎችን ይዘት ተመልክቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር፣ የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህ ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ተጠሪዎች ተጠያቂነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ሲሆን የአላፉነት መጠኑም ተያይዞ ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ሀ/ አላፉነትን በተመለከተ አመልካች ክሱን ሉመሰርት የቻለው በኮንትሮባንድ ወንጀል የተያዘ ቡና አንደኛ ተጠሪ በአደራ አስቀምጠው እንዱያቆዩ፣ ሲጠየቁም በተጠየቀበት ጊዜ ለማስረከብ፣ ይህ ካልሆነ እጥፍ አድርገው ለመክፈል ኀዲር 17 ቀን 1989 ዓ.ም.
በተፃፈ ሰነድ ስምምነት አድርገው በስምምነቱ መሰረት ሉፈፀምለት ባለመቻለ ነው። ይህንኑ ፍሬ ነገር ለማስረዲትም የውለን ሰነድ፣ አንደኛ ተጠሪ በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡ ስለመሆኑ የሚያሣይ የፍ/ቤት ውሣኔ፣ ለአንደኛ ተጠሪ የተሰጠ ማስጠንቀቂያና የሰው ምስክሮችን አቅርቧል። ተጠሪዎች በውለ ላይ ያለውን ፊርማ በመካዲቸው ምክንያትም ፊርማቸው እንዱመረመር ተደርጎ የተጠሪዎች መሆን አለመሆኑ ሉለይ አለመቻለን በግለጽ መርማሪው አካል በደብዲቤ ገልጿል። በውለ ነበሩ የተባለ ምስክሮች እንደሰሙ ተደርጎም ሁለቱ ምስክሮች ውለን እንማያውቁና ያልፈረሙበት መሆኑን፣ ቀሪው ምስክር ግን ውለ መኖሩን በመግለጽ መስክረዋል።
የበታች ፍ/ቤቶች ለእነዚህ የአመልካች ማስረጃዎች ክብደት ያልሰጡት ፊርማው ተመርምሮ ሉለይ አለመቻለና ሁለት ምስክሮች ውለን የማያውቁ መሆናቸው ተረጋግጧል በማለት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1726፣ 1727፣ 27ዐ9፣ 2787፣ 28ዐ2 እና 1922/3/ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ የአመልካች ማስረጃ ዝቅተኛ ነው በሚል ምክንያት ነው።
በአመልካችና በአንደኛ ተጠሪ መካከል የተቋቋመው ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2779 ሥር የተመለከተውን ትርጓሜ ሉያሟላ የሚችል የአደራ ውል ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎች ይዘት በግልጽ ያሣያል። በግራ ቀኙ መካከል ያለው ውል የአደራ ከሆነ ደግሞ ጉዲዩ መታየት የሚገባው በዚህ ረገድ የተመለከቱት የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ነው። እነዚህ ድንጋጌዎች ሉተው የሚችለት ለጉዲዩ እልባት ለመስጠት የማያስችለ ሆነው ሲገኙ ብቻ ስለመሆኑ የሕግ አተጓጎም መርህ ያስገነዝባል። የበታች ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ከአደራ ውል አኳያ የተመለከቱት ስለመሆኑ የውሣኔ ይዘት ቢያሳይም በዚህ ረገድ በዋቢነት የተጠቀሱት ድንጋጌዎችም ሆነ ከጠቅላላ የውል ክፍል የተጠቀሱት ድንጋጌዎች የማስረጃውን ዝቅተኛነት ለማሣየት አግባብነት የላላቸው መሆኑን ይህ ችልት ተገንዝቧል። ለአንድ ውሣኔ በዋቢነት ሉጠቀስ የሚገባው ድንጋጌ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው እንጂ ተዛማጅነት የላለው ላሆን አይገባም።
አመልካች በክሱ ላይ የተገለፀውን ፍሬ ነገር እርግጠኛነት ለፈራጅ ለማሣመን ያቀረባቸው የሰነድ እና የሰው ምስክሮች ናቸው። የሥር ፍ/ቤት ከቀረቡት የአመልካች ማስረጃዎች መካከል አንደኛ ተጠሪ በጉዲዩ በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ የተባለበትና የተቀጡበትን የፍ/ቤት ውሣኔ ለጉዲዩ ያለውን አግባብነት ወይም ብቁነት ሳይገልጽ ስለማለፈ የውሣኔው ግልባጭ ያሳያል። የተቆጠረው ወይም የቀረበው ማስረጃ ለክርክሩ መነሻ ከሆኑት ፍሬ ነገሮች ጋር ግንኙነት እያለው እና ፍሬ ነገሮችን ለማረጋገጥ በሕጉ ክልከላ ያልተደረገበት የማስረጃ ዓይነት እስከሆነ ድረስ በጉዲዩ ላይ የቀረቡት ሁለም ማስረጃዎች መመዘን አለባቸው በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ሁለን ማስረጃዎች በአንድነት ሣይመዘኑ የተወሰኑትን ብቻ ነጥል በመወሰድ የሚሰራ ምዘናም ሆነ ውጤት ፍትሐዊነት አይኖረውም።
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስ አንደኛ ተጠሪ በጉዲዩ ላይ በወንጀል ተከሰው በፍ/ቤቱ ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡ መሆኑንና በበላይ ፍ/ቤትም አለመለወጡ ተረጋግጦ እያለ ይህ የአመልካች ማስረጃ በሰበር ፍ/ቤት በዝምታ ታልፎል።
ይህም የማስረጃ አቀባበል ሥርዓትን ያልተከተለ ነው። የዚህን ማስረጃ አግባብነት እና ብቁነት ስንመለከተውም ለጉዲዩ በማስረጃነት ላቀርብ ወይም ክብደት ሉሰጠው አይገባም የሚባልበትን የሕግ ምክንያት አላገኘንም። በወንጀል ጉዲይ የተሰጠ ውሣኔ በዚያው ጉዲይ በፍትሐብሕር በማስረጃነት አግባብነት እና ብቃት የሚኖረው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ ሕ/ቁ. 2149 ተቃራኒው ንባብ ያስገነዝባልና። በዚህ ድንጋጌ መሰረት በወንጀል የተሰጠ ውሣኔ በፍትሐብሕር ለቀረበው ክስ በማስረጃነት አግባብነት የሚኖረው በወንጀል ክሱ በወንጀል ፍ/ቤት ተከሣሹ ጥፊተኛ ተብል ከተወሰነ ስለመሆኑ እና ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት የወንጀል ክስ ማስረጃ አመዛዘን መርህ ከፍትሐብሓሩ የበለጠ ጠንካራና የማያሻማ ማስረጃ የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ አያዲግትም። የሥር ፍ/ቤት የአመልካችን ማስረጃ ክብደት የመዘነው ከፍረንሲክ ምርመራ ውጤት መግለጫና ከተሰሙት ምስክሮች ቃል አንፃር እንጂ በወንጀል ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ ከሕጉ ጋር አገናዝቦ አይደለም።
በመሰረቱ የፍረንሲክ ምርመራ ውጤት በውለ ሰነድ ላይ የተመለከተው ፊርማ የተጠሪዎች አይደለም በሚል የማይገልጽ፣ ይልቁንም ለመለየት ያልተቻለ መሆኑን የሚያስረዲ ነው። በመሆኑም በዚህ መልኩ የተገለፀውን የባለሙያ አስተያየት በውለ ላይ ያለው ፊርማ የተጠሪዎች አይደለም ብል ለመደምደም የሚያስችል ማስረጃ /conclusive evidence/ አይደለም። በመሆኑም የፍረንሲክ ምርመራ ውጤት ተቀባይነት የሚያገኝበት የሕግ ምክንያት የለም።
ከተሰሙት የአመልካች ምስክሮች ውስጥም አቶ ጎይቶኦሞ ገ/ሕይወት የተባለት በ17/ዐ3/1989 በተፈረመው የውል ሰነድ ላይ የፈረሙ መሆናቸውን የውለ ሰነድ የሚያሣይ ከመሆኑም በላይ በወንጀል ችልት በዓቃቤ ሕግ ምስክርነት ቀርበው የአደራ ውለን መኖር መመስከራቸው ከመረጋገጡ አኳያ በፍትሐብሕር ክስ ጊዜ ውለን አላውቀውም፣ አልፈረምኩም ማለታቸው የምስክሩን ቃል ተዓማኒነት በመቀበል የውል ሰነደንና የወንጀል ችልት ውሣኔ ሰነድ የማስረጃነት ተገቢነት /admissibility/ ሉያስቀር የሚችል አይደለም ሁለተኛ ተጠሪም በወንጀል ችልት የመሰከሩ ከመሆናቸውም በላይ በውለ ሰነድ ላይ መፈረማቸውን ሣይክደ የፈረሙበት ምክንያት አንደኛ ተጠሪን ለማቅረብ ብቻ ነው ማለታቸውን፣ የውለ ይዘት ይኸው የነበረ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐዐ6/1/ በሚያዝዘው መሰረት መቃወሚያ ማስረጃ ሣያቀርቡ የሚከራከሩ በመሆኑ ክርክራቸው የሕግ መሰረት የላለው ነው። ላላው ሁለተኛ ተጠሪ የዋስትና ውለን በተመለከተ ያቀረቡት የሕግ መከራከሪያ ሲታይም በውለ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው አንደኛ ተጠሪ የተረከቡትን ቡና ካልመለሱ 71 /ሰባ አንድ/ ኩንታለን ቡና ለአመልካች ለማስረከብ የተጠቀሰ በመሆኑ ዋሱ እዲውን አውቀው እንደፈረሙ የሚያሣይ ነው ከሚባል በስተቀር የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1922/3/ ድንጋጌን መስፈርት እያሟላም ልባል የማይገባ ሆኖ በመገኘቱ በዚህ ረገድ የቀረበው መከራከሪያ ነጥብ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ተጠሪዎች የአመልካች ማስረጃ አቀራረብም ሥርዓቱን ያልጠበቀ፣ በስር ፍ/ቤት ሣይቀርብ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ የማይገባ ነው በማለት የተከራከሩ መሆኑንም ይህ ችልት ተገንዝቧል። ሆኖም በአመልካች በኩል የተጠቀሱት ማስረጃዎች በስር ፍ/ቤት ተዘርዝረው የቀረቡ መሆናቸውን የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ የሚያሣይ በመሆኑ የማስረጃው አቀራረብ ሥርዓቱን ያልጠበቀ ነው ለማለት አልተቻለም።
በመሆኑም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች የበታች ፍ/ቤቶች በተጠሪዎች አላፉነት ላይ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ የተገኘ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሣኔ ተሽሮ ተጠሪዎች በአደራ ተቀምጦ ለአመልካች ላልተመለሰው ቡና አላፉ ሉባለ የሚገባ ነው ብለናል።
ለ/ የአላፉነትን መጠን በተመለከተ፡- ጉዲዩ በአደራ ውል ድንጋጌዎች መገዛት ያለበት መሆኑ ከላይ ተገልጿል።
በመሆኑም የተጠሪዎች የሃላፉነት መጠን መታየት ያለበትም አደራ ይዘት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት አንደኛ ተጠሪ በአደራ የተረከቡትን ቡና ሲጠየቁ ካልመለሱ እጥፍ አድርገው ለመመለስ በሕዲር 17 ቀን 1989 ዓ.ም. ተደረገ በተባለው ውል የተስማሙ ቢሆንም ይኸው ግዳታቸው በጠቅላላ የውል ድንጋጌዎች መገዛት የላለበት በመሆኑ፣ የአደራ ተቀባዩ በአደራ የተቀመጠውን ዕቃ እንዱመልስ ሲጠየቅ ያለበት ሕጋዊ ግዳታ በአደራ የተቀመጠውን ዕቃ መመለስ እንጂ ሉመለስ የሚገባው ዕቃ ሉያስገኝ የሚችለው ጥቅምና ላላ ተያያዥነት ያለው ትርፍ ጋራ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2779 – 2799 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች መንፈስ ስለማያሣይ፣ አመልካች የአንደኛ ተጠሪ የአላፉነት መጠን እጥፍ ላሆን ይገባል በማለት የጠየቀው ዲኝነት ከአደራ ውል ድንጋጌዎች ጋር ተዛምድ የማይሄድ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም፣ የአንደኛ ተጠሪ የአላፉነት መጠን በአደራ ውለ የተገለፀውን 71 /ሰባ አንድ/ ኩንታል ቡና በዓይነት ለአመልካች መመለስ፣ ወይም ይኸው ብዛት ያለው ኩንታል ቡና በወቅቱ ገበያ በነበረው ዋጋ ብር 17ዐ,4ዐዐ.00 /አንድ መቶ ሰባ ሺህ አራት መቶ/ ተብል በአመልካች ተገልፆ በተጠሪ በኩል የቀረበ የተቃውሞ ነጥብ የላለ በመሆኑ አንደኛ ተጠሪ ይህንኑ የገንዘብ መጠን ለአመልካች በአማራጭ የመክፈል ግዳታ አለባቸው።
ሁለተኛ ተጠሪ በአላፉነት መጠኑ ላይ ያቀረቡት ክርክር የዋስትናው ግዳታ መጠን በገንዘብ ያልተጠቀሰ ነው ከሚል ይዘት ውጪ አንድ ኩንታል ቡና በወቅቱ የነበረውን የገበያ ዋጋ መሰረት አድርጎ የቀረበ ባለመሆኑ የአላፉነታቸው መጠን በአንደኛ ተጠሪ አላፉነት መጠን ውጪ የሚሆንበት ምክንያት የለም። በመሆኑም ሁለተኛ ተጠሪ የገቡት ግዳታ ተራ ዋስትና ዓይነት በመሆኑ እና በዚህ የዋስትና ዓይነት ደግሞ ዋሱ ለባለገንዘቡ የሚገደድበት ባለዕዲው ግዳታውን መወጣት ያልቻለ የሆነ እንደሆነ በመሆኑ ሁለተኛ ተጠሪ አንደኛ ተጠሪ መክፈል ካልቻለ ብቻ 71 /ሰባ አንድ/ ኩንታል ቡና በዓይነት ለአመልካች የመመለስ ወይም በአማራጭ የ71 /ሰባ አንድ/ ኩንታል ዋጋ ብር 17ዐ,4ዐዐ.00 /አንድ መቶ ሰባ ሺህ አራት መቶ ብር/ የመክፈል ግዳታ አለባቸው ተብል ሉወሰን የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም ለክርክሩ መነሻ የሆነው በኮንትሮባንድ ወንጀል ተያዘ የተባለው ቡና አንደኛ ተጠሪ በአደራ ስለመረከባቸው እና በዚህ መሰረት መልሰው ባለማስረከባቸው በእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ የተባለበት የፍ/ቤት ውሣኔ በሰነድ ማስረጃነት አመልካች አቅርቦ እያለ የሰው ምስክሮችን ቃል እና ሙለ በሙለ መደምደሚያ ላይ ሉያደርስ የማይችል የፍረንሲክ ምርመራ ውጤት መግለጫ ብቻ ነጥል በመመዘን በ17/ዐ3/1989 ዓ.ም. ተደረገ የተባለውን የአደራ ውል ሰነድ ውድቅ በማድረግ ተጠሪዎች ተጠያቂነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ የማስረጃ አቀባበልና አመዛዘን ሥርዓትን ያልተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በዞኑ ማዕከላዊ ፍ/ቤት ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22296 ጥር 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አንደኛ ተጠሪ ለአመልካች 71 /ሰባ አንድ/ ኩንታል ቡና እንዱያስረክቡ ወይም በአማራጭ ብር 17ዐ,4ዐዐ.0000 /አንድ መቶ ሰባ ሺህ አራት መቶ ብር/ እንዱከፍለ ብለናል።
ሁለተኛ ተጠሪ ለባለገንዘቡ አመልካች የሚገደደት ባለዕዲ አንደኛ ተጠሪ ግዳታቸውን መወጣት ያልቻለ እንደሆነ ብቻ ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መ/ቤት ይመለስ።