No summary available.
ኀዲር 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ እጅጋየሁ ታደሰ - ቀረበች ተጠሪ፡- መገርሳ ጉደታ - ከጠበቃ ሻለቃ ሃይለ ቦረና ጋር ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የሽርክና ውልን መሰረት ያደረገ የንብረት እና የገንዘብ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረችው የአሁንዋ አመልካች ናት።
በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተችውም በሞት የተለየው ባልዋ እና ተጠሪ በጋራ አቋቁመው ሲሰሩበት ከነበረው ጋራዥ ከተገኘው ገቢ ድርሻዋን እንዱከፍላት ወይም የጋራዡን ግማሽ እንዱሰጣት በመጠየቅ ነው ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ ጋራዡ የግለ እንደሆነ፣ከአመልካች ባል ጋር አድርገውት የነበረው ውል የሽርክና ሳይሆን የደባልነት እንደሆነ በመግለጽ ተከራክሮአል። ክሱን የሰማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተጠሪ እና በአመልካች ባል መካከል የተደረገ የሽርክና ውል የለም በማለት ወስኖ የነበረ ቢሆንም፤ጉዲዩን በይግባኝ የሰማው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሽርክና ውል መኖሩን በማረጋገጥና በመወሰኑ በጉዲዩ ስረ- ነገር ላይ ክርክሩ ቀጥልአል። በመጨረሻም የእሽሙር ሽርክና ውል ተደርጏ ነበር ቢባልም፤በአመልካች ባል ሞት ምክንያት ፈርሶአል። የሽርክና ውለ ተዋዋዮቹ ይዘውት የመጡትን ንብረት እንጂ ጋራዡን አይመለከትም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ፍ/ቤቱ አመልካች ያቀረበችውን የገቢና የጋራዥ ድርሻ ክፍያ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበበት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም ብለዋል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መስከረም 30 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የሽርክና ውል አለ እየተባለ የአመልካች የገንዘብ ክፍያ እና የንብረት ጥያቄ ውድቅ የተደረገው በሕግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በተጠሪ እና በአመልካች ባል መካከል የእሽሙር የሽርክና ውል እንደነበር በፍ/ቤት ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ ይህን በተመለከተ በአሁኑ ደረጃ የሚባል ነገር የለም። በዚህ ደረጃ ሉወሰን የሚገባው ነጥብ የዚህ ውጤት ምንድነው የሚለው ነው። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በውሳኔው እንደገለፀው ተዋዋዮቹ ውለን ሲያደርጉ በየግላቸው የነበሩዋቸውን መሣሪያዎች ይዘው መግባታቸውን በውለ ላይ በግልጽ በማስፈር ነው። ከዚህ ባለፈም የጋራዡን ንግድ ሥራ በጋራ ለማቋቋም ውል አላደረጉም። በየግላቸው የነበሩዋቸውን መሣሪዎች በመያዝ ሥራ የሚሰሩበት ጋራዥ በተጠሪ ይዞታ ስር እንደሆነና የሚታወሰውም በሱ ስም ብቻ እንደሆነም አላከራከረም። በንግድ ሕግ ቁ.271 እንደተመለከተው የእሽሙር ማህበር ማህበርተኞቹ እንደፈቃዲቸው የውላቸውን ሁኔታዎች ወስነው የሚያቋቁሙት እንደመሆኑ በተያዘው ጉዲይም ተዋዋዮቹ በሚያመቻቸው መንገድ ወስነው እንዲቋቋሙት መገንዘብ ይቻላል። በንግድ ሕግ ቁጥር 273 እንደተደነገገው ደግሞ ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በቀር እያንዲንደ ማህበርተኛ ገቢ ላደረገው መዋጮ ባለሃብትነቱን እንደያዘ ነው የሚቆየው። ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር እንደሚታየው ውለ ከተደረገ በኋላ በጋራ የተገዛ ንብረት ወይም የተደረገ መዋጮ የለም። ይልቁንም የጋራዥ ንግደ በተጠሪ ስም ብቻ እንደተመዘገበ ነው የቀጠለው። የንግድ ፈቃደም በተጠሪ ስም ነው። በመሆኑም የአመልካች ባለቤት የጋራዡም የጋራ ባለሃብት ነው የሚባልበት የሕግ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል አመልካች በጋራዡ ላይ የጋራ ባለሐብትነት መብት እንዲለ በመቁጠር ያቀረበችው ክርክር በስር ፍ/ቤቶች ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው።
ቀጥለን የተመለከትነው ላላው ነጥብ ሟች እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ያለውን የትርፍ ክፍያ እና የሽርክና ውለ በተደረገበት ጊዜ ይዘዋቸው መጣ የተባለትን መሣሪያዎች በሚመለከት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን የውሳኔውን ክፍል ነው። አመልካች ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረበችው አቤቱታ ጭምር እነዚህን ነጥቦች በማንሳት ተከራክራለች። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ እንደተመለከተው አመልካች በትርፈም ሆነ በመሣሪያዎቹ ላይ መብት እንዲላት ግንዛቤ ተወሰድአል። ከዚህ ባለፈ ግን በጠየቀችው ዲኝነት መሰረት ይህ ይገባሻል ወይም አይገባሽም የሚል ውሳኔ አልተሰጠም። ስለዚህም በዚህ ረገድ ሉታረም የሚገባው ስህተት እንዲለ ለመገንዘብ ችለናል። ስህተቱ ይስተካከልም ዘንድ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.
አቤቱታ የቀረበበት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 05140 ሰኔ 26 ቀን 1998 ዓ.ም ተሰጥቶ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 48762 ሐምል 26 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽልአል።
አመልካች ከባለቤትዋ ሞት በኋላ ያለውን ትርፍ እንድትካፈል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
ጋራዡን ግማሽ ልካፈል በማለት ያቀረበችውም እንደዚሁ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
የሽርክና ውለ በሟች ምክንያት እስከፈረሰበት ቀን ድረስ ለነበረው ጊዜ የተገኘ ትርፍ ካለ አመልካች የመካፈል መብት አላት። ሟች ለሽርክና ማህበሩ በመዋጮነት ገቢ ያደረጋቸው መሣሪያዎች ካለም ሉመለሱላት ይገባል። ተጠሪ በእነዚህ መሣሪያዎች በመጠቀም ያገኘው ገቢ ካለም እንደዚሁ ተጣርቶ ለአመልካች ሉከፈል ይገባል። ስለዚህ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩ በተከፈተው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ በእነዚህ ሦስት ነጥቦች ግራ ቀኝ ወገኖችን ካከራከረ በኋላ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ይመለስ።