No summary available.
ሐምል 22 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካቾች፡- እነ ሙላቱ አንበርብር - ቀርቧል ተጠሪ፡- ወ/ት ታመነች ዮሴፍ መና ወኪል - ቀርቧል።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረው በኮልፋ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀበላ 06 አስተደደር ማሕበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካቾች የስር ከሣሽ ተጠሪ ተከሣሽ ነበሩ አመልካቾች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ በተጠሪ የመኖሪያ ቤት የፔሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሆኑ ግለሰቦች ከፍተኛ የድምጽ ማጉያ በመጠቀም በሚያካሂደት ጩኸት አካባቢውን በማወካቸው በመኖሪያችን ልናርፍ አልቻልንም በሚፈጠረው የድምጽ ብክለት በጤናችን ላይ ጉዲት እያደረሰበን ስለሆነ የድምጽ ብክለቱ ይወገድልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪም ለክሱ በሰጡት መልስ ይህ የሐይማኖት ጥላቻ በመሆኑ በአድማ የቀረበ ክስ ነው። የማንንም መብት ሣንጋፊ መንግስት ለሐይማኖትና ለእምነት ነፃነት የሰጠው ሕገመንገስታዊ መብት እንዱከበርልን ተደርጏ የማምለክ መብታችን ተጠብቆ እያለ ድንጋይ እየተወረወረብን በደል እየደረስብን ነው በማለት ተከራክሯል።
የማህበራዊ ፍ/ቤቱም ጉዲዩን አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ በመመርመር አመልካቾች ያቀረቡትን አቤቱታ አስመልክቶ ሁከት መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሲል የመሰረት ልማት ቴክኒሻን(ባለሙያ) ወደ ስፍራው በመላክ ሁከት እንዲለ በማረጋገጥ ተጠሪዎች በልላው ሰው ላይ ሁከት እየፈጠሩ ህገ-መንግስታዊ መብታችን እየተጠቀምን ነው ማለቱ ሕጉን በተሣሣተ መተርጏም ሆኖ አግኝተነዋል። ስለዚህ በአዋጅ ቁ. 12/96 አንቀጽ 5/3/ መሰረት፣በወንጀል ሕግ 815/1/ የላልችን ስራና ሰላም ማወክ ሆኖ ስላገኘው ተጠሪዎች 100 ብር (መቶ ብር) ይቀጡ መኖሪያ ቤቱ ለተፈቀደለት አላማ ብቻ ይዋል በማለት ወስኗል።
ተጠሪም በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለአ/አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረባቸው ጉዲዩ የቀረበለትም ፍ/ቤት የግራ ቀኙን በማከራከር በጭብጥነት የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን አይቶ መወሰን ስልጣን አለው ወይ?
የሚለውን በማየት ሲወስን የክልል 14 መስተዲደር ደንብ ቁጥር 1/1986 አንቀጽ 10/2/ በመጥቀስ ይህን ደንብ የጣሰ ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው የመንግስት አካል ተገቢውን አስተደደራዊ ውሣኔ እንደሚወሰድበት ከተጠቃሹ ደንብ አንቀጽ 17/1/ሀ/ ላይ ተመልክቷል። ስለዚህ ተጠቃሹን ደንብ የጣሰ በቅድሚያ አስተዲደራዊ ውሣኔ እንዱሰጥበት ማድረግ እንጂ በቀጥታ ክስ በፍ/ቤት ክስ የማይመሰረትበት ነው። በያዝነው ጉዲይም አመልካቾች ይህን ለማድረጋቸው ያቀረቡት ማስረጃ የለም በአስተዲደር አካል ውሣኔ ካልተሰጠ ደግሞ የስር ፍ/ቤት የዲኝነት ስልጣን የለውም በመሆኑም የስር ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። በማለት ሲወስን የአሁን አመልካቾችም በዚሁ ውሳኔ ባለመስማማት ለአ/አበባ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረባቸው ጉዲዩ የቀረበለትም ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ሣይሰማ አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት የፍ/ብሓር ክርክር በመሆኑ በስር ፍ/ቤት በተወሰነው መሰረት በቅድሚያ የሚመለከተው አስተዲደራዊ አካል ውሳኔ መስጠት ይገባል መባለ በአግባቡ ነው በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 ዘግቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚው ውሣኔ ላይ ነው።
አመልካቾች ህዲር 24 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ በአ/አ/ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና በከተማው የከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጽመበት በመሆኑ ሉታረምልን ይገባል በማለት አመልክቷል።
በዚህም መሰረት የተጠሪን እና የአመልካችን የቃል ክርክር በችልት ሰምተናቸዋል።፡ ጉዲዩ በሰበር እንዱታይ የቀረበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ መስተናገድ ያለበት በአ/አ/አስተዲደር አዋጅ ቁ. 12/96 አንቀጽ 5/3/ አንፃር ሣይሆን በአስተዲደር ደንብ ቁጥር 1/86 አንቀጽ 10/2/ እና 17/1/ሀ ነው በማለት የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የማህበራዊ ፍ/ቤትን የመሻራቸውን አግባብነት ለመመርመር ነው።
የሰበር ችልቱም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ የግራ ቀኙ ካሰሙት ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር ማገናዘብ መርምረናል።
በመሆኑም የጉዲዩን አመጣጥ ጠቅለል ባለ መልኩ ስናይ የአሁን አመልካቾች በስር ክሣቸው የፔሮቴስታንት ተከታዮች በተጠሪ መኖሪያ ቤት ከፍተኛ የድምጽ ማጉያ በመጠቀም በሚያካሄደት ጩኸት አካባቢውን በማወክ በድምጽ ብክለት በጤናችን ላይ ጉዲት እያደረሱብን ነው። ይህ ድምጽ ይወገድልን በማለታቸው ምክንያት። የማህበራዊ ፍ/ቤቱም እንደተባለው የድምጽ ብክለት አለ በማለት ተጠሪ (100) ብር (መቶ ብር) እንዱቀጡ ሲወስን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን በማከራከር ጉዲዩ በፍ/ቤት ከመቅረቡ በፉት በመስተዲደር አካል መታየት ነበረበት ስለዚህ የዲኝነት ስልጣን የለህም በማለት የማህበራዊ ፍ/ቤትን ውሳኔ ሲሽር የከተማው የከፍተኛው ፍ/ቤትም በተመሣሣይ ምክንያት የከተማውን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት አጽንቷል።
እንግዱህ በዚህ ጉዲይ በዋናነት ላታይ የሚገባው የስር ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም?
የሚለው ሆኖ አግኝተነዋል በመጀመሪያ ደረጃ የቀበላ የማህበራዊ ፍ/ቤቱ አዋጅ ቁ. 12/96 በአዋጅ ቁ. 31/99 መሻሻለን ከግንዛቤ ሣያስገባ እና ይህ አዋጅ ቁጥር 31/99 ስልጣን ባልሰጠው ሁኔታ ውሣኔ ሰጥቷል የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ይህን በጥልቀት ሣያጤነው ምንም እንኳ የስር ፍ/ቤት ስልጣን የለውም ቢልም ምክንያት ያደረገው የግራ ቀኙ ክርክር መጀመሪያ በአስተዲደራዊ አካል መታየት ነበረበት በሚል ነው። የከፍተኛውም ፍ/ቤት ይህንኑ አጽንቷል።
በመሰረቱ ለክርክሩ መንስኤ አመልካቾች በተጠሪ ድርጊት የጽምጽ ብክለት ጉዲት አድርሶብናል የሚል ሲሆን ጉዲዩም የፍትሐብሕር ክርክር መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም ሉስተናገድ የሚገባውም በፍ/ብ/ሕጉ ቁጥር 1225 መሰረት ነው።
ይህንንም ጉዲይ ለማየት ስልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ አስተዲደራዊ አካል እና የአ/አ ከተማ ፍ/ቤቶች ስልጣን አይደለም።
በመሆኑም ይህ ታልፍ በስር ፍ/ቤቶች መታየቱ አግባብነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
877/00 በቀን 01/9/2000 እና የከተማው ይግባኝ ሰሚ በመ/ቁ. 08015 ቀን 12/2/2001 የተሰጡት ውሣኔዎች ተሽሯል።
የማህበራዊ ፍ/ቤትም ሆነ ከአ/አ/ከተማ ፍ/ቤቶች ስልጣን የላቸውም።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.