No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የባህርና ትራንዚት አግልግልት ድርጅት - ነ/ፈጅ በዛብህ አመዳ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ሰናይት በዲሣ
ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ተጠሪ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የመሰረተው ክስ ነው። ተጠሪ ባቀረበው ክስ ደንበኛው የሆነው አዋሽ ወይን ጠጅ አ/ማ ለፊብሪካው አገልግልት የሚውል የጠርሙስ ማጠቢያ ማሽን በጉዞ ላይ ለሚደርስበት ጉዲትና ውድመት የመድን ሽፊን ሰጥቷል። የተጠሪ ደንበኛ የጉምሩክ አስተላላፉነት ውክልና ቀጥልም የማጓጓዝ ትእዛዝ ለአመልካች የሰጠ ሲሆን ማሽኑን በስር ሁለተኛ ተከሣሽ በነበሩት ግለሰብ መኪና አስጭኖ ሲያመጣ ተሽከርካሪው ተገልብጦ በማሽኑ ላይ ጉዲት ደርሷል። ማሺኑም ሙለ በሙለ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ ብር 2,200,856.43(ሁለት ሚሉዮን ሁለት መቶ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ስድስት ከአርባ ሦስት ሳንቲም) ለደንበኛው ስለከፈለ አመልካች በገባው የውክልናና የማጓጓዝ ውል መሰረት፣በንግድ ሕግ ቁጥር 590 ባለበት ሃላፉነት፣ሁለተኛ ተከሣሽም የተሽከርካሪው ባለንብረት በመሆናቸው ሁለቱም ገንዘቡን ሉተኩ ይገባል በማለት ጠይቋል። ፍ/ቤቱም ክርክሩን ተመልክቶ አመልካች እቃውን ያጓጓዘው በውክልና ስልጣን በመሆኑ ሉጠየቅ አይገባም በማለት ሁለተኛው ተከሣሽ ብቻ ገንዘቡን እንዱከፍለ ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ አመልካች እቃውን ያጓጓዘው ራሱን ችል እንጂ በውክልና ስላልሆነ ለጉዲቱ ኃላፉ ላሆን ይገባል በማለት ከስር ሁለተኛ ተከሣሽ ጋር ክስ የቀረበበትን ገንዘብ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍል ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ የሰበር ችልትም አመልካች ማሽኑን ያጓጓዘው በውክልና ነው ወይስ እራሱን ችል ነው? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት ግራ ቀኙ ቀርበው ክርክራቸውን በቃል አሰምተዋል። ችልቱም አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካላቸው የሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ ተመክቷል።
ከፍ ሲል እንደተገለጸው የተጠሪ ደንበኛ ያስመጣውን የጠርሙስ ማጠቢያ ማሽን አመልካች ያጓጓዘው መሆኑ አከራካሪ አልሆነም። አከራካሪ የሆነው ነጥብ አመልካች ማሽኑን ያጓጓዘው እራሱ አጓጓዥ ሆኖ ነው? ወይስ በውክልና ነው? የሚለው ነው።
አመልካች እቃ አስተላላፉ ለመሆኑ ተጠሪም በክሱ ገልፆታል። እቃ አስተላላፉ ምን ማለት እንደሆነ እና ምን ምን ስራዎችን እንሚሰራ ስለእቃ አስተላላፉነት እና የመርከብ ውክልና ስራ ፈቃድ አስመልክቶ የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 37/90 ያመለክታል። በዚሁ በተጠቀሰው ደንብ አንቀጽ 2/1/ ስር እቃ አስተላላፉ በአገር ውስጥ ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ እቃ ተቀባይነት ወይም እቃ ላኪን በመወከል የጉምሩክ፣የወደብ ወይም ላልች ስርአቶች አስፈጽሞ ገቢ ወይም የወጪ እቃዎችን ወደብ እንዱገቡ ወይም እንዱወጡ የሚያደርግ ሲሆን እቃን የማጓጓዝና የማስረከብን ስራም ይጨምራል። ይህ ድንጋጌ በጥቅለ ሲታይ እቃ አስተላለፉው ስራውን የሚያከናውነው እቃ ላኪዎችን ወይም ተቀባዮችን በመወከል በውክልና ስልጣን መሆኑን የሚያሣይ ነው። በእርግጥ የእቃ ማጓጓዝ ተግባሩን እንዳት ሉያከናውን እንደሚችል በደንቡ አንቀጽ 3/6/ እና /7/ ስር ተለይቶ ተቀምጧል። በአንቀጽ 3/6/ ስር እቃ አስተላላፉው የራሱ የትራንስፕርት አገልግልት ካለው የእቃ ማጓጓዙን ተግባር የሚያከናውነው እንደ አጓጓዥ ሆኖ እንጂ በውክልና ስልጣን አለመሆኑ በግልጽ ተመልክቷል። ይህም በአንቀጽ 2/1/ ስር የተመለከተው የውክልና ስልጣን ልዩ ሁኔታ(exception) ነው።
በልላ በኩል ግን የራሱ ትራንስፕርት ከላው ወይም ባለእቃው የራሱን ማጓጓዣ ካላቀረበ እቃ አስተላላፉው ማጓጓዣ ተከራይቶ እቃውን እንደሚያጓጉዝ በንኡስ አንቀጽ 7 ስር ተመልክቷል። ይህ ድንጋጌ በንኡስ አንቀጽ 6 ስር በግልጽ እንደተመለከተው የማጓጓዝ ስራውን እንደ አጓጓዥ ሆኖ እንደሚሰራ አያስቀምጥም። ከፍ ሲል እንደተገለጸው ደግሞ እቃ አስተላላፉ ስራውን ሁለ የሚያከናውነው በውክልና በመሆኑ በእራሱ ስም ስለራሱ ሆኖ ይሰራል ተብል በንኡስ ቁጥር 7 ስር ልዩ ሁኔታ (exception) ስላልተመለከተ የማጓጓዝ ተግባሩን የሚያከናውነው በውክልና መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩል የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች የማጓጓዝ ውለን በራሱ ስም መፈጸሙ የማጓጓዝ ተግባሩን የፈፀመው እንደ አጓዥ ሆኖ ነው በማለት ወስኗል። ከላይ እንደተገለፀው ግን እቃ አስተላላፉው እቃውን በወደብ ማስተላለፍ፣የወደብና የጉምሩክ ስርአቶችንና የእቃ ማጓጓዝ ተግባርን በሙለ የሚፈጽመው በውክልና ነው። እንደ አጓዠ ሆኖ የሚቆጠረው የማጓጓዙን ስራ በራሱ ማጓጓዣ ካጓጓዘ ብቻ ነው። የማጓጓዣ ውለን በስሙ መፈረሙ ብቻ ስራው በውክልና ያልተሰራ መሆኑን አያመለክትም በእርግጥ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2251 የተገለጸው የእቃ አስተላላፉ በደንብ ቁጥር 37/90 ስር ከተመለከተው ጋር ሙለ በሙለ ተመሣሣይ ተግባር የሚፈጽም ባይሆንም እቃ አስተላላፉው ስራውን የሚያከናውነው በራሱ ስም ሆኖ ለወካዩ ጥቅም መሆኑን ያመለክታል። ስለሆነም የእቃ አስተላላፉ በራሱ ስም የሚያደርጋቸው ተግባሮች ለወካዩ ጥቅም በውክልና ስልጣን የሚፈጸሙ ናቸው ማለት ነው።
አመልካች ወኪል ነው ከተባለ ተጠያቂ ላሆን የሚችለው የውክልና ስራው በክፊት ያደረገ መሆኑ ከተረጋገጠ ብቻ እንጂ ጉዲት ስለደረሰ ብቻ በኃላፉነት ተጠያቂ እንደማይሆን በንግድ ሕግ ቁጥር 683/3/ ስር ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ ደግሞ አመልካች ስራውን በክፊት በማከናወኑ ጉዲት ያደረሰ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም።
በመሆኑም አመልካች ለደረሰው ጉዲት በኃላፉነት የሚጠየቅበት የሕግ መሰረት የለም።
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶችም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች ኃላፉ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት።
የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 28225 በ7/08/2000 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 40949 በ5/3/99 የሰጠው ውሣኔ ጸንቷል።
አመልካች የማጓጓዝ ስራውን የሰራው በውክልና ስልጣን በመሆኑ ኃላፉነት የለበትም ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.