No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን - ሳሙኤል ተገኑ ቀረበ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - የቀረበ የለም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የመድን ዋስትና ውልን መሰረት ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንዲየነው ተጠሪ ለአመልካች መኪና የመድን ዋስትና ሰጥቶአል። መኪናው ሲሽከረከር በነበረ ጊዜ በመገልበጡ ጉዲት ደርሶበታል። ተጠሪም የገባውን የመድን ዋስትና ግዳታ መሰረት በማድረግ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ መኪናው የተገለበጠው በሹፋሩ ሳይሆን በብልሽት ምክንያት አገልግልት መስጠት አቁሞ በነበረበት ጊዜ የተበላሸውን ፍሬን እያስተካከለ የነበረው መካኒክ ሥራውን ሲሞክር መሆኑን ስለደረስኩበት ኃላፉነት ሳይኖርብኝ ለጥገና ያወጣሁት ገንዘብ ሉመለስልኝ ይገባል በማለት በአመልካች ላይ ክስ መስርቷል። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ክሱ በንግድ ሕግ ቁ 674(1) ወይም (2) መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቦአል። የስረ-ነገር ክርክር በማንሳትም ተከላክልአል።
ክሱን ያስተናገደው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከመረመረ በኋላ የተጠሪን ጥያቄ ሙለ በሙለ በመቀበል ክስ የቀረበበትና ገንዘብ ከነወለደ እና የጠበቃ አበል ጋር እንዱከፈለው ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔውን አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
አመልካች ታሕሣሥ 23 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተፈጸመ ያለውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል። በበኩላችንም የአመልካችን የይርጋ ክርክር የታለፈው በአግባቡ ነው ወይ? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል።
እንደምንመለከተው በዚህ የሰበር ችልት ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው የክርክር ጭብጭ ተጠሪ በአመልካች ላይ የመሰረተው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል ወይስ አልሆነም? የሚለው ነው። ይህ ጭብጥ ግራቀኝ ወገኖችን ያከራከረ ወይም ግራቀኝ ወገኖች የተለያዩት የሕግ አግባብ /የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.246(1)/ በመሆኑ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር ተገናዝቦ የሚታይ ይሆናል። በልላ በኩል ግን ወደሕጉ ከመኬደ በፉት ከዚህ የተያያዘው የፍሬ ነገር አግባብ መመርመሩ ተገቢ ይሆናል።
በግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንደተመለከተው ተጠሪ ክሱን ያቀረበው ሚያዝያ 3 ቀን 1999 ዓ.ም ሲሆን ለክሱ መነሻ የሆነው ጉዲት ደረሰ የተባለው ደግሞ ግንቦት 12 ቀን 1994 ዓ.ም ነው። ይህ ጊዜ ማለትም ጉዲቱ በደረሰበት እና ክሱ በቀረበበት መሃል ያለው ሲታሰብ አራት ዓመት ከአስር ወር በላይ ነው። ይህ እንግዱህ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው እውነታ ሲሆን፣ እውነታው ከየትኛው ሕግ ጋር ሲገናዘብ ነው ለይርጋው ክርክር አወሳሰን አግባብነት የሚኖረው የሚለውን ደግሞ ቀጥለን እንመለከታለን።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው ተጠሪ ገንዘቡ ሉመለስልኝ ይገባል በማለት ወደክስ ሉያመራ የቻለው የመድን ሽፊን ባልሰጠሁበት ሁኔታ የወጣ ነው የሚል ምክንያት መሰረት በማድረግ ነው። አመልካች ሁለት የፍሬ ነገር አግባቦችን በመጠቀስ ክሱ በንግድ ሕግ ቁ 674 መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኖአል በማለት ተከራክሮአል። የፍሬ ነገር አግባቦቹም የመጀመሪያው አደጋው ከደረሰበት ቀን አንስቶ ክሱ እስከቀረበበት ቀን ድረስ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ተጠሪ የአደጋውን መንስኤ ካወቀበት ግንቦት 26 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ ክሱ እስከ ቀረበበት ቀን ድረስ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ነው። በዚህ መሰረትም ክሱ በንግድ ሕግ ቁ 674(1) ወይም (2) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው ልባል ይገባል ብልአል። ተጠሪ በአመልካች ክርክር የተጠቀሱት የፍሬ ነገር አግባቦች ትክክል አይደለም የሚል ክርክር የለውም።
የሚከራከረው ያቀረብኩት ክስ ያለአግባብ የተከፈለን ገንዘብ እንዱመለሰ የሚጠይቅ በመሆኑ ተጠሪ በጠቀሰው ሕግ መሰረት በይርጋ ቀሪ አይሆንም። ሕጉ ለተያዘው ክርክር አግባብነት የለውም በማለት ነው።
ተደጋግሞ እንደተገለጸው የግራቀኝ ወገኖች ግንኙት መነሻው የመድን ዋስትና /የኢንሹራንስ/ ውል ነው። ተጠሪ መኪናውን ያስጠገነው የውል ግዳታ እንዲለበት በማመን ነው። በኋላ ግን የጉዲቱን አደራረስ ወይም ሁኔታ ባውቅ ኖሮ መኪናውን አላስጠግንም ነበር። ጉዲቱ የደረሰው በመድን ዋስትና ውለ ባልተሸፈነ ሁኔታ ነው የሚል ምክንያት አንስቶአል። ይህ አይነቱ የተጠሪ ክርክር ከተገባው ውል ውጪ በተሸሸገ ምክንያት ወይም በሐሰት በቀረበ ጥያቄ መሰረት እኔም ልሳሳት ችያለሁ ከሚል ተለይቶ የሚታይ አይደለም። በተሸሸገ ወይም በሐሰት ቃል የቀረበ ጉዲይ ያጋጠመ ሲሆን፣ የይርጋው ዘመን የሚታሰበው ኢንሹራንስ ሰጪው የተሸሸገውን ወይም በሐሰት የቀረበውን ቃል ካወቀበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ በንግድ ሕግ ቁ. 674(2) ተደንግጎአል። የይርጋው ዘመን ሁለት ዓመት እንደሆነም በዚሁ ቁጥር ንኡስ ቁ (1) ተመልክቶአል።ተጠሪ ክሱን ያቀረበው የተደበቀ ነገር መኖሩን ካወቀ ከሁለት ዓመት በላይ ቆይቶ እንደሆነም በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦአል። በመሆኑም አመልካች የንግድ ሕጉን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መከራከሩ ተገቢ ሲሆን የተጠሪ ክርክር ግን የሕግ መሰረት ያለው አይደለም። ሲጠቃለል ተጠሪ ክሱን ያቀረበው በሕጉ በይርጋ ቀሪ ከሆነ በኋላ በመሆኑ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.