No summary available.
ሐምል 16 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- በወላይታ ዞን የቦዱቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት - ነ/ፈጅ አረታ ቶሩ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ወንድሙ ኃይላ - ጠበቃ ዲንኤል ገ/ጊዮርጊስ ቀርበዋል።
ጉዲዩን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቹ የካቲት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ አቤቱታው የደቡብ ብ/ብ/ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በፍ/ር ሰበር መ/ቁ. 22624፣ ታህሣሥ 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱታረምለት በመጠየቁ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በወላይታ ዞን በቦዱቲ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ በአፈፃፀም ከሳሽነት እንዱሁም የአሁኑ አመልካች በአፈፃፀም ተከሣሽነት ተከራክረዋል፤ የአሁኑ ተጠሪ በሥር ፍ/ቤቱ ያቀረቡት ክስ አጭር ይዘቱ በቦዱቲ ከተማ ምዕራብ ክፍል በ6ዐዐ ሜ.ካ ያረፈውን ቤትና ቦታ ከወላጅ አባታቸው አቶ ኃይላ መርሻ እና ከአክስቶቼ ወ/ሮ የሺ መርሻና ወ/ሮ ተዋበች መርሻ በስጦታ አግኝቼ ስጦታው በቦዱቲ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፀደቀልኝ ሲሆን በዚሁ ውሣኔ መሰረት የቦዱቲ ማዘጋጃ ቤት ወደ ስሜ እንዱያዞርልኝ ብጠይቀውም ፍቃደኛ ባለመሆኑ በፍርድ ቤቱ ተገድድ ይፈጽምልኝ የሚል ሲሆን፣ ሥር ተከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ወደ ሥር ፍ/ቤቱ ቀርቦ በአከራካሪው ቦታ የመንግሥት ቤት ስላለና ጉዲዩ በቤቶች ኤጄንሲ መታየት ያለበት ነው ብል መልስ ሰጥቷል፤ ክርክሩ በመጀመሪያ የቀረበለት የቦዱቲ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. ዐዐ446 ጥቅምት 14/2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት በሰጠው ውሣኔ ጉዲዩ በቤቶች አጀንሲ መታየት ያለበት እንጂ በቀጥታ ማስፈፀም አይቻልም ያለውን የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 8618፣ ሰኔ 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጉዲዩን በይግባኝ አከራክሮ የሥር ፍ/ቤቱን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቶታል።
ከላይ የሰፈረውን የሥር ፍርድ ቤቶቹ ውሣኔ በመቃወም የአሁኑ ተጠሪ ጉዲዩን ወደ ደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እንዲቀረቡትና ፍ/ቤቱም የመንግሥትና የግለሰቡ ይዞታዎች ለይቶ መፈፀም ሲገባ የግለሰቡ /የአሁን ተጠሪ/ መብት በደፈናው መዝጋት አግባብነቱ ለመመርመር ብል ጉዲዩን ካቀረበው በኋላ ተከሣሹ ተቋም መልስ እንዱሰጥ ባዘዘው መሰረት ውክልናቸው በተከሣሹ መስሪያ ቤት በሚገባ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የተቋሙ የፔሮቶኮል ቁጥርና ፊርማ በላለበት ኀዲር 12/2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ ነገረ ፈጁ የተባለት በሰጡት መልስ የግለሰቡ ቤት ከመንግሥት የውርስ ቤቶችና ቦታ ነጥለን ለማስረከብ ዝግጁ ነን ብለዋል በማለትና መልሱ የተቋሙ የፔሮቶኮል ቁጥርና ፊርማ ባይኖረውም የሚታመን ነው በማለት በዚሁ መሰረት እንዱፈፀም በመወሰን የሥር ፍ/ቤቶቹ የሰጡትን ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ሽሮታል።
ከላይ የሰፈረውን የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በፍ/ር
ታህሣሥ 17/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት የአሁኑ አመልካች የካቲት 24/2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ አቤቱታቸው ውሣኔው እንዱሻርለት ጠይቋል፤ ያቀረበው ምክንያትም ተገቢው ውክልና ባልተሰጠው ነገረ ፈጅ የቀረበው የፔሮቶኮል ቁጥርና ፊርማ የላለበትን መልስ መሰረት አድርጎ ውሣኔ መስጠቱ ተገቢነት የለውም የቀረበው መልስ የአመልካች አይደለም፤ ከአዋጅ ውጭ የተወረሱትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 11ዐ/87 መሰረት አጣርቶ የመወሰን ስልጣን የቤቶች ኤጀንሲ እንጂ የፍ/ቤቱ አይደለም የሚል ነው። ይህ ሰበር ችልትም የአመልካች ስምና ፊርማ እንዱሁም የፔሮቶኮል ቁጥር የላለውን ደብዲቤ መሰረት በማድረግ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ መሻሩ አግባብነቱን ለመመርመር ብል ጉዲዩን በማቅረብ ተጠሪው መልሱን እንዱሰጥ አዟል፤ ተጠሪውም መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 የተፃፈ መልስ ሰጥተዋል፤ አጭር ይዘቱም የአመልካች ነገረ ፈጅ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የላቸውም የተባለት አቶ መሰለ ማሞ በትክክል የተቋሙ ነገረ ፈጅ ናቸው፤ እኚህ ነ/ፈጅ ባቀረቡት መልስ ለምን የፔሮቶኮል ቁጥርና ፊርማ የለውም ተብለው ሲጠየቁ ከቦታው ርቀት አኳያ ትራንስፕርት እንዲያመልጠኝ ብዬ በመቸኮላ እንጂ የጽሁፈ /የመልሱ/ ይዘት በትክክል የአመልካቹ መሆኑ ስላስረደና የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልትም በዚህ አባባላቸው እምነት በማሳደሩና ይህን ማድረጉም ተገቢነት ያለው ነው፤ አመልካቹ ቤቶቹ የተወረሱ ናቸው ይበል እንጂ የተወረሱ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥለት ማስረጃ አላቀረበም፤ ስለሆነም የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ፍርድ ይጽናልኝ የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ወገኖች የክርክር አመጣጥ ከላይ እየተገለፀ እንደመጣው በመገንዘብ ይህ ፍርድ ቤት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ለግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር የመጨረሻ እልባት የሰጠው ከአመልካች ተገቢውን ፍርማሉቲ የጠበቀ መልስ ከቀረበለት በኋላ ነው ወይስ አይደለም? የሚል መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
በዚህ ክርክር ለመገንዘብ እንደተቻለው የአመልካቹ ቁልፍ ቅሬታ የሚያተኩረው በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተላለፈብኝ ፍርድ በተገቢው ነገረ ፈጅ ሳልወክልና ነገረ ፈጅ የተባለት ግለሰብ የሰጡት መልስም የአመልካች የፔሮቶኮል ቁጥርና ፊርማ በተገቢው መንገድ ያላሟላና በዚህ መልስ መሰረት ተደርጎ የተሰጠ ውሳኔም የአመልካች ክርክር በአግባቡ ያካተተ ስላልሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል ሲል ተጠሪው ደግሞ ይህንን አይቀበልም። አመልካች መንግስታዊ ተቋም ሲሆን የመንግስት ተቋም በሚከስበትም ሆነ በሚከሰስበት ክርክር ወክል የሚከራከር ነገረ ፈጅ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 59 መሰረት በሚመለከተው የመንግስት ተወካይ መወከል አለበት። የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ ዓንቀፅ 80፣92 እና 93 እንደሚገልፁትም ማንኛውም አቤቱታ በዋናው ባለጉዲይ ወይም በጠበቃው መፈረም እንዲለበት ነው፤ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92(3) በተለይ እንዲሰፈረው ደግሞ መንግስት በሚከስበትም ሆነ በሚከሰስበት ጊዜ አቤቱታውን የሚፈርመው ስለዚህ ጉዲይ በተለይ የተወከለ ወይም ስልጣን ያለው ሰው ነው፤ የፅሁፈ ትክክለኛነት የሚያረጋግጠው ደግሞ ጉዲዩን በተለይ የሚያውቀውና ለዚህም የተለየ ስልጣን የተሰጠው ክፍል ሃላፉ እንደሆነ ነው። በእጃችን ወዲለው ክርክር ስንመጣ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንደ የአመልካች መልስ በመቁጠር ለውሳኔው ግብአት ያደረገው የፅሁፍ መልስ የፔሮቶኮል ቁጥር የላለውና በሚመለከተው የአመልካች ወኪል ያልተፈረመ ሆኖ እያለ ነገረ ፈጅ ነኝ ብለው የቀረቡት ሰው ትራንስፕርት እንዲያመልጠኝ በመቸኮላ በሚመለከተው ኃላፉ አላስፈረምኩም ያለትን ሃሣብ በማመን ብቻ ተመስርቶ የቀረበው መልስ የአመልካቹ ነው ብል መውሰደ ከላይ ከተጠቀሱት ህጎች አኳያ ተገናዝቦ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ፈፅሟል፤ ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ር ሰበር መ. ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል፤ ይፃፍ።
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልቱ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔን የሻረው የአሁኑ አመልካች መልስ መሆኑ በተገቢው መንገድ ባላረጋገጠው ፅሁፍ ተመስርቶ ስለሆነ ተገቢውን ፍርማሉቲ ያሟላ የአመልካች መልስ ተቀብል ለጉዲዩ የመሰለውን ውሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል፤ ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወገኖች በዚህ ፍ/ቤት ላካሄደት ክርክር ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
የካቲት 24 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት የተላለፈው እግድ ተነስቷል፤ ለሚመለከተው ይፃፍ።
ጉዲዩ ያለቀ በመሆኑ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.