No summary available.
ግንቦት 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ብራንድ ኒው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ኃ/የተ/የግ/ማኀበር ጠበቃ አቶ ቸርነት ወርድፊ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ መስፍን ታደሰ - አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሆኖ ተጠሪ ከሳሽ ሲሆኑ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበር።
የክሱ ምክንያት መጋቢት 7 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሚመነዘር ቼክ ቁጥር የሆነ ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ /አንድ መቶ ሺህ/ የያዘ ቼክ ሰጥተውኝ ለክፍያ ባንክ ስቀርብ ሂሣቡ ታግዶል በሚል ምክንያት ቼኩ ሳይከፈል ተመልሷል። ስለዚህ በቼኩ የተመለከተውን ገንዘብ ከነወለደ እንዱከፈል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 286 መሰረት በአጭር ሥነ-ሥርዓት ታይቶ እንዱወሰን በማለት ክስ ቀረበ።
አመልካችም ቼኩ የተሰጠው የካቲት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ለተደረገው እስከቫተር ሽያጭ ውል ስምምነት መነሻ ሆኖ ከሽያጩ ገንዘብ ውስጥ 2ዐዐ,ዐዐዐ ብር በዕለቱ ተከፍል ቀሪው 1ዐዐ,ዐዐዐ ብር መጋቢት 12 ቀን 2ዐዐዐ የሚመነዘር ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መስጠታቸውን በማስመልከት ለመከላከል እንዱፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
ግራ ቀኙን ያከራከረው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በሆነው በ12/2/2ዐዐ1 ዓ.ም. በዋለው ችልት ለመከላከል እንዱፈቀድ የቀረበለትን ጥያቄ ባለመቀበል ክስ የቀረበበትን በቼኩ ላይ የተመለከተውን ገንዘብ ከነወለደ እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛ ፍ/ቤትም በመ/ በ26/5/2ዐዐ1 ዓ.ም.
በዋለው ችልች ውሣኔውን አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
ይህ ፍ/ቤትም አመልካች የግል ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በመጥቀስ ለመከላከል እንዱፈቀድለት ጥያቄ አቅርቦ የመታለፈን አግባብነት ለመመርመር ለሰበር እንዱቀርብ ታዞ መጋቢት 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የግራ ቀኙን ክርክር አድምጧል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ በአጭሩ የተመዘገበው ሲሆን እኛም ክርክራቸውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 284 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በአጭር ሁኔታ በሚወሰኑ ክርክሮች ላይ ስለሚፈፀም ሥነ-ሥርዓት በሕጉ የተመለከቱ ሥርዓቶችን መሰረት በማድረግ እንደሚከተለው መርምረናል።
በመሰረቱ በአጭር ሥነ-ሥርዓት ዲኝነት ታይቶ እንዱወሰን ክስ የሚቀርብበት ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 285/1/ እንደተመለከተው ከሕጉ ጋር በተያያዘው ሰንጠረዥ ቁጥር 2 መሰረት ተከሣሽ የሆነው ሰው መጥሪያ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በአሥር ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ክሱን ለመከላከል እንዱፈቀድለት ፍ/ቤቱን ፈቃድ እንዱጠይቅ መደረግ እንዲለበት በሕጉ መሰረት ቼኩ የተሰጠበት ምክንያት የኤክስካቬተር ሽያጭ ውል ምክንያት እንደሆነ በመጥቀስ ለመከላከል እንዱፈቀድለት በቃለ መሐላ የጠየቀ መሆኑን ከክርክሩ መዝገብ መረዲት ተችሎል። የተጠሪ ዋና ክርክር በቼኩ ላይ ሐተታ ወይም ገደብ የለበትም በማለት ነው። አመልካች ደግሞ በሽያጩ ውል ላይ የቼክ ቁጥር ተጠቅሶ ውል የተገባ መሆኑን በመግለጽ የሚከራከር ሲሆን በዚህ ፍ/ቤት የቃል ክርክር ጊዜ ተጠሪም ይህ የውል ግንኙነት በመካከላቸው እንዲላቸው አልካደም። በመከላከያ ፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻ ላይም ይህ ግንኙነት መኖሩ እስከተገለፀ ድረስ ምንም እንኳን ቼክ እንደ ገንዘብ ለተለያዩ ሰዎች በቀላለ ሉተላለፍ የሚችል ባሕርይ ያለው የገንዘብ ሰነድ በመሆኑ ቼክ አከፊፈል ላይ ማንኛውም መቃወሚያ ላቀርብበት እንደማይችል በንግድ ሕጉ የተደነገገ ሲሆን ሕጉ ለይቶ ባስቀመጣቸው ጉዲዮች ካልሆነ በስተቀር የቼክ ክፍያ በማናቸውም ምክንያት ሉቆምና ሉታገድ የማይችል መሆኑ አካከራካሪ አይደለም። ነገር ግን በባለ ጉዲዮቹ መካከል ግልጽ የሆኑ ሁኔታዎች ወይም ግንኙነቶች በተፈጠሩ ጊዜ ብቻ ይህን መቃወሚያ ለማድረግ እንደሚቻል በን/ሕ/ቁ. 717/1/ ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ይህን መሰረት በማድረግ ለመከላከል እንዱፈቀድለት ያቀረበውን ጥያቄ ፍ/ቤቱ ያልተቀበለው የቼክ ክርክር በመሆኑ ብቻ የቼክን ባህርይ መሰረት ለማድረግ ነው። ሆኖም በዚህ የፈቃድ ጥያቄ ደረጃ ላይ የቼክ ባሕርይ ሳይሆን መታየት ያለበት አመልካች ለመከላከል እንዱፈቀድለት ያቀረበው ምክንያት ፈቃድ የሚያሰጥ መሆን አለመሆኑን ነው። ላላ የፍሬ ነገር ክርክር ከፈቃድ በኋላ የሚታይ ነው። ከዚህ አኳያ አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበረውን የሽያጭ ውል ግንኙነት መሰረት በማድረግ ለመከላከል እንዱፈቀድ ፍ/ቤቱን ለመጠየቅ ሕጋዊ ምክንያት አለው። ሆኖም ፍ/ቤቱ በአጭር ሥነ-ሥርዓት እንዱታይ የሚቀርቡ ክሶች አመራር ሥርዓትን ሳይሆን የተከተለው የቼክ ባሕርይን መሰረት በማድረግ ውሣኔ መደምደሚያ ላይ መድረሱ አግባብ ሆኖ አላገኘንም። ምክንያቱም ለመከላከል እንዱፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በፍ/ቤቱ አግኝቶ የተጠየቀውን ገንዘብ ላለመክፈል በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑ የሚታወቀው ፍ/ቤቱ ከአጭር ሥነ-ሥርዓት ወደ መደበኛ የክርክር ሥነሥርዓት ውስጥ በመግባት ግራ ቀኙን በአግባቡ በማስረጃ ካከራከረ በኋላ ነው። በመሆኑም ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 12 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ጥር 26 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ያለውን መከላከያና ማስረጃ አቅርቦ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በመደበኛ የክርክር ሥርዓት አከራክሮና ማስረጃ ሰምቶ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341 መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ። መዝገቡን ዘግተናል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.