No summary available.
ታህሣሥ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ በርገና ሽፈራው - ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
አቶ አብርሃም ሽፈራው
አቶ መስፍን ሽፈራው ወ/ነ/ፈጅ አቶ አብረሃም ሽፈራው ቀረቡ።
ወ/ሮ ታሪኳ ሽፈራው
ወ/ሮ ሽታዬ ሽፈራው - በላለችበት የሚታይ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 2ዐዐ32 በሆነው መዝገብ ግንቦት 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ ተጠሪዎች በወረዲ ፍ/ቤት ከሣሾች ሲሆኑ አመልካች ተከሣሽ ነበር። የክሱም ምክንያት የሟች አባታችን ንብረት የሆነውን የውርስ መሬት ይዞ ስለሚገኝ ድርሻችንን ያካፍለን የሚል ሲሆን አመልካችም በዚሁ መሬት ከዚህ በፉት ታላቅ ወንድማቸው ክስ አቅርቦ ተከራክረን በመ/ቁ. 32/94 በሆነው መዝገብ በ12/9/94 ዓ.ም. የዋለው ችልት ውሣኔ የሰጠ በመሆኑ ላልች ወንድሞቹ ተመሣሣይ ክስ ቢያቀርቡም በተመሣሣይ ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 መሰረት ደግሞ ክስ ሉያቀርቡ አይገባም። አባታችን የሞቱት በ1973 ዓ.ም. በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐዐዐ/1/ መሰረት ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ የተከራከረ ስለመሆኑ መዝገቡ የስረዲል። በመጀመሪያ ደረጃ ያከራከረው የምዕራብ አባያ ወረዲ ፍ/ቤት ከዚህ በፉት ውሣኔ ያገኘ ጉዲይ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5/1/ መሰረት እንደገና ክስ ሉቀረብበት አይገባም አመልካች ከ15 ዓመት በላይ ግብር እየገበረበት የሚጠቀምበት ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክርን መሰረት በማድረግ የከሳሾችን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። የጋሞ ጎፊ ዞን የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤትም የወረዲውን ፍ/ቤት ውሣኔ አጽንቷል። ግራ ቀኙን ያከራከረው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ወንድማቸው አቶ በለጠ ሸፈራው ስለራሱ ተከራከረ እንጂ ከሣሾችን ወክል አልተከራከረም። ስለዚህ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5/1/ መሰረት በማድረግ የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ አይደለም በማለት የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመሻር ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ሰኔ 3 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጽፍ ያቀረበው ቅሬታ፡-
እኔ ከጦር ሜዲ እንደተመለስኩ እንደ እኔ ከጦር ሜዲ ግዲጃቸውን ፈጽመው ለተመለሱ ሲሰጣቸው የተሰጠኝን ይዞታ መሬት አርሼ ለ19 ዓመታት ከተጠቀምኩ በኋላ የተጠሪዎች ታላቅ ወንድም በ1993 ዓ.ም. ክስ መስርቶ ተከራክረን በተወሰነው ጉዲይ እንደማያውቁ ሆነው ክስ ማቅረባቸው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5/1/ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው፣
ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐዐዐ/1/ መሰረት በይርጋ እንደሚታገድ በማስመልከት ያቀረብኩትን ክርክር የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሳያጣራ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሣኔ በመሆኑ ተሽሮ የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ እንዱፀና እንዱወሰንልኝ የሚል ነው።
ቅሬታውን መሰረት በማድረግ ለማጣራት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ታዞ መስከረም 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
የተፃፈ መልስ ከ1-3 ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተጠሪዎች መልስ አቅርበዋል። የመልሱም ፍሬ ሀሣብ አቶ በለጠ ሽፈራው ያቀረበው የይዞታ ክርክር እንጂ የውርስ ንብረት ክርክር አይደለም። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5/1/ ለክርክሩ አግባብነት የለውም።
አመልካችም በ5/3/2ዐዐ1 በተፃፈው የመልስ መልስ ወንድማቸው ያቀረበው ክስ የውርስ ጥያቄ ነው። የይርጋ ክርክርም ቢሆን ከበታች ፍ/ቤቶች ጀምሮ የተከራከርኩበት መዝገብ ያስረዲል በማለት ተከራክሯል።
No topics extracted.
እኛም የግራ ቀኙን ክርክር አግባብ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔዎች አግባብነት እንደሚከተለው መርምረናል።
ግራ ቀኙ የሚከራከሩት የሟች አባታቸው ይዞታ የነበረ ሙዝና ቋሚ ሰብል ያለበት በውርስ ሉደርሰን የሚገባንን አመልካች ለብቻው ይዞ ይጠቀማልና ድርሻችንን ያካፍለን በማለት ነው። የአመልካች ክርክር ደግሞ ለ19 ዓመታት በእጄ አድርጌ የምጠቀምበት ነው። ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት ይከራከራል። አባታቸው የሞቱት በ1973 ዓ.ም. መሆኑን ግራ ቀኙ አልተካካደም። ለተጠሪዎች በአመልካች ላይ መሬቱን እንዱያካፍላቸው ክስ ያቀረቡት ሰኔ 6 ቀን 1999 ዓ.ም.
ነው።
በመሰረቱ ከሣሽ መብቱንና የውርስ ንብረቶች በተከሣሹ መያዛቸውን ካወቀ ሦስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለወራሽነት የሚያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንደማይኖረው አመልካች ጠቅሶ በሚከራከረው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐዐዐ/1/ ሥር ተደንግጓል። አባታቸው ከሞቱበት ከ1973 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ ክስ እስከቀረበበት ሰኔ 6 ቀን 1999 ዓ.ም. ድረስ ያለው ጊዜ ሲሰላ 26 ዓመታት ያሕል አስቆጥሯል። በሕጉ አነጋገር ተጠሪዎች የአባታችን መሬት በዚህ ጊዜ ነው በአመልካች መያዙን ያወቀነው በማለት የይርጋው ጊዜ ሉያሳጥርላቸው የሚችልበትን ለይተው የተከራከሩበት ወይም መያዙን አላወቅንም ሲለ የተከራከሩበት ወይም በልላ ምክንያት ይርጋው ሉቋረጥ የሚችልበትን ምክንያት መሰረት በማድረግ ያደረጉት የሕግ ክርክር የለም። የመሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ሕዝብና የመንግሥት ከመሆኑ አንፃር ከዘር የወረደ ርስት ነው ተብል የሚጠየቅ አይደለም። ይህ ባልሆነበት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከላልች የክርክር ነጥቦች በቀዲማይነት ላታይ የሚገባውንና አመልካችም ከወረዲ ፍ/ቤት ጀምሮ በጥብቅ የሚከራከርበትን የመቃወሚያ ክርክር ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት በላለበት በዝምታ በማለፍ የወረዲውንና የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ ሲል የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐዐዐ/1/ መሰረት በወራሾች መካከል የሚደረግ የውርስ ጥያቄ ክርክር ከ3 ዓመት በኋላ ላቀርብ እንደማይገባ የተደነገገውን ሕግ ትርጉም የልጠበቀና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁጥር 2ዐዐ32 በቀን ዐ1/ዐ9/2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
የተጠሪዎች ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐዐዐ/1/ መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል ብለናል።
የምዕራብ አባያ ወረዲ ፍ/ቤት አመልካች በመሬቱ መሰረት አድርጎ የሰጠው ውሣኔና የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤትም የፀናው በአግባቡ ነው ብለን ውሣኔዎቹን አጽንተናል።
ወጪና ኪሣራ የዚህ ፍ/ቤትን ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
ውሣኔው ዛሬ በ22/ዐ4/2ዐዐ1 በንባብ ተሰማ።