No summary available.
የሰ/ ህዲር 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ፡- ወ/ሮ መስታወት በላቸው - ቀረቡ ተጠሪ፡- ፡- አቶ ለገሰ ሣህለ - ጠ/መከተ ዲኜ ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። የግራ ቀኙ ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የንብረት ክፍፍለ ጉዲይ በቤተ ዘመድ ሽምግልና ጉባኤ ሲታይ ቆይቶ ጉባኤው በዐ6/21/1998 ውሣኔ ሰጥቷል።
ይህንኑ ውሣኔ እንዱያጸድቅላቸው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ሲያመለክቱ አመልካች ግን ጉባኤው ክርክሩን በአግባቡ ለመምራት መሰረታዊ የህግ ግንዛቤ የላለው በመሆኑ የተሰጠውም ከፉል ውሣኔ ከጉባኤው ስልጣን ውጪ በመሆኑና የህግ ስህተቶችም ስላለበት ጉዲዩን ፍ/ቤቱ ተረክቦ ውሣኔ ይስጥበት በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ግን የአመልካችን መቃወሚያና ክርክር ወድቅ አድርጎ ውሣኔውን በማጽናት የጋራ ናቸው ተብለው ውሣኔ የተሰጠባቸው ንብረቶችን ከተስማሙ በአይነት እንዱካፈለ ካልተቻለ አንደኛው ለላለኛው ልዩነቱን እንዱከፍል በማድረግ እንዱካፈለ በዚህ ካልተስማሙ ንብረቶቹ በሐራጅ ተሸጠው ገንዘቡን እንዱካፈለ ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካች በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው አመልካች ለተጠሪ ብድር ብር 7ዐዐ,ዐዐዐ (ሰባት መቶ ሺህ)ስለከፈልኩ ግማሹን ተጠሪ ይክፈለ በማለት አቅርበውት የነበረውን የዲኝነት ጥያቄ ጉባኤው ሣይቀበል እንዱሁም አመልካች ለተጠሪ የዚህን ገንዘብ ግማሽ እንዱከፍለ በማለት የሰጠውን ውሣኔ ብቻ በመሻር የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ አፅንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ የረር ሃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የራሱ የህግ ሰውነት ያለው በስሙ መከሰስና መክሰስ የሚችል ድርጅት መሆኑ እየታወቀ እንዱካፈለት መወሰኑ ለተጠሪ የግል ዕዲ ከጋራ ገንዘብ የተከፈለ ገንዘብ ለመሆኑ ምስክር ሣይሰማ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ እንዱሁም ላልች የቤት ቁሣቁሶች በተመለከተ ማስረጃ ሣይሰማ መወሰኑ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው። ይህ ችልታም የአመልካች አቤቱታ በሰበር ችልት ሉጣራ የሚገባው መሆኑን በማመን ተጠሪ ቀርበው እንዱከራከሩ አድርጓል።
ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ስህተት ተፈጽሞበታል ከተባለው ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝቦ መርምሯል።
በዚህ መሰረት ራሱን ችል የህግ ሰውነት ያለው ድርጅት በቤተ ዘመድ ሽምግልና ጉባኤ እንዱከፊፈል መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን እንዱሁም ማስረጃ ሣይሰማ ውሣኔ ተሰጥቶበታል የተባለው የንብረት ክፍፍል አግባብ መሆን አለመሆኑን ችልቱ መርምሯል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ የረር ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በንግድ ህጉ መሰረት የተቋቋመ እና የህግ ሰውነት ያለው መሆኑ ግራ ቀኙ አልተካካደበትም። የንግድ ማህበሮች የሚቋቋሙበት እና የሚፈርሱበት ሁኔታ ደግሞ በንግድ ህጉ ውስጥ ተመልክቷል። በዚህም መሰረት የተወሰነ ኃላፉነት ያለው የግል ማህበር ሉፈርስ የሚችልበት ምክንያቶች በንግድ ህግ ቁጥር 542 ሥር ተዘርዝረዋል። በዚህ የንግድ ህጉ ድንጋጌ ሥር የተመለከቱት ምክንያቶች ሲኖሩ ማህበሩ በፍ/ቤት አማካኝነት ይፈርሣል። ከዚህ ውጪ የንግድ ማህበሩ አባላት የህጉን ሥርዓት ሣይከተለ በራሣቸው ወይም በልላ አካል አማካኝነት ሉፈርስ የሚችልበት የህግ መሰረት የለም። በፍ/ቤት አማካኝነት ከፈረሰና ሂሣቡ ተጣርቶ የመጨረሻው ውጤት በሂሣብ አጣሪዎች ከታወቀ በኋላ ማህበሩ ከንግድ መዝገብ ተሰርዞ በህግ የተሰጠው መብቱ ቀሪ የሚሆንበትን ሥርዓት የንግድ ህጉ አስቀምጧል ሃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የህግ ሰውነት ያለውና በራሱ ስም ህጋዊ ተግባራትን ሉፈፅም የሚችል ሉከስና ሉከሰስ የሚችል በመሆኑ የሰራቸው ህጋዊ ተግባራትም የተለያዩ ውጤቶች የሚያስከትለ በመሆኑም ህጉ በተለየ ሁኔታ እንዱስተናገደ አድርጓል። በመሆኑም ምንም እንኳን የማህበሩ ብቸኛ የአክስዩን ባለድርሻ ባልና ሚስቱ ቢሆኑ እንኳን እንደላላ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ማህበሩን በዓይነት የሚካፈለት ወይም በሃራጅ ተሸጦ ገንዘቡን ሉከፊፈለ የሚችለበት የህግ መሰረት የለም። ስለሆነም የሽምግልና ጉባኤው እንደላላ ንብረት ማህበሩን እንዱከፊፈለ የሰጠው ውሣኔ የንግድ ህጉን ያላገናዘበ ነው።
የቀረውን ነጥብ በተመለከተ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች የመኖሪያና የጀምናዝየም ዕቃዎች ከቤቶቹ ጋር አብረው የተሸጡ መሆኑ በአግባቡ ሣይጣራ ተወስኖብኛል ያለ ሲሆንም ከሽምግልና ጉባኤው ውሣኔ ቤቶቹ መሸጣቸውን የሚያረጋግጠው የፁሁፍ ማስረጃ ከቤቶቹ ጋር የቤትና የጅምናዝየም ዕቃዎች አብረው መሸጣቸውን የማያመለክት በመሆኑ በቂ ማስረጃም ያልቀረበበት መሆኑን በማረጋገጥ ውሣኔ መስጠቱን ተመልክተናል።
No topics extracted.
በልላ በኩል ግን አመልካች እነዚህ የቤት እቃዎችና የጅምናዝየም ዕቃዎች ቤቱን የገዙት ግለሰብ ከቤቱ ጋር አብረው የገዟቸው ስለመሆናቸው ቀርበው እንዱመሰክሩላቸው በማስረጃነት የቆጠሯቸው መሆኑን ከሽምግልና ጉባኤ ውሣኔ ላይ ተገንዝበናል። እነዚህ ንብረቶች የሚንቀሣቀሱ ንብረቶች በመሆናቸው የንብረቶቹ ሽያጭ የግድ በፁሁፍ መደረግ ያለበት መሆኑ ወይም ንብረቶቹ ለመሸጣቸው ሉረጋገጥ የሚገባው በፁሁፍ /በሰነድ ማስረጃ/ ብቻ ለመሆኑ በህግ ተለይቶ የተመለከተ ነገር የለም። በህግ በተለይ ሁኔታ እንዱረጋገጥ ካልተመለከተ በቀር አንድን ጉዲይ በማንኛውም አይነት ማስረጃ ማረጋገጥ እንደሚቻል ከፍ/ብ/ህ/ቁ.2ዐዐ2 እና 1677(1) መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም አመልካች የቤትና የጅምናዝየም እቃዎቹ ስለመሸጣቸው በሰው ምስክር ለማስረዲት እየጠየቁ ጉባኤው በቤት ሽያጭ ውለ ላይ እነዚህ ንብረቶች ስለመሸጣቸው አልተገለፀም በማለት ክርክርራቸውን ውድቅ ማድረጉ የአመልካችን የመከላከል መሰረታዊ መብት የማያጣብብ ሆኖ አግኝተዋል።
ው ሣ ኔ
የረር ሃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና የቤትና የጅምናዝየም ዕቃዎችን በተመለከተ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ሚያዝያ 22/1999 ዓ.ም. በመ/ የሰጠው ትዕዛዝ እንዱሁም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ህዲር 12/2ዐዐዐ ዓ.ም. በመ/ የሰጠው ውሣኔ ተሽረዋል።
የረር ኃ/የተ/የግ/ማ በንግድ ህጉ በተመለከተው መሰረት የሚፈርስና ሂሣቡ የሚጣራ ካልሆነ በቀር እንደላላቹ የባልና ማስት የጋራ ንብረቶች ተገቢዎቹ በዓይነት የሚካፈለት ወይም ተሸጦ ገንዘቡን የሚካፈለት ንብረት አይደለም ብለናል።
የቤትና የጅምናዝየም ዕቃዎችን በተመለከተ አመልካች በማስረጃነት የቆጠሯቸው ምስክር ቀርበው ከተሰሙ በኋላ ተገቢው ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 343 (1) መሰረት ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ተመልሷል።
ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ወጪና ኪሣራ ይቻለ መዝገቡ ተዘግቷል። ለመ/ቤት ይመለስ።