No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኒያላ ኢንሹራንስ አ/ማ - ጠበቃ አቶ በረከት በርሄ ቀረበዋል ተጠሪ፡- አቶ ሐጏስ ገ/ድህን - ጠበቃ አቶ ገ/ሄር ተስፊይ ቀርበዋል ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከመረመር በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ጉዲይ ላቀርብ የቻለው አመልካች ታህሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው አቤቱታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 41455 መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ግድፈት የተፈጸመበት ነው በማለት እንዱሻርለት ስለጠየቀ ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች በስር ከሳሽነት፣የአሁኑ ተጠሪ እና ላልች በዚህ ሰበር ችልት ተከራካሪ ያልሆኑ ሁለት ሰዎች ተከሳሾች በመሆን የተከራከሩ ሲሆን የስር ከሳሹ (የአሁኑ አመልካች) መስከረም 14 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ ያቀረበው ክስ አጭር ይዘቱ ደንበኛዬ ከጣሉያን ሃገር ገዝቶ ለሚያስገባቸው የጫማ ሶል መስሪያ ኬሚካልች በጉዞ ላይ እንዲለ ለሚደርስባቸው ጉዲት የመድን ሽፊን የሰጠሁ ሲሆን እነዚህ የመድን ሸፊን የሰጠኋቸውን ንብረቶች ከጅቡቲ ወደብ ወደ አዱስ አበባ ከተማ ለማጓጓዝ የተባበሩት የጭንት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር(አንደኛ ተከሳሽ) ግዳታ በመግባት ተረክቦ በአቶ ሐጏስ ገ/መድህን(ሁለተኛ ተከሳሽ) ንብረት በሆነችው እና በአቶ ፊሲል ሐጏስ(ሦስተኛ ተከሳሽ) ንብረት በሆነችው እና ቁጥሯ 3-37484/3-04254 በሆነች መኪና ተጭኖ በመጓጓዝ ላይ እንዲለ የመኪናው ተሳቢ በመገለበጡ ግምቱ ብር 129,333.93(አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ሰላሳ ሦስት ብር ከዘጠና ሦስት ሳንቲም) በሆነ 42 በርሜል እና 4 ጀሪካን ኬሚካል ላይ ጉዲት በመድረሱ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለደንበኛዬ መድህን ከፍያለሁ እና ተከሳሾቹ ይህንን የገንዘብ መጠን ከነወለደ ይክፈለኝ የሚል ነው።
ተከሳሾቹም ለቀረበባቸው ክስ መልስ እንዱሰጡ በታዘዘው መሰረት፣ አንደኛ ተከሳሽ በሰጠው መልስ ከሳሹና ደንበኛዬ የሚለው ባለንብረት የፈጸሙት የኢንሹራንስ ውል ተገቢውን የአፃፃፍ ፍርም ያላሟላ በመሆኑ ለከሳሹ የመዲረግ መብት አይፈጥርለትም፤ለከሳሹም የመዲረግ መብት በባለንብረቱ አልተሰጠውም፤እንዱሁም ክሱ በይርጋ ይታገዲል፤በኢንሹራንስ ውለ የተዋዋይ ወገኖችና የምስክሮች ፊርማ የላለ በመሆኑ ውጤት የለውም ብሎል፤
ሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ እኔ የማጓጓዙ ውል ተዋዋይ አይደለሁም፤እቃው የተጫነበት ንብረት የእኔ ስለመሆኑም የሚያስረዲ ማስረጃ አልቀረበም፤አደጋው በደረሰ በ7 ቀናት ውስጥም ያልቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብሎል፤
ሦስተኛ ተከሳሽም የተባለው እቃ አልጫነኩም፤ክሱም በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት መልሷል።
የስር ፍርድ ቤቱም በግራ ቀኙ ወገኖች መካከል የቃል ክርክር ካካሄደ በኋላ ከላይ ላቀረቡት ክርክሮች እንደሚከተለው ወስኗል፣ይኸውም የስር ከሳሽ የመዲረግ መብት አለኝ በማለት ክሱን ያቀረበው ወይም መብቱ መነጨ የሚለው ኢንሹራንሱን ከከፈለው ደንበኛው ጋር ካደረገው የኢንሹራንስ ውልና ይህ ደንበኛው በሱ መብት ተዲርጏ ክሱን በተከሳሾቹ ላይ ማቅረብ እንደሚችል ከፃፈለት ደብዲቤ በመሆኑና ተደረገ የተባለው የኢንሹራንስ ውል በሚመለከት በንግድ ሕግ አስገዲጅ የሆነ የተለየ ፍርማሉቲ ያልተቀመጠለት በመሆኑ የኢንሹራንሱ ውል የፍርማሉቲ ጉዲይ የሚታየው በፍትሐብሄር ሕጉ በተቀመጠው በጠቅላላ ውል ዓንቀፆች 1725፣1727 እና 1720(1) መሰረት ተደርጏ በመሆኑና ከሳሹ ከደንበኛው ጋር ያደረገው የኢንሹራንስ ውል በግራ ቀኙ ወገኖችና በምስክሮች ያልተፈረመ በመሆኑ ህጋዊ እውቅና የለውም፣አይጸናም፤ ስለሆነም የከሳሹ ደንበኛ በላለ የኢንሹራንስ ውል ተመስርቶ ለከሳሽ የፃፈለት የመዲረግ መብት ህጋዊ ውጤት የለውም፣ ሁለተኛው ተከሳሽም የንብረቶቹ አጓዥ ተብለው በማጓጓዝ ሰነድ እስካልተጠቀሱ ድረስ የመኪናው ባለቤት በመሆናቸው ብቻ አጓዥ ሉባለ ስለማይገባ በውልም ሆነ ከውል ውጭ መሰረት ያደረገ ክስ ላቀርብባቸው አይገባም የሚል ነው።
ከላይ የሰፈረውን የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በመቃወም የአሁኑ አመልካች ወደ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ወገኖች ካከራከረ በኋላ በኮ/መ/ቁ. 41455፣መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቶታል።
በስር ፍ/ቤቶቹ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት አመልካቹ ታህሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችልት ያቀረበ ሲሆን፤አጭር ይዘቱም፡- ከደንበኛዬ ጋር ህጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል በማድረግ እቃዎቹ በተጠሪው መኪና ከወደብ ተጭኖ ወደ አዱስ አበባ በመምጣት ላይ እያለ አደጋ በመድረሱ ለደንበኛዬ በክስ የቀረበውን ገንዘብ መክፈላ ተረጋግጦ እያለ፣የመኪናዋ ባለቤት ተጠሪው መሆናቸው እና የጭነት ውለ የተደረገው ከወኪላቸው (የስር አንደኛ ተከሳሽ) ጋር በመሆኑ በንግድ ህጉ መሰረት የእቃው አጓዥ መባል ሲገባቸው አጓዥ መሆናቸው በሰነደ አልተጠቀሱም ስለሆነም አጓዥ አይባልም፤የመኪናዋ ባለቤት ቢሆንም ጉዲዩ የተያያዘው ከውል ጋር በመሆኑ ከውል ውጭ መሰረት በማድረግ ሉጠየቁ አይገባም በማለት የተሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉሻረልኝ ይገባል የሚል ነው።
ተጠሪውም ነሐሴ 07 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው በስር ፍ/ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ማህበር የእኔ ወኪል አይደለም፤ እኔ የፈጸምኩት የእቃ አጓዥነት ውል የለም፤አመልካች ገንዘቡ ከስር ሦስተኛ ተከሳሽ እንዱያገኝ ተፈርድለት እያለ አላግባብ በእኔ ላይ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ይህ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር ከላይ እየተገለፀ በመጣው መልኩ ከተገነዘበ በኋላ፣
አመልካች ከደንበኛው ጋር የፈጸመው ህጋዊ የኢንሹራንስ ውል አለ ወይስ የለም?
አመልካች ለደንበኛው ተክቶ ወይም ተዲርጏ በስር ተከሳሾች (በእነ ተጠሪ) ክስ ሉመሰረት ይችላል ወይስ አይችልም?
ተጠሪው የእቃው ማጓዝ ውል ወስደዋል ወይስ አልወሰደም? በልላ አባባል ተጠሪው በዚህ ጉዲይ አጓዥ ናቸው ወይስ አይደለም?
የሚለ መሰረታዊ ጭብጦችን በማውጣት ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል፡የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ የስር ፍርድ ቤቶቹ የሰጡት ትርጉም በተጠሪውና በደንበኛው መካከል በሕግ የሚጸና የኢንሹራንስ ውል የለም የሚል ለዚህም የሰጡት ምክንያት በውለ ላይ ተዋዋይ ወገኖቹና ምስክሮች ስላልፈርሙበት በሕግ የሚፈለግበትን ተገቢ ፍርማሉቲ አላሟላም፤የንግድ ሕጉ የኢንሹራንስ ውል ይዘት ከሚዘረዝር በስተቀር ስለውለ ፍርማሉቲ የሚለው ነገር ስለላለ የኢንሹራንስ ውል ፍርማሉቲ በሚመለከት በፍትሃብሄር ሕግ ውስጥ በጠቅላላ ውለ ዓንቀጽ 1725 እና 1727 በተመለከተው መሰረት መከናወን እንዲለበት ማለትም ውለ የግድ በጽሁፍ መዘጋጀት ያለበትና ተዋዋይ ወገኖችና ምስክሮች የግድ ሉርፈርሙት እንደሚገባ፣ይህ ሳይሟላ ከቀረ ግን በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር ዓንቀጽ 1720(1) መሰረት ውለ እንደረቂቅ የሚቆጠርና ምንም አይነት ውጤት የማያስከትል ነው፤በመሆኑም አመልካች ከደንበኛው ጋር ያደረገው የኢንሹራንስ ውል በተከሳሾቹ ላይ ግዳታ ሉያስከትል አይችልም የሚል ነው። ይሁን እንጂ የንግድ ሕጉ ስለ የኢንሹራንስ ውል ፍርማሉቲ ምንም ነገር አላለም የተባለው ተገቢነት የለውም። ምክንያቱም የንግድ ሕግ አንቀጽ 657 ስለ ውለ ፍርማሉቲ የሚደነግግ ሣሳብ አስፍሯል፤ ይኸውም የኢንሹራንስ ውል በኢንሹራንስ ውል ፕሉሲ በሚባል ጽሁፍ እንደሚደገፍና የመድህን ገቢው ጥያቄ መሰረት በማድረግ በፕሉሲው ላይ መድህን ሰጭው ከፈረመ ህጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት በመድህን ሰጭው እና በመድህን ገቢው መካከል እንደሚመሰረት ነው፤ይህ ሁኔታ ደግሞ የንግድ ሕጉ ልዩ የሆነ የኢንሹራንስ ውል አፈፃፀም የሰፈረ እንጂ ጉዲዩ በጠቅላላ የውል ሕግ የሚመራ ግንኙነት አይደለም፤ይህ ሰበር ችልትም የኢንሹራንስ ውል አለ ለማለት ተመሳሳይ ትርጉም በ
ሚያዝያ 09 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ሰጥቶበታል። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶቹ በአመልካችና በደንበኛው መካከል የተደረገው ውል ሁለቱ ወገኖች እና ምስክሮች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1725 እና 1727 በሚያዙት መሰረት ባለመፈረማቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1720/1/ መሰረት የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት የለም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ ሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። በመሆኑም በአመልካችና በደንበኛው መካከል ህጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት አለ ብለናል።
ሁለተኛው ጭብጥ በተመለከተ የአመልካች ደንበኛ ሐምል 17 ቀን 1995 ዓ.ም የተፃፈ ሰነድ አዘጋጅቶ አመልካቹ በእርሱ እግር ተተክቶ መብቱን የማስከበር ወይም የመዲረግ መብት እንዲለው ቢያረጋግጥም፣የስር ፍ/ቤቶቹ በሰጡት ፍርድ ይህ የመዲረግ መብት ሕጋዊ ከሆነ የኢንሹራንስ ውል የመነጨ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ይሁን እንጂ በአመልካችና በደንበኛው መካከል ሕጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት እንዲለ በላይኛው ጭብጥ የተረጋገጠ ነው። ስለሆነም አመልካቹ ን/ሕ/ቁ. 683 መሰረት በደንበኛው እግር ተዲርጏ በተከሳሾቹ ላይ ክስ ማቅረብ የሚያስችለውን መብት ከደንበኛው አግኝቶ እያለ የስር ፍ/ቤቶቹ ሳይቀበለት መቅረታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተገቢነት የለውም ብለናል።
ሦስተኛውን ጭብጥ በሚመለከት አመልካቹ ተጠሪው የመኪናዋ ባለንብረት በመሆናቸው አጓዥ ናቸው፤በስር ፍ/ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው የተባበሩት የጭነት ማመላለሻ ንብረቶች ማህበር ለተጠሪው ጥቅም ሲባል የሚጫን ነገር ከማፈላለግ ውጭ ጥቅሙ ለተጠሪው የሚውል በመሆኑ በን/ሕ/ቁ. 566/የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2251 መሰረት የትራንስፕርት ስራው በውክልና የሚያስተዲድር አካል ነው፤ስለሆነም ተጠሪው አጓዥ መባል አለበት ሲል ተጠሪው ደግሞ አጓዥ እንዲልሆኑ በመግለጽ የአመልካቹ አባባለን የሚደግፍለት ማስረጃ አላቀረበም በማለት ይከራከራለ። ይሁን እንጂ ጉዲት ያደረሰችውን የአሁኑ ተጠሪ መኪናን በሚመለከት ከአመልካቹ ደንበኛ ጋር የአሁኑ ተጠሪ የመጓጓዣ ውል በቀጥታ የፈጸመው በስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው (የተባበሩት የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር) ቢሆንም ይህ አካል ያደረገው ውል ተጠሪውን በመወከል ነው፤ምክንያቱም የዚህ አካል የስራ ድርሻ በማህበሩ የታቀፈት መኪኖች የጭነት ስራ እንዱያገኙ ከማድረግ አልፍ የእያንዲንደ መኪና የጭነት ኪራይ ገቢ የባለቤቱ ነው፣በአሁኑ ክርክርም ተጠሪው መኪናቸው በተባበሩት የጭነት ማመላለሻ ማህበር ከመታቀፎ ውጭ የመኪናው ገቢ በቀጥታ ተጠቃሚ ናቸው፤ስለሆነም በንግድ ሕ/ቁ. 566 እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2251 መሰረት ተጠሪው ከአመልካቹ ደንበኛ ጋር የጭነት ማጓዝ ውል የነበራቸው ሆነው እያለ የስር ፍ/ቤቶቹ ተጠሪው አጓዥ አይደለም በማለት የደረሱበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
No topics extracted.