No summary available.
ሰኔ 23 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ነጂሃ ድዋላ ዋይስ - አልቀረበችም።
ተጠሪ፡- አዋሽ ኢንተርናሸናል ባንክ አ/ማ - ነ/ፈጅ ቀርቧል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ3497 መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በሰጠው ትእዛዝ ላይ ነው። በመዝገቡ እንደተመለከተው ጉዲዩ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበችውን የገንዘብ ይመለስልኝ ጥያቄን መሰረት ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ ልትመሰርት የቻለችው ድሬዲዋ በሚገኘው ቅርንጫፈ በኩል ተገቢውን የአገልግልት ኮሚሽን በመክፈል አዱስ አበባ በሚገኘው ሲዲሞ ተራ በሚባለው ቅርንጫፈ አቶ ሸሪፍ ከዱር ለተባለ ሰው እንዱሰጥ የላከችውን ብር 45,ዐዐዐ (አርባ አምስት ሺህ) ለማይመለከተው ሰው ከፍያለሁ በማለት አደራውን አልተወጣም በማለት ነው።
ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ ገንዘቡ አመልካች በገለጸችው ሁኔታ መላኩንና የደረሰው መሆኑን ሳይክድ ነገር ግን ገንዘቡ የተላከልኝ ሰው እኔ ነኝ በማለት መታወቂያ ይዞ ለመጣ ሰው መክፈለን በመግለጽ ከክሱ በነፃ ይሰናበት ዘንድ እንዱወሰንለት ጠይቆአል። ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም በዚህ መልክ የቀረበውን የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ ክሱን ውድቅ በማድረግ ተጠሪን በነፃ አሰናብቶአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሳይቀበል ቀርቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሰኔ 3 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጭበርብሮ ገንዘቡን ለማይገባው ሰው የከፈለው ተጠሪ መሆኑ እየታወቀ ገንዘቡን ለአመልካች ለመተካት አይገደድም በሚል የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው አመልካች ተገቢውን ኮሚሽን በመክፈል ገንዘቡን ለባንኩ አስረክባለች። ገንዘቡን ለባንኩ የሰጠችውም ለተላከለት ሰው እንዱያደርስላት ነው። በእርግጥም ባንኩ የተሰጠው አደራ ገንዘቡን ለተላከለት ሰው ማድረስ እንደመሆኑ የማድረስ ግዳታ አለበት። ነገር ግን ባንኩ /ተጠሪ/ ገንዘቡን ለተላከለት ሰው አላደረሰም። ይልቁንም ለማይመለከተው /ላልተላከለት/ ሰው መክፈለ ተረጋግጦአል። በተጠሪ ክርክር እንደተገለጸው ገንዘቡን የከፈለው የተላከልኝ ሰው እኔ ነኝ የሚል መታወቂያ ደብተር የያዘ ሰው ስለቀረበ ነው። ይህ ሰው ግን በእርግጥም አመልካች ገንዘብ የላከችለት ሰው አይደለም። በመሆኑም በዚህ ሁኔታ የተጭበረበረው ተጠሪ /ባንኩ/ እንጂ አመልካች አይደለችም። አጭበርባሪውን ሰው ከሶ ገንዘቡን ማስመለስ የሚችለውም ተጠሪ እንጂ አመልካች ልትሆን አትችልም። ግልጽ ሆኖ እንደሚታየው በአመልካች እና አጭበርብሮ ገንዘቡን ከተጠሪው ባንክ በወሰደው ሰው መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም። ተጠሪ ስለተጭበረበረ አመልካችም እንደተጭበረበረች ይቆጠራል ወደሚለው መደምደሚያ የሚደርስ ሁኔታ የለም። በዚህ መዝገብ የተያዘው አከራካሪ ሆኖ የተነሣው ነጥብ ባንክ ሂሣብ /ገንዘብ/ ባላቸው ሰዎች ስም ላልች ሰዎች አጭበርብረው ገንዘብ ከሚያወጡበት ሁኔታ ተለይቶ የሚታይ ነው። ባንክ ገንዘብ ያስቀመጡትን ሰዎች ሰነድች እና ፊርማ አጭበርብሮ በማግኘት ገንዘብ የሚወስደ ሰዎች በባለሂሣቦቹም ሆነ በባንኩ ሉጠየቁ የሚችለበት ሁኔታ ይኖራል። በተያዘው ጉዲይ ግን አመልካች ባንኩን አጭበርብሮ ገንዘብ የወሰደውን ሰው በመጠየቅ ገንዘቡን የምታስመልስበት አግባብ የለም።
ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ተጠሪ ገንዘቡን ለተላከለት ሰው ለመስጠት ከአመልካች ሲቀበል የአደራውን ሃላፉነት ወስድአል። አደራ ተቀባይ የሆነው ወገን በአደራ ያስቀመጠውን /የተቀበለውን/ ዕቃ መመለስ ያለበት ለአደራ ሰጪው ወይም አደራ ሰጪው ይቀበልልኝ ብል ላመለከተው ሰው እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2792/1/ በግልጽ ተመልክቶአል።
ተጠሪ ከእነዚህ ግዳታዎቹ አንደንም አልተወጣም። ስለዚህም ገንዘቡን ለአመልካች አልከፍልም የሚልበት የሕግ ምክንያት የለም። አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔም ከዚህ አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 21113 ኀዲር 2ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ3497 መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለአመልካች ይመልስ ብለናል። በሥር ፍ/ቤቶች እና በዚህ ሰበር ችልት አመልካች የከፈለችው የዲኝነት ገንዘብም ተጠሪ ይተካላት ብለናል።
ላልች ወጪና ኪሣራ በተመለከተ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሣኔው ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ። መዝገቡ ይመለስ።