No summary available.
ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ መሰረት ኃይለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዘውደ ቢረዲ - ከጠበቃቸው አቶ ፍቅሩ ታደሰ ጋር ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 3ዐ4ዐ4 ሐምል 19 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ህዲር 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በመጠየቁ ነው። የክርክሩ መነሻ ባልና ሚስት የነበሩት አመልካችና ተጠሪ በፍቺ ጋብቻቸው መፍረሱን ተከትል የቀረበው የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ነው። አመልካች በመርካቶ የገበያ አዲራሽ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ በተሰጣቸው ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ /መቶ ሺ ብር/ የሚገመት የተዘጋጁ የሴት ልብሶችና ጫማ የያዙ የሱቅ የንግድ ድርጅቶች የጋራ ንብረት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እንዱያካፍላት የጠየቀች ሲሆን ከላይ ከተገለፁት የሱቅ የንግድ ድርጅቶች በተጨማሪ ላልች ንብረቶችም እንዱያካፍላት ጠይቃለች።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በሱቅ የንግድ ድርጅቶቹ ውስጥ ያለው ሸቀጥ ለብቻው ተቆጥሮ አመልካችና ተጠሪ እንዱካፈለ የወሰነ ሲሆን በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለው የንግድ ድርጅትን በተመለከተ ቤቶቹ የኪቤአድ ንብረት በመሆናቸው በጋራ ንብረትነት የሚካፈለበት ምክንያት የለም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ምክንያት የለም በማለት ይግባኙን ሰርዞታል። አመልካች የሥር ፍርድ ቤቶች በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለውን የንግድ ድርጅት በጋራ ንብረትነት ለመካፈል ያቀረቡትን ጥያቄ ባግባቡ አልመዘነም፤ የሥር ፍ/ቤት የሰጠውም ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው፤ የሥር ፍርድ ቤት በማስረጃ አስደግፋ ያቀረብኩትን ላልች የጋራ ንብረት ክፍያዎች አላግባብ ያለፈብኝ ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ለሰበር ባቀረቡት አቤቱታ ጠይቀዋል።
ይኸ የሰበር ችልትም የሥር ፍርድ ቤት በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ የሚንቀሣቀሰው የንግድ ድርጅት የሚከናወንባቸው ክፍልች የኪራይ ቤቶች አስተዲደር ድርጅት ንብረት በመሆናቸው በጋራ ንብረትነት ለማካፈል አይቻልም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ተገቢነት ለማጣራት ብቻ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ለተጠሪ እንዱደርሰው አድርጓል። ተጠሪ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለው የንግድ ድርጅትና የመከራየት መብት ከጋብቻ በፉትም ሆነ በኋላ የእኔ የግል ንብረት በመሆኑ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ምንም አይነት የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። አመልካች በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ይከናወን የነበረው የንግድ ድርጅት በእሣት ቃጠል ምክንያት ከወደመ በኋላ እንደገና በጋራ ሀብታችን የተቋቋመና የተደራጀ ስለመሆኑ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ክድ ያልተከራከረ በመሆኑ በሰበር ደረጃ ይህንን ነጥብ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም የሚል የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና የሰበር ችልት በጭብጥነት የያዘው ነጥብ፣ አመልካችና መልስ ሰጭ በሰበር ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው በመጀመሪያ ደረጃ አመልካች የጋራ ንብረት ስለሆነ ድርሻዬ ተከፍል ሉሰጠኝ ይገባል በማለት የጠየቁት ንብረትነታቸው የመንግሥት የሆኑ የንግድ ማከናወኛ ክፍልችን አይደለም። አመልካች ለመካፈል የጠየቁት በመርካቶ የገበያ አዲራሽ ውስጥ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ የሆነውን የጫማና የተዘጋጁ የሴት ልብሶች መሸጫ የንግድ ድርጅት ግምታቸው 1ዐዐ,ዐዐዐ /አንድ መቶ ሺ ብር/ የሆነ ሸቀጦችን እንደያዘ እንደሆነ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሣኔው በግልጽ አስፍሮታል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው አመልካች በጋራ ንብረትነት ለመካፈል ጥያቄ ያቀረቡት በሱቅ የንግድ ድርጅት ውስጥ የሚገኙ ሸቀጦችን ለብቻ ንግድ የሚከናወንባቸውን ክፍልች ደግሞ ለብቻ በመነጣጠል ፍርድ ቤቱ እንዱያካፍላቸው አይደለም።
አመልካች በጋራ ንብረትነት ፍርድ ቤቱ እንዱያካፍላቸው የጠየቁት በመርካቶ የገበያ አዲራሽ በቁጥር 2ዐ9 ያለውን የንግድ ድርጅትና በቁጥር 21ዐ ያለውን የንግድ ድርጅት የንግድ ሕግ ቁጥር 124 በሚደነግገው መሰረት በንግድ ድርጅትነቱ ከውስጡ ካለ ሸቀጦች ጋር በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይህንን በማለፍ አመልካች ሸቀጦቹ ለብቻ ቆጠራ ተደርጎ እንዱካፈለ የንግድ ሥራ የሚከናወንባቸው ክፍልች ግን የጋራ ንብረት ሣይሆኑ ንብረትነታቸው የመንግሥት ስለሆነ ጥያቄሽ ተገቢነት የለውም በማለት መወሰኑ አግባብነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
የሥር ፍርድ ቤት በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለው የንግድ ድርጅቶች በንግድ ድርጅትነታቸው ሣይሆን ነጣጥል በማየት ውሣኔ ሰጥቷል። ከንግድ ሕግ ቁጥር 127 ድንጋጌዎች ለመረዲት እንደሚቻለው የአንድ የንግድ ድርጅት መሰረታዊ አካል የንግድ ድርጅቱ መልካም ዝና ስምና በደንበኞቹ የተለመደ መሆኑ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ላልች ነገሮችን አካትቶ የሚይዝ ነው። ከዚህ ውስጥ ንግደ የሚከናወንበትን ክፍል የመከራየት መብት የንግድ ድርጅት አንደኛው ክፍል እንደሆነ በንግድ ሕግ ቁጥር 127 ንዐስ አንቀጽ 2/ሐ/ በግልጽ ተደንግጓል። ስለሆነም አመልካች በዚህ የሕግ ድንጋጌ መሰረት በመርካቶ የገበያ አዲራሽ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ በጋራ ንብረትነት አመልካችና ተጠሪ ያላቸውን የንግድ ድርጅት የንግድ ሥራው የሚከናወንበትን ክፍል የመከራየት መብት ጭምር ፍርድ ቤቱ እንዱያካፍላትና እንዱወስንላት ያቀረበችውን ሕጋዊ ጥያቄ የንግድ ሥራ የሚከናወንባቸው ክፍልች የመንግሥት ንብረቶች ናቸው በሚል ምክንያት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የሥር ፍርድ ቤት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በመርካቶ የገበያ አዲራሽ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለት የሱቅ የንግድ ሥራ ድርጅቶች የተጠሪ የግል ንብረት ናቸው በማለት ሣይሆን የንግድ ሥራው የሚከናወንበት ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅት ንብረት በመሆኑ በጋራ ንብረትነት ለማካፈል አይችልም በማለት በመሆኑ ተጠሪ የሱቅ የንግድ ድርጅቱ የግል ንብረቴ ነው በማለት በሰበር ደረጃ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑም አመልካች በጋራ ንብረትነት ለመካፈል የጠየቀችው በመርካቶ የገበያ አዲራሽ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለትን የሱቅ የንግድ ድርጅቶች በንግድ ድርጅትነታቸው ባለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 124 እና 127 ድንጋጌ መሰረት ሆኖ እያለ ፍርድ ቤቱ እነዚህን የሕግ ድንጋጌዎች እና የንግድ ሕግ ቁጥር 145 ንዐስ አንቀጽ 1ን ሣያገናዝብ፣ አመልካች የላላ ሰው ንብረት የሆነ የንግድ ማከናወኛ ቤት ለመካፈል መጠየቅ አትችልም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ 1/ በመርካቶ ገበያ አዲራሽ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለት የሱቅ ንግድ ድርጅቶች አመልካች ለመካፈል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ይህንን ነጥብ በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ስህተት የለበትም በማለት የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል። ይፃፍ።
2/ አመልካች በመርካቶ የገበያ አዲራሽ በቁጥር 2ዐ9 እና 21ዐ ያለት የሱቅ የንግድ ድርጅቶች የንግድ ሥራ የሚከናወንበትን ክፍል ከመከራየት መብት ጭምር በጋራ ንብረትነት የመካፈል፣ መብት አላት ብለናል።
በዚሁ መሰረት እንዱፈፀም የውሣኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።
3/ በሰበር ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሣቸው ይቻለ።
ይኸ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.