No summary available.
ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሻምሺ ዩኑስ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ኑሪያ ማሚ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 16/99 የካቲት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት መጋቢት 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በድሬዲዋ ናኢባ ፍርድ ቤት ነው። በድሬደዋ ናኢባ ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ቀርባ ሟች አባቴ በድሬደዋ ከተማ ቀበላ ዐ8 በአምስት መቶ ካሬ ሜትር ባለው ቦታ ላይ አመልካች ቦታውን እንድትለቅ ስትጠየቅ ለመልቀቅ ተስማምታ ትንሽ ቤት ሰርታ ትኖር ነበር፤ ቦታውን የያዘችው የዛሬ ሰባት ዓመት ሲሆን ወላጅ አባቴ ከሞተ በኋላ በቦታው ላይ ግንባታ ለማካሄድ ቦታውን እንድትለቅልኝ ስጠይቃት እንቢ ስላለችኝ ቦታውን እንድትለቅ እንዱወሰንልኝ በማለት ክስ ያቀረበች ሲሆን፣ የአሁን አመልካች በተጠሪነት ቀርባ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት የመደበኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ የይግባኝ መቃወሚያ አቅርበዋል። አመልካች በፍሬ ጉዲይ እረገድ ቦታው በአዋጅ ቁጥር 47/1967 የተወረሰ ነው የሚለና ላልች ክርክሮችን አቅርበዋል።
የናኢባ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበችውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማለፍ የፍሬ ጉዲይ ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ አመልካች ይዞታውን ለተጠሪ እንድትለቅ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለድሬዲዋ ፋዳራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ከተከራከሩ በኋላ የከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤቱ የሥረ ነገር ሥልጣንን በተመለከተ የቀረበውን የይግባኝ ቅሬታ በማለፍ በፍሬ ጉዲይ በኩል አጣርቶ እንዱወስን ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 መሰረት መልሶ ልኮለታል። ሆኖም በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አቅርባ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ የናኢባ ፍርድ ቤት ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የማያንስ ስልጣን አለው ካለ በኋላ በፍሬ ጉዲይ ረገድ፣ የድሬደዋ ፋዳራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የናኢባ ወረዲ ፍርድ ቤትን ውሣኔ በማጽደቅ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች ይህ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት፤ ተጠሪ ያቀረባቸው ክስ የወላጅ አባቴን ይዞታ ታስረክበኝ የሚል ሲሆን እኔ ደግሞ 1982 ዓ.ም. ጀምሮ በቦታው ላይ ቤት ሰርቼ እየኖርኩ ያለሁ መሆኔን ገልጬ የናኢባ ፍርድ ቤት ይዞታን አስመልክቶ የሚነሳ ክርክርን የማየት ሥልጣን የለውም በማለት ያቀረብኩትን መቃወሚያ አላግባብ አልፍና በይዞታ ጉዲይ አከራክሮ ወስኗል፤ ስለዚህ ያለበቂ ማስረጃ አከራክሮ ውሣኔ የሰጠ በመሆኑ፣ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤትም የተፈፀመውን የሕግ ስህተት ያላረመ በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
ተጠሪ በበኩሎ ክርክሩ በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተደረገው በአመልካች ፈቃደኝነት ነው፤ ስለዚህ የሸሪዓ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም የሚል ክርክር አቅርበዋል። አመልካች በጽሁፍ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታዋን የሚያጠናክር ክርክር አቅርባለች።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥ ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን፣ እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የሸሪዓ ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተፈጠረውን የይዞታ መብት ጥያቄ አይቶ የመወሰን የሥረ ነገር ስልጣን አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከድሬደዋ ናኢባ ፍርድ ቤት፣ ከከፍተኛ ሸረዓ ፍርድ ቤትና ከጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የውሣኔ ግልባጭ ለመረዲት እንደቻልነው ጉዲዩ ይዞታ ክርክር ነው። ተጠሪ ቤቱ የሟች ወላጅ አባቷ መሆኑንና አመልካች ቤት የሰራችው በአባቷ ፈቃድ ልቀቂ ስትባል ለመልቀቅ ተስማምታ መሆኑን በመግለጽ የምትከራከር ሲሆን፣ አመልካች በበኩሎ ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ ይዞታው የእሷ መሆኑን በመግልጽ የይዞታ ክርክርን የናኢባ ፍርድ ቤት ማየት የለበትም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርባለች።
የፋዳራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት የወል የዲኝነት ስልጣን በምን ጉዲዮች ላይ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 188/1992 በአንቀጽ 4 ተደንግጓል። በዚህ የሕግ ድንጋጌ መሰረት በፋዳራል በማናቸውም ደረጃ የሚገኙ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን አይተው የመወሰን የዲኝነት ሥልጣን የሚኖራቸው፡- -በማንናቸውም የጋብቻና የፍች፣ የቀለብ አወሳሰን፣ አካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ሞግዚትነት እና የቤተሰብ ተዛምድ ላይ የሚነሱ ጉዲዮችን አስመልክቶ ጥያቄ ያስከተለው ጋብቻ በእስልምና ሀይማኖት ሥርዓት መሰረት የተፈፀመ የሆነ እንደሆነ ወይም ባለጉዲዮቹ በእስልምና ሀይማኖት ሥርዓት ለመዲኘት አቅደው እንደሆነ፤
የእውቅና ስጦታ /ሂባ/፣ ውርስ ወይም ኑዛዜ ጉዲዮችን በተመለከተ አውራሹ ወይም ስጦታ አድራጊ ወይም ተናዛዥ ሙስሉም የሆነ እንደሆነ ወይም ሟች በሞተበት ሰዓት ሙስሉም ሆኖ የሞተ እንደሆነ፤
ከላይ በተገለጹት ጉዲዮች ላይ የሚቀርቡ ክሶችን ኪሣራ የሚመለከት ሲሆን እንደሆነ ከአዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 4 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ለመረዲት እንችላለን።
ከዚህ ውጪ በሆኑ ጉዲዮች ላይ የናኢባ ፍርድ ቤት፣ የከፍተኛው ሸሪዓ ፍርድ ቤትም ሆነ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ክርክር የመስማትና ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን የላቸውም። የያዝነው ጉዲይ የይዞታ ክርክር ጉዲይ ነው። አመልካችና ተጠሪ የአንድ ሰው ወራሾች በመሆናቸው ምክንያት የቀረበ የውርስ ንብረት ክፍያ ጥያቄ አይደለም። ስለሆነም ቦታው የማን ይዞታ ነው የሚለውን ጉዲይ አከራክረው የመወሰን የዲኝነት ሥልጣን ያላቸው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት መደበኛ ፍርድ ቤቶች ናቸው። ከዚህ አንፃር ስናየው የፋዳራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የድሬደዋ ናኢባ ፍርድ ቤት ቦታውን አስመልክቶ ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያላነሰ ሥልጣን አለው በማለት መወሰኑ የፋዳራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የወጣው አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 4 ንዐስ አንቀጽ 1 ላይ የተመለከቱትን መሰረታዊ ድንጋጌዎች ባለማገናዘብ የተሰጠ ሆኖ ስላገኘነው መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት፣ የፋዳራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የድሬዲዋ ናኢባ ፍርድ ቤት የይዞታ ጉዲይ አከራክረው የመወሰን የዲኝነት ስልጣን የላላቸው በመሆኑ ውሣኔያቸው ሙለ በሙለ ተሽሯል።
ይህ ውሣኔ ተጠሪ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ አቅርባ ከመጠየቅ የሚገድባት አይደለም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.