No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 19 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ሙለጌታ አባይ - ቀረበ ተጠሪ፡- የፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን - ኑሪዬ አብተው /ነገረ ፈጅ/ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በፋዳራል የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተጀመረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አከፊፈል ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው ለጉባኤው በይግባኝ የቀረበው አመልካች ሲሆን፣ ቅሬታውም በተጠሪ የተጣለብኝ መቀጫ ያለአግባብ ስለሆነ ይነሳልኝ የሚል ነው። ጉባኤው ከተጠሪ የቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ የመቀጮውን መጠን ዝቅ በማድረግ ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ የጉባኤውን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በዚህ ደረጃም የተሰማ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ መቀጮን በተመለከተ በሚቀርበው ክርክር /ይግባኝ/ ላይ ስልጣን የለውም የሚል ምክንያት በመስጠት የጉባኤውን ውሳኔ ሽሮአል። የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት አመልካች ያቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
የሰበር ችልቱ አመልካች ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረቡለትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቶአል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመቀጮ ላይ በሚነሳው ክርክር ላይ ስልጣን የለውም በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው።
አንደምንመለከተው አከራካሪው ነጥብ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በዋናው ግብር ላይ የሚጣለውን መቀጫ በመቃወም በሚቀርበው ይግባኝ ላይ ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለው ነው። በሰበር መ. በቀረበው ክርክር በአሁኑ በተያዘው መዝገብ የተነሣው ጭብጥ አከራካሪ ስለነበር የሰበር ችልቱ ለሕጉ ትርጉም በመስጠት የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመቀጮ እና ወለድ ላይ የሚቀርበውን ይግባኝ አይቶ የመወሰን ስልጣን አለው በማለት ውሳኔ ሰጥቶአል። በዚህ አይነት የሰበር ችልቱ የሚሰጠው ውሳኔ (የሕግ ትርጉም) በችልቱ እስካልተለወጠ ድረስ አስገዲጅ እንደሚሆን የፋዳራል ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁ 454/97 በአንቀጽ 2(4) ተደንግጎአል።
ስለዚህም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 21 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ. የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመቀጮ እና ወለድ ላይ የሚቀርበውን ይግባኝ የማየት ስልጣን አለው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.