No summary available.
ሐምል 8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- መምህር ሙለ ኃይለሥላሴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ዘመናዊ ማተሚያ ቤት ጠበቃ አቶ ዓለሙ ወ/አረጋይ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው መቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሆኖ አመልካች ከሣሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ ነበር። ክሱም ተጠሪ መጽሐፍት እንዱያትምልኝ ውል ፈጽሜ በድርጅቱ ሰራተኛ ተሰርቆ በተሸጡት 9 መጽሐፍት ምክንያት ኪሣራ ደርሶብኛልና በአዋጅ ቁጥር 410/96 የተመለከተውን የሞራል ካሣና ሳይሸጡ የቀሩ መጽሐፍት ዋጋ በድምሩ 260,000 /ሁለት መቶ ስድሳ ሺ ብር/ እንዱከፍለኝ የሚል ሲሆን ተጠሪም በሰጠው መልስ ተሰርቋል የተባለው 7 መጽሐፍት እንጂ ላላውን ለመክፈል አንገደድም ሰረቀ የተባለው ሰው ጣልቃ እንዱገባ ይታዘዝልን ስርቆት ግላዊ ባህርይ በመሆኑ ካሣውን ሉከፍል የሚገባው የሰረቀው ሰው ነው በማለት ተከራክሯል።
ግራ ቀኙን ያከራከረው ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱንና ማስረጃውን በማገናዘብ ተሰርቆ ተሸጠ የተባለውን የ9 መጽሐፍት እያንዲንደን በ20 ብር ግምትና በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 34(4) የተመለከተውን የሞራል ካሣ ጭምር 100,180,00 /አንድ መቶ ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ብር/ ለአመልካች ተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል። ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ውሣኔውን በአብላጫ ድምፅ በማጽናቱ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ ችልቱም ተጠሪ ድርጊቱን ሉያውቅ የሚችልበት በቂ ምክንያት በላለበት የሞራል ካሣ 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ እንዱከፍል መወሰኑ ስህተት ነው፤ ተሰርቋል የተባለውን የ7 መጽሐፍት ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ የ7 መፅሐፍት ዋጋ 140,00 /አንድ መቶ አርባ ብር/ እንዱከፍል በማሻሻል ወስኗል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
አመልካች ታህሣሥ 4 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው ቅሬታ፡ተጠሪው ስርቆቱን ቢያውቅም ባያውቅም በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 34/(4) የተመለከተውን አነስተኛ የሞራል ካሣ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የሚያስቀር አይደለም በማለት ውሣኔው እንዱሻር የሚጠይቅ ነው።
ይህ ችልትም የውሳኔውን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ታዞ መጋቢት 2 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት ግራ ቀኙ ቀርበው ክርክርራቸው ተሰምቷል።
ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር በሕግ ረገድ እንደሚከተለው ተመልክቶታል።
የተከራካሪዎቹ ግንኙነት ተጠሪ 5,000(አምስት ሺህ) መጽሐፍት አትሞ ማስረከብ ሲሆን አመልካች ደግሞ ቀሪውን በውል የተመለከተውን ገንዘብ መክፈል ነው። ከዚህ ግንኙነት አንፃር የግራ ቀኙ ክርክር ላታይ የሚገባው በውል ነው ወይንስ ከውል ውጪ ነው? የሚለውን ስንመለከተው፡- አንድ ጉዲይ ከውል ውጪ ነው ልባል የሚችለው አንድ ሰው በራሱ በኩል ምንም የገባው ግዳታ ሳይኖር በራሱ ጥፊት ላደረሰው ጉዲት አላፉ እንደሚሆን ከውል ውጪ የሆኑ የኃላፉነት ምንጮችን ከሚደነግገው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2027 መገንዘብ ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ ግራ ቀኙ ወገኖች ግልጽ ስምምነት አድርገው የውል ግዳታ ገብተዋል። ይኸው የውል ግዳታ ከመፈፀሙ በፉት በስምምነቱ ውስጥ የተካተተው መጽሐፍ በተጠሪ ድርጅት ሰራተኛ ተሰርቆ ገበያ ላይ በመዋለ ምክንያት ግዳታው በተባለው ሁኔታና ጊዜ አለመፈፀም ምክንያት ሆነ ከሚባል በቀር ጉዲዩን የውል ውጪ (extra contractual) አያደርገውም፤ ይልቁንም ውለ ከሚመለከተው የሕትመት ሥራ አንፃር ውለ ሳይፈፀም የተወሰኑ መፃሕፍት በሕትመት ሰራተኛ መሰረቅ የውል መጣስ (breach of contract) የነበረ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የውል መጣስ ወይም ውለ በታሰበው አኳኋን አለመፈፀም ጉዲይ የሚታየው በውል ሕግ እንጂ ከውል ውጪ የሚሆንበት የሕግ አግባብ የለም። ይህን ጉዲይ በየደረጃው ያዩ ፍ/ቤቶች ግዳታውን ከውል የመነጨ ሆኖ እያለ ውለም ባልተካደበት በድርጅቱ ሰራተኛ በመሰረቁ ብቻ ከውል ውጪ ኃላፉነት ተደርጏ መታየቱ ስህተት ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ጉዲዩ ከውል ውጪ መሆኑን ተቀብል ለውሣኔው መሰረት ያደረገው በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 34(5) መሰረት ተጠሪው ድርጊቱን ያላወቀ ከሆነ ወይም ሉያውቅ የሚችልበት በቂ ምክንያት የላለው ከሆነ የሚለውን ትርጉም መሰረት በማድረግ ነው። በአዋጁ አንቀጽ 34(5) የተጠቀሰው “ - - ያላወቀ ከሆነ ወይም ሉያውቅ የሚችልበት በቂ ምክንያት የላለው ከሆነ - - -” የሚለው የሕጉ ትርጉም መጽሐፍን እንዲለ መሰረቅን የሚመለከት ሳይሆን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 መሰረት ጥበቃ የተደረጉ የአዕምሮ መብቶች ሲጣሱ ማለትም ከመፃሐፈ ውስጥ እንደ ቅጅ፣ ማባዛትና ላልች ተመሣሣይ ድርጊቶችን ሳያውቅ የጥሰት ተግባር በተፈፀመ ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆን እንጂ አሁን በተያዘው ጉዲይ ዓይነት ማተሚያ ቤቱ ሚስጥራዊነቱን ጠብቆ እንዱታተም በተገባው ውል ስምምነት መሰረት አትሞ በመስጠት ሂደት ላይ በማተሚያ ቤቱ ሰራተኛ መጽሐፍት ተራ በሆነ ስርቆት ወጥቶ ቢሸጥ ማተሚያ ቤቱ ሉያውቅ ወይም ማወቅ የሚችልበት በቂ ምክንያት አለመኖሩን የሚመለከት አይደለም። ከዚህ አንፃር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ለሕጉ የሰጠው ትርጉም የተሳሳተ ነው። ተጠሪ ስርቆት ግላዊ ባርይ በመሆኑ መጽሐፍትን የሰረቀው ሰው ካሣውን ሉከፍል ይገባል የሚለውን ክርክር በተመለከተ ሰረቀ የተባለው ሰው ግንኙነቱ በአሰሪነት ከተጠሪ ጋር ነው እንጂ ከአመልካች ጋር አይደለም። የውል ግንኙነቱ ከተጠሪ ጋር በመሆኑ ይህ ተዋዋይ ወገን እንደውለ ግዳታውን ያልፈፀመበትን በቂ ምክንያት ካላስረዲና ይህም ምክንያት ከአቅም በላይ መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር የውለ አለመፈፀም ከሚያመጣው ኃላፉነት ሉድን እንደማይችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1791(2) ተመልክቷል። መጽሐፈን የሰረቀው ከውጪ የመጣ ዘራፉ አይደለም። የድርጅቱ ሰራተኛ በሆኑ የመቆጣጠር ኃላፉነት የተጠሪ ሲሆን ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1792(1) መሰረት ከአቅም በላይ የሆነ ሉመልሱት የማይችለ ኃይል ነው የሚያሰኝ አይደለም። እንዱያውም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1792(2) መሰረት በአዕምሮ ግምት መጽሐፈ ሉሰረቅና ወይም ተደብቆ ሉወጣ ይችላል በሚል ተጠሪው ቀደም ብል ሉያስብበት የሚችል ከመሆኑ አንፃር ከአቅም በላይ የሆነ ኃይል ነው ተብል የሚወሰድ አይደለም። ይልቁንም በውለ አለመፈፀም ምክንያት አመልካች የደረሰበትን የጉዲት ኪሣራ እንዱጠይቀው የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1771(1) መብት የሚሰጠው ሲሆን ተጠሪ ምንም ጥፊት ባያደርግ እንኳ በውለ መሰረት ባለመፈፀሙ ምክንያት ብቻ የጉዲት ኪሣራውን መክፈል እንዲለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.791(1) ተመልክቷል። ስለዚህ የጉዲት ኪሣራ ከውልም ሆነ ከውል ውጪ ሉከሰት የሚችል ሲሆን ቁሣዊ ጉዲት ብቻ ሣይሆን የህሉና ወይም የሞራል ጉዲትንም የሚጨምር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1790(2)እና 2090 – 2123 ከተመለከቱ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
የመብቱ ባለቤት ከሆነው ከአመልካች ፈቃድ ውጪ የአዕምሮ ሃብቱ የሆነው መጽሐፍት አመልካች ከመረከባቸው በፉት መሰረታዊ የውል ዓላማ ተጥሶ በውል ተቀባይ ድርጅት ሰራተኛ መጽሐፍት ገበያ ላይ መዋላቸው በፍ/ቤት ተረጋግጧል።
በሕጉ የመብቱ ባለቤት መብቶች ናቸው የተባለት ኢኮኖሚያዊና የሞራል መብቶች ሲሆኑ በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 7 የተመለከቱ ኢኮኖሚያዊ መብቶች አንደ ተጥሶ በተገኘ ጊዜ የሞራል ጉዲት ጥሰት ይኖራል ማለት ነው። አዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 7 የተመለከቱ ኢኮናሚያዊ መብቶች እንደሚከተለው ይነበባል።
ሀ/ ሥራን የማባዛት፣ ለ/ ሥራን የመተርጏም፣ ሐ/ ሥራን የማመሳሰል፣ የማቀናበር ወይም ወደ ላላ አይነት የመቀየር፣ መ/ በሽያጭ ወይም በኪራይ ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጂውን የማከፍፈል፣ ሰ/ ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጂውን ከውጭ ሃገር የማስገባት፣ ረ/ ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጂውን ለሕዝብ የማሣየት፣ ሰ/ ሥራን በይፊ የመከወን፣ ሸ/ ሥራን ብሮድካስት የማድረግ፣ ቀ/ ሥራን በልላ መንገድ የማሰራጨት፣ እንደሆነ ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ በፉደል “ረ” የተመለከተው ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጅውን ለህዝብ ማሳየት የሚለው ድንጋጌ በተጠሪ ተጥሷል። ይኸውም መጸሐፈ ከአመልካቹ ፈቃድ ውጪ ገበያ ላይ ውል በሕዝብ መነበቡ ነው።
አንድ ፉልም ከባለቤቱ ፈቃድ ውጪ ኦርጅናለ ወይም ቅጅው ለሕዝብ ቢታይ የአመንጪው ኢኮኖሚያዊ መብቱ እንደሚጣስ ሁለ አንድ መጽሐፍም እንዱሁ ከአመልካቹ ፈቃድ ውጪ ገበያ ላይ ውል ቢነበብ ኦርጅናል ሥራን ወይም ቅጅውን ለሕዝብ ማሳየት (public display of original or copies of the work) የሚለው በሕጉ የተመለከተው የአመልካች መብት ተጥሷል ማለት ነው። ይህ መብት ተጥሶ የሞራል ጉዲት በደረሰ ጊዜ የካሣው መጠን በአዋጁ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 34(4) መሰረት ከ100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የማያንስ የገንዘብ ካሣ ሉከፍል እንደሚገባ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት በአመልካች ላይ የደረሰውን የህሉና ጉዲት ሞራል ካሣ ተጠሪው በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የመክፈል ግዳታ ይኖርበታል።
የከፍተኛ ፍ/ቤትና የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከላይ እንደተጠቀሰው የግራ ቀኙ ግንኙነት ውል ሆኖ ሳለ ሰራተኛ መጽሐፍ በመሥረቁ ብቻ ከውል ውጪ አድርገው ትርጉም በመስጠት የተመለከቱት በአግባቡ ባይሆንም በውጤት ረገድ ግን በአግባቡ ሆኖ አግኝተናል።
በአጠቃላይ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ ድርጊቱን ያላወቀ ወይም ሉያውቅ የሚችልበት በቂ ምክንያት የላለው ከሆነ የሚለውን ከሕጉ መንፈስ ውጪ የሆነውን ትርጉም መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሣኔ ከፍ ሲል ከተመለከቱት ምክንያቶች አንፃር መሰረታዊ የሕግ ትርጉም ስህተት የተፈፀመበት ውሣኔ ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ
ከትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 25/99 በ11/3/2001 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትና ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ በውጤት ረገድ በአግባቡ ነው ብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት በማፅናት አመልካች የሞራል ካሳ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና የሰባት መፃሕፍት ዋጋ ብር 140 /አንድ መቶ አርባ ብር/ በድምሩ 100,140 /አንድ መቶ ሺ አንድ መቶ አርባ ብር/ ይከፈለው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለን መዝገቡን ዘግተናል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.