No summary available.
ኀዲር 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሸምሱ ከድር አህመድ - ቀርበዋል።
ተጠሪ፡- የኢ.ፋ.ዳ.ሪ የፍትህ ሚኒስቴር - አልቀረቡም ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ይህ አቤቱታ የቀረበው አመልካች ሚያዝያ 22 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻቸው እንደገለፁት የኢ.ፋ.ዳ.ሪ የፍትህ ሚኒስቴር በቁ. 12 ጥ/2029/2037 ታሕሳስ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ለአመልካች ባሳወቀው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ወደ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢቀርብም ፍርድ ቤቱ በመ/ቁ. 62758 የካትት 25 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 ይግባኙን በመሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟልና ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች መስከረም 9 ቀን 2000 ዓ.ም ለተጠሪ በፃፈት ማመልከቻ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ እንዱፈቀድላቸው ቢያመለክቱም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአመልካች ጥያቄና ማስረጃ በማገናዘብ በሰጠው ውሳኔ አመልካች ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮላጅ ነሐሴ 10 ቀን 1998 ዓ.ም በሕግ ዱፔልማ ከተመረቁ በኋላ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀጽ 8/1/ መሰረት በሙያው 5 ዓመት ያላገለገለ ናቸው በማለት የአመልካች ጥያቄን ሳይቀበለው ቀርቷል።
አመልካችም በዚህ ውሳኔ ቅሬታ በማሳደር ወደ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ በመ/ቁ.
62758 የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 ሰርዞታል።
አመልካችም ሚያዝያ 22 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም አግባብነት ባለው የሕግ ሞያ ከ12 ዓመት በላይ ማለትም ከሰኔ 01 ቀን 1981 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 1985 ዓ.ም በአውራጃ አቃቤ ሕግነት፣ ከሐምል 01 ቀን 1985 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1988 ዓ.ም ድረስ በወረዲ አቃቤ ሕግ ሐላፉነት እንዱሁም ከጥቅምት 01 ቀን 1989 ዓ.ም እስከ ግንቦት 14 ቀን 1995 ዓ.ም ድረስ በአዱስ አበባ ከተማ መስተዲደር በነገረ ፈጅነት ያገለገልኩና በ1981 ዓ.ም ለአውራጃ አቃቤ ሕግነት የተሰጠውን ስልጠና በመከተታል የሕግ ስርተፍኬት እንዱሁም ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮላጅ በሕግ ዱፔልማ ያለኝ ማለትም የኢትዮጵያ መሰረታዊ ሕጏች የማወቅ ነኝ፤ ይህ ሁኔታ ደግሞ አዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀጽ 8/1/ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት ወደ ፈተና ለመቀመጥ የሚያበቃኝ ሆኖ እያለ ተጠሪው እና የስር ፍርድ ቤቱ ሕጉን አላግባብ በመተርጏም ዱፔልማው ካገኘህበት ጊዜ ወዱህ ቢያነስ 5 አመት ማገልገል ይጠበቅብሐል ማለታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል፤ በተጠቀሰው አንቀጽ የተመለከተው መስፈርት በተለይም ደግሞ በሞያው 5 ዓመትን የማገልገል ሁኔታ በህግ ዱፔልማ ከተመረቅኩ ወዱህ ብቻ ሳይሆን ከመመረቄ በፉት የሰጠኋቸውን አግባብነት ያላቸውን አገልግልቶቼም የሚጨምር ነው፤ስለሆነም የፈፀሙት የሕጉን የአተረጓጏም ስህተት ታርሞልኝ የጠየቀኩትን የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የሚያስችለኝን ፈተና እንድወስድ ሆኖ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ተጠሪም ሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የሰጠ ሲሆን ይዘቱም አመልካች የሕግ ዱፔልማውን ካገኙ በኋላ የ5 ዓመት ግልጋልት ስለላላቸውና ከዚያ በፉት የነበሯቸው አገልግልቶች ለተፈለገው የጥብቅና ፍቃድ ብቃት ስለላላቸው ቦርደ በአዋጁ አንቀጽ 8/1/ መሰረት የተመለከቱትን መስፈርቶች ያልተሟለ ሆኖ ስላገኘው የአመልካች ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ በመሆኑ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጡ ከላይ እንደተገለፀው ሆኖ ፍርድ ቤቱም አመልካች ላቀረቡት የጥብቅና ፈቃድ ጥያቄ የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ያሟላለ ወይስ አያሟለም? የሚል መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል፡ከላይ እንደተጠቀሰው የአመልካች ጥያቄ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ማግኘት ሲሆን ይህ የጥብቅና ደረጃ የሚመለከቱ መስፈርቶች በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀጽ 8/1/ በግልጽ የተዘረዘሩ ሲሆኑ እነዚህም በሕግ ዱፔልማ ያለው፣ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ሕጏችን ማወቅ እንዱሁም አግባብነት ባለው ሞያ ቢያንስ 5 ዓመታትን ማገልገል የሚለ ናቸው፣ የአመልካች ጥያቄ ከእነዚህ መስፈርቶች አኳያ ሲታይ ደግሞ ቀደም ብል የሕግ ሰርተፍኬት (በ1981 ዓ.ም የተሰጠ) የነበራቸውና ነሐሴ 10 ቀን 1998 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮላጅ በሕግ ዱፔልማ ማግኘታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች የትምህርቱን መስፈርት ያሟለና የኢትዮጵያ መሰረታዊ ህጏች እንደሚያውቁ ነው። የሰጡት ግልጋልትም ሲታይ በአውራጃ አቃቤ ህግነት ለ4 ዓመታት፣ በወረዲ አቃቤ ሕግ ሐላፉነት ለ2 ዓመት ከዘጠኝ ወራት እንዱሁም በአዱስ አበባ ከተማ ነገረ ፈጅነት ለ6 ዓመት ከ8 ወራት አካባቢ በጠቅላላ ወደ 13 ዓመታት መስራታቸውን ስለሚያሳይ ከዚሁ ውስጥም ለጠየቁት የጥብቅና ደረጃ ከ5 ዓመታት በላይ ማገልገላቸው ያሳያል፤ ቀጥል መታየት ያለበት ነጥብ በተጠቀሰው አንቀጽ የሰፈረው የ5 አመታት አገልግልት የግድ መቆጠር ያለበት ዱፔልማ ካገኙበት ነው ወይ? የሚለው ነው። ሕጉ በግለጽ እንደሚያሳየው የ5 አመታት አገልግልት የግድ በዱፏልማ ከተመረቁ በኋላ የሰጡት መሆኑ አያሳይም፣ እነዚህ መስፈርቶች ራሳቸውን ችለው የተቀመጡ እንጂ የአገልግልት ዘመኑ መቆጠር ያለበት የሕግ ዱፔልማ ካገኙበት ጊዜ ጀምሮ አይደለም። በአጠቃላይ አመልካች ለጠየቁት የጥብቅና ፈቃድ ደረጃ በሕጉ የተመለከቱትን መስፈርቶች ያሟለ ሆነው እያለ ተጠሪው ሚኒስቴርም ሆነ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መስፈርቱን እንዲላሟለ በማድረግ ያስቀመጡት የሕጉ አተረጎጏም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
ተጠሪ በቁ. 12 ጥ/2029/2037 ታህሳስ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ለአመልካች ያሳወቀው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 62758፣የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ ተሽረዋል፤ ይፃፍ።
አመልካች ለጠየቁት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጥብቅና ፈቃድ በአዋጅ ቁ. 199/1992 አንቀጽ 8/1/ የተዘረዘሩትን የትምህርት ደረጃ፣ የአገልግልት ዘመንና የሕግ እውቀት የሚያሟለ ስለሆነ ተጠሪው ፈተና ሉፈትናቸው ይገባል፤ ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ። ጉዲዩ ያለቀ ስለሆነ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.