No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት- ክንፈ ታደለ ቀረቡ ተጠሪ፡- ብያን ኡመር- ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የጉዲት ካሣ ክፍያን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብ/ክ/መ በምእራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። ተጠሪ ክስ የመሰረተው ጉዲት አደረሰ በተባለው መኪና ባለንብረት እና በሹፋሩ ላይ ነው። አመልካች ለመኪናው የመድን ዋስትና ግዳታ ገብቷል ስለተባለ ጣልቃ እንዱገባ ተጠይቆ ነው የክርክሩ ተካፊይ የሆነው። በዚህ አግባብ መሰረት ቀርቦ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የስረ-ነገር ክርክር አቅርቧል። ደረሰ ለተባለው ጉዲት ኃላፉ ላሆን እንደማይገባው በመግለጽም ተከራክሯል።
በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ተከሣሾቹ እና አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ ናቸው፤ የጉዲት ካሳውን ይክፈለ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ይህን ውሳኔ በመቃወም በአሁኑ አመልካች ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠ/ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም ብሎል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
አመልካች ታሕሣስ 14 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተፈጸመ የሚለውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቧል። በበኩላችንም ጉዲቱ የደረሰው በተጠሪው ጥፊት ነው እየተባለና አመልካችም የመድን ሽፊን ባልሰጠሁበት ተግባር ላይ ተሰማርቶ በነበረው መኪና ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት የለብኝም በማለት መከራከሩ እየታወቀ የጉዲት ካሣ እንዱከፍል መወሰኑ አግባብ ነው ወይ? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ግራ ቀኝ ወገኖቹን አከራክረናል።
ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው አመልካች የሰ/ቁ. 3-29779 አ.አ ለሆነው የጭነት (የእቃ) ተሽከርካሪ የመድን ዋስትና ሰጥቷል። ተጠሪ ጉዲት ደረሰብኝ የሚለው በዚህ መኪና ላይ ተሳፍሮ ሲሄድ በነበረበት ጊዜ ነው። የአመልካች ክርክርም ከዚህ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የቀረበ ነው። የመድን ዋስትና የሰጠሁት በሕዝብ ማመላለሻነት ለተሰማራ መኪና ሳይሆን፣ እቃዎችን ለሚያጓጉዝ የጭነት መኪና በመሆኑ ከገባሁት ውል ውጪ ኃላፉ የምሆንበት ምክንያት የለም በማለት ነው የተከራከረው። በተጠሪ በኩል አመልካች ባቀረበው የፍሬ ነገረ ክርክር ላይ ምንም አይነት ማስተባበያ አልቀረበም።
እንደምንመለከተው አመልካች ክርክሩ ውስጥ የገባው የመኪናው ባለንብረት ጣልቃ እንዱገባለት በመጠየቁ ነው።
ባለመኪናው የጣልቃ ይግባልኝ ጥያቄ ያቀረበው ደግሞ የመድን ዋስትና ውል አለኝ በማለት ነው። አመልካች እንግዱህ በውልህ ትገደዲለህ ከተባለ የውለን ይዘት ማየቱ የግድ ይሆናል። ቀደም ሲል እንደተገለጸው ውለ ዋስትና በተገባለት የጭነት መኪና ላይ ተሳፍረው በሚጓዙ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዲት የሚሸፍን አይደለም። ተደጋግሞ እንደተገለጸው ተጠሪ እንደማንኛውም መንገደኛ በመኪናው ተገጭቶ አይደለም ጉዲት የደረሰበት። በመሆኑም በማንኛውም ሁኔታ፣ የደረሰበት ጉዲት አመልካች በነበረው ውል የሚሸፈን አይደለም። ሲጠቃለል አመልካችን ኃላፉ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ስለዚህ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/የምእራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 08797 መስከረም 26 ቀን 2001 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 71528 ኀዲር 25 ቀን 2001 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ አመልካችን በሚመለከት ያለው የውሳኔው ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 384/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የስር አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሣሾች በነበሩት ላይ የተሰጠው ውሳኔ አልተሻረም። ፀንቷል።
አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ የሚሆንበት የሕግም ሆነ የውል ምክንያት የለም ብለናል።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸው ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.