No summary available.
ህዲር 4 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1/ አቶ ለማ ኩማ - አልቀረቡም 2/ አቶ አዱሱ ታመነ - አልቀረቡም 3/ አቶ ሺግዛው አስራት - አልቀረቡም ጉዲዩን ከመረመርን በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ አቤቱታ ላቀርብ የቻለው የሃረሪ ሕዝብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. ዐዐ627 ሐምል 14/1997 ዓ.ም የሰጠውን ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበትና ይታረምልኝ በሚል ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በሐረሪ ክልል የአሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ ሲሆን በዚሁ አካል በተደረገ ክርክር የአሁኑ ተጠሪዎች በከሣሽነት የአሁኑ አመልካች ደግሞ በተከሣሽነት እንዱሁም በሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁኑ አመልካች ይግባኝ ባይ የአሁኑ ተጠሪዎች ደግሞ መልስ ሰጭዎች ነበሩ።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ስር ከሣሾች የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች የካቲት 11/1997 ዓ.ም በተፃፈ ወደ ቦርድ ያቀረቡት ክስ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም በተከሣሽ ድርጅት /የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን ሃረር ዱስትሪክት/ ውስጥ በቴክኒክ ሰራተኛነት እየሰሩ ያለ መሆናቸውን ገልፀው ካላቸው አገልግልትና የትምህርት ደረጃ ጋር በማይመጣጠን ደረጃ ዐ3 ተመድበው እየሰሩ እንደሆነና ተከሣሽ በሚመጥናቸው / በሚገባቸው /ደረጃ/ ግሬድ ዐ6 እንዱመድባቸው ቢጠይቁትም ለመመደብ ፍቃደኛ ባለመሆኑ በቦርድ ውሣኔ እንዱስተካከልላቸው የሚጠይቅ ነው።
ስር ተከሣሹም ከላይ ለቀረበበት ክስ የካቲት 29/1997 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ሰጥቷል፤ በዚህ መዝገብ ለተያዘው ጭብጥ አግባብነት ስለላለው ዝርዝሩን ማስቀመጥ ሣያስፈልግ ታልፎል፤ ይሁን እንጂ መሰረታዊ ይዘቱ ክርክሩ በአስማሚ አካል ሣይታይ ቦርደ የማየት ስልጣን እንደላለው የሚገልጽ ነው፡ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያከራከረው ቦርድ ሰኔ ዐ3/1997 ዓ.ም ውሣኔ የሰጠ ሲሆን ስር ተከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች በዚሁ የቦርድ ውሣኔ ቅሬታ በማሣደር ወደ ሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ በመ.ቁ. ዐዐ627 ሐምል 14/1997 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ በአዋጅ ቁ. 377/1996 ዓንቀጽ 139/1/ለ/ መሰረት የተጠቀሰው ቦርድ የሰጡውን ውሣኔ ተከትል ይግባኙን የማየት ስልጣን ለክልል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ማለትም ለክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንጂ ስልጣኑ የሱ እንዲልሆነ በመግለጽ የቀረበለትን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 9/2/ መሰረት ውድቅ አድርጓል።
የአሁኑ አመልካችም ነሐሴ 17/1997 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችልት ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም በሃረሪ ክልል የአሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ በቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ በአስማሚ አካል ሣይታይ ቦርደ ጉዲዩን ተቀብል በቀጥታ ማከራከር እንደላለበትና ጉዲዩም በይርጋ ቀሪ እንደሆነ ገልፆ ተከራክሮ እያለ ቦርደ ሕጉን ሣያገናዝብ በመወሰኑ ተከትል የቀረበለትን ይግባኝ የሃረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስልጣኔ አይደለም በማለት ይግባኙን መሰረዝ የለበትም፤
አዋጅ ቁ. 377/1996 ዓንቀጽ 154 እንዱሁም የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት ዓንቀጽ 8ዐ መሰረት በማድረግ ሲታይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን ይግባኝ ማስተናገድ የነበረበት ሆኖ እያለ ስልጣኔ አይደለም ማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ የሚል ነው፤ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ቢታዘዙም ሉቀርቡ ባለመቻላቸው ጉዲዩ በላለበት እየተካሄደ ነው።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ እየተገለፀ አንደመጣው ሆኖ ይህ ፍርድ ቤትም የሃረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአመልካች የቀረበለትን ይግባኝ የማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚል ጭብጥ በመመሥረት ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል። ይህ የሥራ ክርክር የተጀመረው በሃረሪ ክልል የአሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ ሲሆን ይህ አካል ለቀረበለት ክርክር የመጨረሻ እልባት/ ውሣኔ/ ከሰጠ በኋላ የይግባኝ አቀራረቡ ሥነ-ሥርዓት ምን እንደሚመስል በአዋጅ ቁ. 377/1996 ዓንቀጽ 154/1/ በግልጽ እንደተመለከተው በሕግ በኩል ውሣኔው ተዛብቷል የሚል ወገን ወደ ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስራ ክርክር ችልት ይግባኝ የማቅረብ መብት እንዲለው ነው፤ ቦርድ ያረጋገጣቸው የፍሬ ነገር ክርክሮች በተመለተ ግን የመጨረሻና ክርክር የማይነሣባቸው ነጥቦች በመሆናቸው በአዋጁ ዓንቀጽ 153 ተመልክቷል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኑ ወቅት መዋቅሩ በእያንዲንደ ክልል ያልተዘረጋና በዚሁ የፍርድ ቤት የስልጣን እርከን የሚጠቃለለ ጉዲዮች በክልልች በሚያጋጥሙበት ጊዜ በስልጣን ደረጃ ተመሣሣይ የሆነው የእያንዲንደ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ወክል /ተክቶ/ ክርክሮችን እያስተናገደ የሚገኙበት ነው፤
ከዚህ አኳያም የሃረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረቡለትን ይግባኝ በአዋጅ ቁ.377/1996 ዓንቀጽ 140 እና 154 መሰረት ተቀብል ማስተናገድ ሲገባው የዓንቀጽ 139/1/ለ/ ይዘት በመውሰድ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
ው ሣ ኔ 1/ የሃረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. ዐዐ627 ሐምል 14/1997 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ ተሽሯል።
2/ በተከራካሪ ወገኖች መካከል የተደረገው ክርክር ከሃረሪ ክልል አሰሪና ሰራተኛ ወሣኝ ቦርድ የጀመረ በመሆኑ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁ. 377/1996 ዓንቀጽ 14ዐ እና 154/1/ መሰረት ተቀብል ይግባኙን የማየት ስልጣን አለው፤ ስለሆነም ይግባኙን ተቀብል አከራክሮ እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
341 መሰረት ተመልሶለታል፤ ይፃፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ በት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፉረማ አለበት።
ተ.ወ
No topics extracted.