No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 37ዐ5ዐ ታህሣሥ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወሉ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሻምበል ሁሴን አሉ - ጠበቃ መድህን መሐሪ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሱማላ ክልል ዐ/ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የጅጅጋ ዞን ዐ/ሕግ መስከረም ዐ2 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈው የክስ ማመልከቻ የአሁኑ አመልካች በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1ሀ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ነሐሴ 26 ቀን 1998 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሲሆን በጅጅጋ ዞን ፕሉስ ጽ/ቤት ፉት ለፉት የሱፍ መሐመድ ሰሉም ይባል የነበረውን ግለሰብ ታጥቆት በነበረው ሽጉጥ አንድ ጥይት በመተኮስ ራሱ ላይ በመምታት ለህልፈት የዲረገው በመሆኑ ሉቀጣ ይገባል በማለት በመሰረተው ክስ መነሻ ሲሆን የአሁኑ አመልካች በተከሣሽነታቸው ቀርበው ክሱ ከተነበበላቸው በኋላ ፍ/ቤቱ ለክሱ የሚከራከርለትን ጠበቃ እንዱፈቅድላቸው ጠይቀው ፍ/ቤቱም ተከሣሹን የክሱ ማመልከቻ የሚለውንና የተነበበው የገባቸውና የተረደት መሆኑን ጠይቋቸው ተጠሪም የተረደት መሆኑን ለፍ/ቤቱ ከገለፁ በኋላ የድርጊት አፈፃፀሙን በተመለከተ ግን በዐ/ሕግ የክስ ማመልከቻ በተከሰሡበት ዓይነት አልፈፀምኩም ሲል የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ከዚህም በኋላ ለጥቅምት ዐ8 ቀን 1999 ዓ.ም ለሆነው ቀጠሮ የዐ/ሕግ ምስክሮች እንዱቀርቡ አመልካች ጠበቃቸውን ይዘው እንዱቀርቡ ተደርጎ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሉቀርቡ አለመቻላቸው የአመልካች ጠበቃም ያልቀረቡ መሆኑ ተረጋግጦ ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዞ የዐ/ሕግ ምስክሮች ሲቀርቡ የአመልካች ጠበቃ በልላ ቦታ ላይ በነበራቸው ቀጠሮ ምክንያት ያልቀረቡ መሆኑን በመግለጽ ተጠሪ ቀጠሮው በአዲሪ /ለተከታዩ ቀን/ እንዱለወጥላቸው ቢጠይቁም በዐ/ሕግ በኩል ነገሩን ያጓትተዋል የሚል ተቃውሞ ቀርቦ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙ አዲምጦ ጠበቃው የበለጠ ጊዜ ሉጠበቅ አይቻልም፣ ግራ ቀኙም ተስማምተውበታል በማለት የአመልካች ጠበቃ ሣይቀርቡ ወይም ላላ ጠበቃ ሣይተካ የዐ/ሕግ ምስክሮች እንዱሰሙ ተደርጓል። አመልካች የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸውን ዐ/ሕግ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በፀዲ ሁኔታ አረጋግጦባቸዋል ተብል እንዱከላከለ ከተደረገ በኋላ መከላከያ ማስረጃ የማቅረብ መብታቸውን መተዋቸውን ገልፀዋል ተብል ከታለፈ በኋላ የዐ/ሕግ ተጨማሪ ምስክሮች እንዱሰሙ ተደርጓል። ከዚህም በኋላ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ አመልካችን በዐ/ሕግ የክስ ማመልከቻ በተጠቀሰው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጎ በሞት እንዱቀጣ ወስኖበታል። ከዚያም የአሁኑ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ እንዱከራከሩ ከተደረገ በኋላ ይኸው ፍ/ቤትም በአመልካች ላይ የተሰጠውን የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሚያዚያ ዐ4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈት 7/ሰባት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ ጠበቃ የመወከል መብታቸው ያልተጠበቀላቸው መሆኑን፣ የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀማቸው በማስረጃ ያልተጋጠባቸው መሆኑን መከላከያ ማስረጃ የማቅረብ መብታቸው የታለፈውም በቂ ጊዜ ሣይሰጣቸው መሆኑን፣ የተጨማሪ ማስረጃ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ መሆኑን የጥፊተኛነት ውሣኔ የተሰጠበት ድንጋም አግባብነት እንደላለው እና የሞት ቅጣት ፍርደም ተገቢነት የላለው መሆኑን በመዘርዘር የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ይሻርላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል የክልለ ዓ/ሕግ ሐምል ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመለከቻ መልስ ሰጥቷል። አመልካች በበኩላቸው ህዲር 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ምበተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሱን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች የተከሱበት ጉዲይ ከባድ መሆኑ እየታወቀ በጠበቃ ሣይወከለ ክርክሩ መካሄደና ውሣኔ መሰጠቱ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከመዝገቡ የክርክር ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በስርፍ/ቤት የቀረቡትና የእምነት ክህደት ቃል የሰጡት መስከረም ዐ4 ቀን 1999 ዓ.ም ሁኖ በዚህ ዕለት ጠበቃ ያልተወከለላቸው መሆኑን፣ ጥቅምት ዐ8 ቀን 1999 ዓ.ም የዐ/ሕግ ምስክሮች እና የአመልካች ጠበቃ እንዱቀርቡ ተገልጾ ቀጠሮ በተያዘበት ቀንም የአመልካች ጠበቃ አለመቅረባቸው፣ በተከታዩ ቀነ ቀጠሮም የዐ/ሕግ ምስክሮች ቀርበው የአመልከች ጠበቃ ሣይቀርቡ የቀሩበትን ምክንያት አመልካች ለፍ/ቤት ገልፀው የዐ/ሕግ ምስክሮች ጠበቃቸው በበነጋው ሲቀርቡ እንዱሰሙላቸው ቢያመለክቱም ተቀባይነት በማጣት የዐ/ሕግ ምስክሮች አመልካች በጠበቃ ባልተወከለበት ጊዜ የተሰሙ መሆኑ መረጋገጡን ነው።
በመሰረቱ በወንጀል ፍትህ አስተዲደር የተያዙና የተከሰሱ ሰዎችን በተመለከተ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግሥት የተካተቱትን መብቶችን የሚገልፁት ድንጋጌዎች አቀራረፅና ይዘታቸው ሲታይ በተቻለ መጠን ወዱያውኑ ሉተገበሩ የሚገባ መሆኑን ያስገነዝቡናል። ከዚህም በላይ በወንጀል ፍትህ አስተደደር የተያዙና የተከሰሡ ሰዎች ሕገ- መንግሥታዊ መብታቸውን የዲኝነት አካለ የማክበርና የማስከበር ሕገ መንግሥታዊ ግዳታ ያለበት መሆኑን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 13/1/ ስር በግልጽ አስቀምጧል። በመሆኑም የተያዙና የተከሰሡ ሰዎች ሕገ መንግሥታዊ መብት የማክበርና የማስከበር ግዳታ በዲኛው ትከሻ የወደቀ ስለመሆኑ ሉስተዋል ይገባል። በወንጀል ፍትህ አስተዲደሩ ዳኞች ይህንኑ ግዳታ ሲወጡ ደግሞ ማህበረሰቡ የሂደቱን ፍትሃዊነት ከማክበሩም በተጨማሪ የሂደቱን ውጤትም በአክብሮት እንዱቀበል ያደርጋል። የሕግ ሥርዓቱ በሕገ-መንግሥቱ ጥበቃ የተደረገላቸውን የዜጎች መብቶች የማክበርና የማስከበር ግዳታ ካልተወጣ ደግሞ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነትና አክብሮት እንደሚቀንስ ይታመናል። ስለሆነም በሕገመንግሥቱ የተመለከቱት ሰብአዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር የግድ ይሎል።
አንድ በወንጀል ፍትህ አስተዲደሩ የተያዘና የተከሰሰ ሰው ከሂደቱ መጀመሪያ እስከ ፍፃሜ ድረስ በሕገ-መንግሥቱ ከተረጋገጠለት ሰብአዊ መብቶች መካከል አንደ በጠበቃ የመወከል መብት ነው። ይህ መብት ተከሣሹ በራሱ የሚፈልገውን ጠበቃ በማቆም ሉጠቀመው የሚችለው ወይም ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣቱ ፍትህ ሉጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም በመንግሥት ወጪ ጠበቃ በማቆም ሉከበርለት የሚገባው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 2ዐ/5/ድንጋጌ ያስገነዝባል። ከድንጋጌው መንፈስ የምንገነዘበውም ተከሣሹ ራሱ በመረጠው ጠበቃ የመወከል ሕገመንግሥታዊ መብቱን አንዱጠቀም በቂና አሣሣኝ ጊዜ ከመስጠት በተጨማሪ ይኸው መብት እንዲለውም በችልቱ ሉገለጽለት የሚባው መሆኑን ነው።
ይህ ብቻ ሣይሆን ተከሣሹ ብቃት ባለው ጠበቃ መወከለም ሉያረጋገጥ ይገባል። ይህ ሁለ የፍ/ቤቱ የስራ ድርሻ ነው። ስለሆነም በጠበቃ የመወከል መብት ትልቅ ሕገ- መንግሥታዊ መብት መሆኑን ለመገንዘብ አያዲግትም።
እጃችን ወደአለው ጉዲይ ስንመለስም የአሁኑ አመልካች ከሂደቱ መጀመሪያ ጀምሮ እስከመጨረሻው በፈለጉት ጠበቃ የመወከል ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው በቂና አሣማኝ ጊዜ ተሰጥቷቸው በስር ፍ/ቤት የተከበረላቸው አለመሆኑን ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። በመሆኑም የአመልካች ሕገ-መንግሥታዊ መብት ሣይከበር የተሰጠ የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉሻር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
195/2/ለ1/ መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል ይፃፍ።
አመልካች በመረጡት ጠበቃ የመወከል ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ሉከበር ይገባል ብለናል።
አመልካች በመረጡት ጠበቃ የመወከል ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ተከብሮ ጉዲዩ ከዚህ በፉት ባላዩት ዳኞች እንደገና ታይቶ ተገቢው ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩን ለጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መልሰናል። ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.