No summary available.
ኀዲር 25 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ፈርተውሐል ወ/ጊዮርጊስ ቀረቡ ተጠሪ፡- አንበሣ ጫማ አ/ማ - ጠበቃ መኮንን ኪዲኔ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በጡረታ አዋጅን የተመለከተውን የጡረታ መዋጮ ክፍያን በወቅቱ ገቢ ያለማድረግን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ጥቅምት 24 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ የአሁኑ ተጠሪ የጥር ወር 1992 ዓ.ም ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ብር 39,974.35(ሰላሣ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አራት ብር ከሰላሣ አምስት ሣንቲም) ለአመልካች ድርጅት ገቢ ያደረገው ከሦስት ዓመታት በኋላ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም መሆኑን በመግለጽ ለዘገዬበት 2%(ሁለት በመቶ) ተጨማሪ ክፍያ የመክፈል ህጋዊ ግዳታ ያለበት በመሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 ስራ ላይ ከዋለበት ከሰኔ 01 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ድረስ ብር 41,573.32(አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሦስት ብር ከሰላሣ ሁለት ሣንቲም)፣ ከሐምል 01 ቀን 1998 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ ብር 8,474.56(ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰባ አራት ብር ከሃምሣ ስድስት ሣንቲም) በድምሩ ብር 50,047.88 (አምሣ ሺህ አርባ ሰባት ብር ከሰማኒያ ስምንት ሣንቲም) ከነ ህጋዊ ወለድ እና በቂ ወጪና ኪሣራ ጋር ተጠሪ እንዱከፍል ይወሰንለት ዘንድ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በተከሣሽነቱ ቀርቦ አዋጁ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ ነው፣የክፍያ ጥያቄውም ሁለት ዓመት ያለፈበት በመሆኑ እንደተከፈለ የሚቆጠር ስለመሆኑ የሚለትን ነጥቦችን በመቃወሚያነት፣ለአመልካች በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ገቢ ባልሆነው የመዋጮ ገንዘብ ላይ ብቻ በመሆኑ እና ተከሳሽም የተጠየቀውን እዲ ስለከፈለ ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ ጥያቄ መቅረቡ ከአዋጁ ዓላማ ውጪ መሆኑን የተጠየቀው የጡረታ መዋጮ ተጨማሪ ክፍያ ይመለከተዋል ቢባልም ስላቱ ተገቢነት የላለውና በማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን በፍሬ ነገር መከራከሪያ ነጥብነት በማንሣት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የተጠሪን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችን በመመርመር አመልካች የሚጠይቀው መብት በጥር ወር 1992 ዓ.ም እንደመሆኑ መጠን ይህ በ1998 ዓ.ም የተከፈለው እንኳን ቢሆን ከአዋጁ በፉት የተገኘው መብት በአዋጁ መሰረት ሉገዛ ስለማይችል አዋጁ ወደ ኋላ ተመልሶ ተፈፃሚ ላሆንበት የማይችል ነው በሚል ምክንያት የአመልካችን ክስ ወድቅ አድርጏ ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ጥር 27 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ የ1992 ዓ.ም ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ገቢ የተደረገው ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም መሆኑና ክፍያ የተጠየቀውም አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እንጅ ወደ ኋላ አለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ ሕጉ ወደ ኋላ ሂድ አይሰራም ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባል በመባለ ተጠሪ ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል። በመልሱ ላይም የአመልካች ጥያቄ የህግ ድጋፍ የላለው ስለመሆኑ ያሣያለ ያላቸውን መከራከሪያ ነጥቦች በማንሣት ተከራክሯል።
አመልካች በበኩለ ሰኔ 16 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በአዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 7/3/ መሰረት የጡረታ መዋጮ ለዘገየበት 2%(ሁለት በመቶ) ተጨማሪ ክፍያ ተጠሪ ሉከፍል አይገባም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ድርጅት የጥር ወር 1992 ዓ.ም ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ብር 39,974.35(ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አራት ብር ከሰላሣ አምስት ሣንቲም) ለአመልካች ድርጅት ገቢ ያደረገው ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም መሆኑን ነው። ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረው የአዋጅ ቁጥር 345/95 ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም፣ይሰራል ከተባለም የሁለት ዓመት ጊዜ ያለፈ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024/ሰ/ መሰረት እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው፣ስላቱም የተሣሣተ ነው የሚለትን ነጥቦችን በማንሣት ነው። እኛም እነኚህን የመከራከሪያ ነጥቦች ከህጉ ጋር አገናዝበናል።
በዚህ መሰረት የአመልካች ድርጅት ዲኝነት የጠየቀበት መብት የበሰለው በጥር ወር 1992 ዓ.ም ውዝፍ የጡረታ መዋጮ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። በዚህ ወቅት በተጠሪ ዓይነት አካላት ተፈፃሚነት የነበረው ሕግ የመንግስት የሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 49/1967 ሲሆን በዚህ አዋጅ ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ተጨማሪ ክፍያ የሚከፈልበት ስለመሆኑ የሚያመላክት ድንጋጌ አልነበረም። ይህንኑ አዋጅ የሻረው አዋጅ ቁጥር 345/1995 ዓ.ም በአንፃሩ ውዝፍ የጡረታ መዋጮ የ2% /ሁለት በመቶ/ ተጨማሪ ክፍያ እንደሚከፈልበት በአንቀጽ 7/3/ ስር ደንግጓል። ይህ አዋጅ ስራ ላይ የዋለው ከሰኔ 01 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን የመሸጋገሪያ ድንጋጌም ይዟል። የአዋጁ መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀጽ 52/1/ የሚያሣየውም አዋጁ ከመጽናቱ በፉት ለተፈጠሩ ህጋዊ ሁኔታዎች /legal situations/ ቀደም ሲል ሲሰራባቸው የነበሩ ህጏችና መመሪያዎች ተፈፃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ ነው። ከዚህ የድንጋጌ መንፈስ በግልጽ መገንዘብ ከሚቻለው የአዋጅ ቁጥር 345/1995 ዓ.ም ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑን ነው። አዋጁ ተፈፃሚነቱ ከሰኔ 01 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑ በአንቀጽ 56 ስርም በግልጽ ተመልክቷል። ከዚህ የአዋጁ አቀራረጽ መረዲት የሚቻለው መብቶቹ በነባር ህጏችና መመሪያዎች የተፈጠሩ ከሆነ የሚፈፀሙትም በነባሮቹ ህጏችና መመሪያዎች መሆኑን ሲሆን አሁን በተያዘው ጉዲይ ውዝፍ የጡረታ መዋጮ የመጠየቅ መብት በነባሮቹ ህጏች የተፈጠረ በአዱሱ አዋጅም ቀሪ ስለመሆኑ ያልተመለከተ ሁኖ በዚህ ውዝፍ መዋጮ ተጨማሪ ክፍያ የማስከፈል መብት የተፈጠረው በአዱሱ አዋጅ ነው።
ስለሆነም አመልካች ተጠሪን መጠየቅ የማይችለው ከጥር ወር 1992 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 1995 ዓ.ም ባለት ጊዜያት ውስጥ ያለውን ተጨማሪ ክፍያ እንጂ በአዱሱ አዋጅ መጽናት በኋላ ላለት ጊዜያት ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ተጨማሪ ክፍያን ልባል አይገባም። የአመልካች ጥያቄም ከሰኔ 01 ቀን 1995 ዓ.ም በኋላ ያለትን ጊዜያትን መሰረት ያደረገ መሆኑን አቤቱታው በግል ያሣያል። ተጠሪ የመክፈል ግዳታ የሚኖረው ውዝፍ የጡረታ መዋጮውን ብቻ ነው። ለማለት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት አልተገኘም። በመሆኑም የአመልካች ጥያቄ ከአዋጅ ቁጥር 345/1995 በፉት የተገኘ መብት በመሆኑ በአዋጁ አይገዛም ተብል ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሁኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል ተጠሪ አዋጁ ተፈፃሚነት አለው ከተባለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024/ሰ/ መሰረት ተጨማሪ ክፍያው እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው በማለት የሚያቀርበውን ክርክር ስንመለከተው ተጠሪ ዋናውን ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ወዱያውኑ አለመክፈለን እያመነ ተጨማሪ ክፍያው እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት መከራከሩ ተቀባይነት የላለው ከመሆኑም በላይ አመልካች ድርጅት ተጧሪ ባለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024/ሰ/ አግባብነት ሉኖረው አይችልም። በመሆኑም ተጠሪ ከሰኔ 01 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ገቢ ላላደረገበት ጊዜ ተጨማሪ ክፍያ(2%) ሁለት በመቶ የማይከፈልበትን ህጋዊ ምክንያት አላገኘንም። አመልካች ህጋዊ ወለድ ሉታሰብ ይገባል የሚለው የዲኝነት ጥያቄ ግን ህጉ የ(2%) ሁለት በመቶ ተጨማሪ ክፍያ ይከፈላል ከሚል ውጪ በድጋሚ እንዱታሰብ የሚፈቅድበት ሁኔታ ምክንያት ባለመኖሩ የምንቀበለው ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም የበታች ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 345/1995 ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለውን ምክንያት ብቻ በመያዝ የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የሚኖረበት ስለመሆኑ ባላገናዘበ መልኩ ሆኖ ስለተገኘ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 77477 ግንቦት 10 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 56348 ጥር 15 ቀን 2000 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ከሰኔ 01 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ እስከ
No topics extracted.