No summary available.
ጥር 5 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ እመቤት መኯንን- ጠበቃ ነቃጥበብ በየነ።
ተጠሪ፡- ወረዲ 2ዐ ቀ. 29 አ/ጽ/ቤት ነ/ፈጅ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል ከ/ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪና በሥር ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሣሾች ላይ ባቀረቡት ክስ በወረዲ 2ዐ ቀበላ 29 ክልል የሚገኘውን ቁጥር 449 የሆነውን ቤት ከቀበላው አስተዲደር አንደኛ ተከሣሽ ላይ ተከራይቼ በቤቱ የሆቴል የንግድ ድርጅት በማቋቋም ስጠቀምበት የነበረ ሲሆን ይህንኑ የንግድ ድርጅት ለማስፊፊት ከቤቱ ፉት ለፉት በነበረው 67 ካሬ ሜትር ባድ ቦታ ላይ ግንባታ ፈጽሜ የድርጅቱ አካል አድርጋ ለመጠቀም ለቀበላው ጥያቄ አቅርቤ ተፈቅድልኝ ብር 3ዐዐ,000(ሦስት መቶ ሺህ) ወጭ አድርጌ ገንብቻለሁ።
ከዚህ በኋላም ለሁለተኛ ተከሣሽ /ለአሁን ተጠሪ/ እና ለሦስተኛ ተከሣሽ አውራሽ ወ/ሮ የሻሐረግ ገዲሙ የሆቴል ንግድ ድርጅቱን ከሙለ የሆቴል ቤት መገልገያዎች ጋር በ3/1ዐ/87 ዓ/ም በተደረገ ውል ያከራየሁ ሲሆን ነገር ግን የውለ ማለቂያ ቀን በሆነው በ2/1ዐ/89 ዓ/ም ተከራይ ወ/ሮ የሻረግ ገዲሙ ለከሣሽ መመለስ ሲገባት ከአንደኛ ተከሣሽ ጋር በመተባበር ከሐምል ወር 1998 ዓ/ም ጀምሮ ድርጅቱን ቀበላው ወርሶታል ከዚህ በኋላ የድርጅቱ ሕጋዊ ተከራይ ወ/ሮ የሻረግ ገዲሙ ነች በማለት ለማስረከብ ፈቃደኛ ያልሆኑ ስለሆነ ይህንኑ ድርጅት ሶስቱም ተከሣሾች በአንድነትና በነጠላ ለከሣሽ እንዱያስረክቡ ከሣሽ ማግኘት የሚገባኝን የተቋረጠ ኪራይ በድምሩ ብር 342,000 (ሦስት መቶ አርባ ሁለት ሺህ) በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ።
የድርጅቱን ግንባታ ለማከናወን ወጭ ያደረግሁትንም ብር 3ዐዐ,000(ሦስት መቶ ሺህ) በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ እንደዚሁም የወ/ሮ የሻረግ ገዲሙ ወራሾች የሆኑት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሣሾች በኪራይ ውለ ላይ የተመለከተውን ብር 4000(አራት ሺህ) የገደብ መቀጫ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተከሣሾችም በየበኩላቸው የመከላከያ መልስ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ የክርክር ነጥባቸውም በከሣሽና በቀበላው አስተዲደር መካከል ተደርጎ የነበረው የኪራይ ውል መንግስት ባወጣው የተከራይ አከራይ መመሪያ መሰረት ተቋርጦ በአንደኛ ተከሣሽና በወ/ሮ የሻረግ ገዲሙ መካከል የኪራይ ውል የተደረገ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፋዳራል ከ/ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ ለክሱ መነሻ የሆነውን የንግድ ቤት አንደኛ ተከሣሽ የቀበላው አስተዲደር ለከሣሽ ማከራየቱን ያልካደ ሲሆን ውለን ለማቋረጥ ያቀረበው ምክንያት ከሣሽ የቤቱን ኪራይ በወቅቱ ስትከፍል ያልነበረች ከመሆኑም በላይ ለላላ ሰውም አሳልፊ አከራይታለች በማለት ሲሆን ነገር ግን ይህ ሁኔታ ውለን በአንድ ወገን በእራሱ ሥልጣን ለማቋረጥ እንደሚያስችለው ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ ስለላለ በመካከላቸው የነበረው ውል የተቋረጠው ከሕግ ውጭ ነው ካለ በኋላ በከሣሽና በሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሣሾች አውራሽ በወ/ሮ የሻረግ ገዲሙ መካከል የተደረገው ውል ጊዜው ያላለቀ ስለሆነ ይህንኑ የንግድ ድርጅት ሦስቱም ተከሣሾች ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ለከሣሽ ሉያስረክቡ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የኪራይ ክፍያ ጥያቄውን በተመለከተም ከሳሽ ከድርጅቱ ኪራይ ያጣቸው ብር 54,000(ሃምሣ አራት ሺህ) ስለሆነ ይህንኑ ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ተከሣሾች ለከሣሽ እንዱከፍለ የንግድ ቤቱን ለማስፊፊት ለግንባታ ወጭ ሆኗል የተባለውና ከሣሽ እንዱተካላቸው የጠየቁት የብር 3ዐዐ,000(ሦስት መቶ ሺህ) ክፍያ በተመለከተ በንግድ ቤቱ ላይ ከተከራይነት ያለፈ መብት እንዲላት ከሣሽ ያላስረዲች ስለሆነ የክፍያ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም ብሎል። የሥር አንደኛ ተከሣሽ በዚህ ውሣኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም ይግባኙን መርምሮ መ/ሰጪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሮ መልስ ሰጭ ልከራየው የምትለው ቤት ንብረትነቱ የቀበላው አስተዲደር /የይግባኝ ባይ/ ሲሆን ንብረቱ በመሆኑም ከመልስ ሰጭዋ ጋር የነበረውን የኪራይ ውል በመተው ለላላ ሰው አከራይቶታል። በእርግጥ ቤቱ የንግድ ሥራ የሚሰራበት በመሆኑ መልስ ሰጭ የይግባኝ ባይን ፈቃድ ሣትጠይቅ በኪራይ ለላላ ሰው ማስተላለፍ እንደምትችል በንግድ ሕግ ቁጠር 145/1/ ላይ ተደንግጓል። ነገር ግን ይህ ድንጋጌ የቤቱ ባለሀብት የሆነውን ይግባኝ ባይን ከመልስ ሰጭ ጋር አድርጏት የነበረውን የኪራይ ውል እንዲያቋርጥ የሚያግደው ነው በሚል የሚተረጏም እንዲልሆነ ተገንዝበናል። ይግባኝ ባይ ከፈቃደ ውጭ ከማይፈልገው ሰው ጋር የኪራይ ውል አድርግ የሚባልበት የሕግ ምክንያት የለም። በመሆኑም ይግባኝ ባይ ቤቱን ለመልስ ሰጭ አስረክብ ኪራይም ክፈል መባለ ትክክል አይደለም በማለት የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔውን ሽሯል።
No topics extracted.
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ ተጠሪ ከማይፈልገው ሰው ጋር የኪራይ ውል አድርግ የሚባልበት ምክንያት የለም ተብል በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ አግባብነቱ ከንግድ ሕግ ቁጥር 145 አንፃር ሉመረመር እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን በቃል አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ተጠሪ በወረዲ 2ዐ ቀበላ 29 ክልል የሚገኘውን ቁጥር 449 የሆነውን ቤት ለአመልካች እንዲከራየና አመልካችም በቤቱ የሆቴል ንግድ ድርጅት በማቋቋም ሲሰሩ እንደነበር ከተጠሪ ባገኙት ፈቃድ መሰረትም የሆቴል ድርጅቱን አስፊፍተው እንዱሰሩና በኋላም ይህንኑ የሆቴል ድርጅት ለሥር ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሣሾች አውራሽ ለወ/ሮ የሻሐረግ ገዲሙ በ3/1ዐ/87 ዓ/ም በተደረገ የንግድ መደብር ኪራይ ውል እንዲከራዩ ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል።
በልላ በኩልም ተጠሪ ከአመልካች ጋር አድርጏት የነበረውን የኪራይ ውል ለማቋረጥ በምክንያትነት የጠቀሰው አመልካች የቤቱን ኪራይ በወቅቱ አትከፍልም ነበር። ቤቱንም ለላላ ሰው አሳልፊ አከራይታለች በማለት ሲሆን የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በዚህ መልኩ የቀረበውን የተጠሪን ክርክር ሳይቀበለው የቀረው ይህ ድርጊት በከሣሽ /በአሁን አመልካች/ ተፈጽሟል ቢባል በዚህ ድርጊት መነሻነት ውለን በአንድ ወገን በእራሱ ሥልጣን ለማቋረጥ ከውለ ወይም ከሕግ የመነጨ መብት ያለው ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ ካለመኖሩም በላይ ከሣሽ ውለን የጣሰ ድርጊት ፈጽማለች ቢባል እንኳን ተከሣሽ በሕጉ አግባብ መብቱን ማስከበር ከሚችል በስተቀር በእራሱ ሥልጣን ውለን ለማቋረጥ በሕግ የተሰጠው መብት የለም በማለት ሲሆን፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደግሞ ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረውን ውል በማቋረጥ ከላላ ሰው ጋር የተዋዋለ ስለሆነና ሁለተኛውን ውል አቋርጦ ከአመልካች ጋር እንዱዋዋል ሉገደድ የማይችል ከመሆኑም በላይ ቤቱ የንግድ ሥራ የሚሰራበት በመሆኑ አመልካች የተጠሪን ፈቃድ ሣታገኝ በኪራይ ለላላ ሰው ማስተላለፍ እንደምትችል በንግድ ሕግ ቁጥር 145/1/ ላይ የተደነገገ ቢሆንም ይህ ድንጋጌ የቤቱ ባለቤት የሆነውን ተጠሪን ከአመልካች ጋር አድርጏት የነበረውን የኪራይ ውል እንዲያቋርጥ የሚያግደው ባለመሆኑ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች እንዱያስረክብና ኪራይም ክፈል መባለ ተገቢነት የለውም በሚል ነው።
በበኩላችንም ጉዲዩን አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ መርምረነዋል። እንደመረመርነውም ምላሽ ማግኘት የሚገባው የጉዲዩ ጭብጥ አመልካች ከተጠሪ የተከራዩትን የንግድ ቤት አሳልፈው ለሦስተኛ ወገን በማከራየታቸው ተጠሪ ውለን በማቋረጥ ከውል ወይንም ከሕግ የመነጨ መብት አለው ወይንስ የለውም? የሚለው በመሆኑ ከዚህ ጭብጥ አኳያ የሰበር አቤቱታው ተመርምሯል።
በዚህም መሰረት ለጉዲዩ አግባብነት ካለው የንግድ ሕግ ቁጥር 145/1/ ላይ የንግድ መደብርን የተከራየ ወገን ይህንኑ የንግድ መደብር 3ኛ ወገንን የተከራይ ተከራይ አድርጏ ማስተላለፍ እንደሚችል ይህንንም ሲያደርግ የንግድ መደብሩን ባለቤት ፈቃድ እንደማያስፈልገውና የንግድ መደብሩን ለ3ኛ ወገን አሳልፍ ለማከራየት የባለቤቱ ፈቃድ ያስፈልጋል የሚል የውል ቃል ቢኖርም እንኳን የዚህ አይነት የውል ቃል/term/ፈራሽና? ዋጋ እንደላለው እንደዚሁም የማይንቀሣቀስ ንብረትን ለ3ኛ ወገን አሳልፍ ለማከራየት የባለቤቱ ፈቃድ አስፈላጊ እንደሆነ በውል ሉወሰን ይችላል ተብል በፍ/ብ/ሕ/ቁ/2959 ላይ የተደነገገው ለንግድ መደብር ኪራይ ተፈጻሚነት እንደላለው ተደንግጏ እናገኛለን።
ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለውም የንግድ መደብር የተከራየ ሰው የንግድ መደብሩን ለላላ 3ኛ ወገን አሳልፍ ላለማከራየት ከንግድ መደብሩ ባለቤት ጋር የውል ግዳታ ቢገባም እንኳን የዚህ ዓይነቱ ስምምነት ውጤት እንደላለው ስለሚቆጠር አሳልፍ ማከራየት እንደሚችልና የንግድ መደብሩ ባለቤት ይህ ተግባር በመፈጸሙ ምክንያት ውለን ማቋረጥ እንደማይችል ሲሆን ነገር ግን የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይህ ድንጋጌ የቤቱ ባለቤት የሆነውን ወገን ውለን ከማቋረጥ አያግደውም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ ለድንጋጌው የተሳሳተ ትርጏም በመስጠት እንደሆነ ተገንዝበናል።
ሲጠቃለልም ተጠሪ ከአመልካች ጋር ለክርክሩ ምክንያት በሆነው የንግድ ቤት ላይ አድርጏት የነበረውን የኪራይ ውል ለማቋረጥ ከውልም ሆነ ከሕግ የመነጨ መብት እንደላለው መገነዝብ የሚቻል በመሆኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪና የሥር ተከሣሾች የንግድ ቤቱን ለአመልካች እንዱያስረክቡ አመልካችም ከንግድ ድርጅቱ ያጡትን ኪራይም እንዱከፍለ በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢነት ያለው ሆኖ ሳለ ነገር ግን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ከላይ በተመለከተው አኳኋን ይህንኑ ውሣኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 27ዐ48 ሚያዝያ 19 ቀን 1999 ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 15978 ሰኔ 27 ቀን 1998 ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ ፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።