No summary available.
መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው ዓልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
ይህ ክርክር ላቀርብ የቻለው አመልካቾች ሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው የኦሮሚያ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 26/98 ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም እና ሚያዝያ 08 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጣቸው ውሳኔዎች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመባቸው በመሆናቸው ይሻሩልን በማለታቸው ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በኢሉባቡር ዞን ከፍተኛ ሸሪዓ ፍ/ቤት ሲሆን በዚሁ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካቾች ተከሳሾች፣የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን፣የስር ከሳሹ ነሐሴ 09 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት ክስ አጭር ይዘቱ አንደኛዋ ተጠሪ ሚስቴ ሆና እያለች ሁለተኛው ተጠሪ የሸሪዓን ህግ በመጣስ ስላገባት በጋብቻ ላይ ጋብቻ በመፈፀም ጥፊት ስለፈፀመ በህግ ፉት ቀርቦ የጥፊተኝነት ውሳኔ ይሰጠው የሚል ነው። ስር ተከሳሾች በቀነ ቀጠሮው ባይቀርቡም የስር ፍ/ቤቱ ሐምል 6 ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ብይን ጉዲዩ ወንጀል ነክ በመሆኑ አከራክሬ የመወሰን ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። ስር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪም በስር ፍ/ቤቱ ውሳኔ ላይ ቅሬታ በማሳደር ጉዲዩን በይግባኝ እንዱታይላቸው ለኦሮሚያ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አቅርበውት ፍ/ቤቱም ተከሳሾቹ በላለበት በመ/ቁ 26/98፣ሚያዝያ 08/1999 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ አቶ ሙሑዱን ጀማል ወ/ሮ ሳሉያ ኢብራሂም የሐጂ ሰማን ኢሳ ህጋዊ ባለቤት መሆኗን እያወቀ ስላገባት በጋብቻ ላይ ጋብቻ በመፈፀም ጥፊት ፈጽሟል በማለት ስር ተከሳሾቹ ለከሳሹ ብር 1700 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር) እንዱከፍለትና በሚመለከተው አካል በወንጀል የመክሰስ መብቱ በመጠበቅ ወስኗል።
ይህ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላም የአሁኑ አመልካቾች ታህሳስ 23 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78/1/2/ መሰረት ባለበት ክርክሩ እንደገና እንዱካሄድ ፍርደን ለሰጠው የኦሮሚያ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት አመልክተው ከተፈቀደላቸው በኋላ ያቀረቡት ክርክር በጋብቻ ላይ ጋብቻ እንዲልፈፀሙ፣አቶ ሙሐዱን ወ/ሮ ሳሉያን ያገባት ቀደም ብል ከሐጂ ሰማን ኢሳ ጋር የነበራትን ጋብቻ /ኒካ/ ከፈረሰ በኋላ እንደሆነና ማስረጃም እንዲላቸው የሚገልጽ ሲሆን ይግባኝ ባዩ ሐጂ ሰማን ደግሞ ከወ/ሮ ሳሉያ ጋር የነበረኝ ጋብቻ በሸሪዓ ፍ/ቤት አልፈረሰም የሚል ክርክር አቅርበዋል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤቱም በኦ/ጠ/ሸሪዓ ፍ/ቤት መ/ቁ. 26/98፣ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ተከሳሾቹ በጋብቻ ላይ ጋብቻ አልፈጸምንም በማለት ያቀረባቸው የጽሁፍ ማስረጃዎች ማለትም የዘመድ ዳኞች በ27/08/1990 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና የኢልባቦር ዞን የእስልምና ጉዲዮች ጉባኤ በ01/02/1993 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ሲታዩ እነዚህ አካላት ጋብቻውን የማፍረስ ስልጣን የላቸውም በማለት ተከሳሾቹ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ፈጽመዋል በማለት ቀደም ብል ማለትም በመ/ቁ. 26/98፣ሚያዚያ 08/1999 ዓ.ም ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ ተመልሶ አጽድቆታል።
ከላይ የሰፈረውን ውሳኔ በመቃወምም የአሁኑ አመልካቾች ሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም በጋብቻ ላይ ጋብቻ አልፈፀምንም፤ጋብቻችንን የፈጸምነው በአንደኛ አመልካችና በተጠሪው መካከል የነበረው ጋብቻ በህጋዊ አካል ከፈረሰ በኋላና ይህንን መሰረት በማድረግ የኢልባቦር ዞን የእስልምና ጉዲዮች ጉባኤ በቁጥር DHIIL 62/3/3-1/93 ጥቅምት 01/1993 ዓ.ም በፃፈው ደብዲቤ ወ/ሮ ሳሉያ ኢብራሂም ጋብቻዋ የፈረሰ በመሆኑ የፈለገችውን ማግባት እንደምትችል ማረጋገጫ ከሰጠ በኋላ እንደሆነ፤በጋብቻ ላይ ጋብቻ ፈጽማችኋል በማለት በብር 1700 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር) በወንጀል እንድንቀጣ መወሰኑ መዝገቡን በጥልቀት ሳይመረምር ከስልጣኑ ውጭ እንደሆነ በመግለጽ በኦ/ጠ/ሸሪዓ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይሻርልን የሚል ነው።
ተጠሪው ለቃል ክርክር ተዘጋጅተው እንዱቀርቡ መጥሪያው ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ፍ/ቤቱ ጥር 14 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ አዞ የተካሄደ ያለ በመሆኑ ተጠሪው መልስ አልሰጡም።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ እየተዘረዘረ በመጣው መልኩ ከተገነዘበ በኋላ አመልካቾቹ ጋብቻ የፈፀሙት አንደኛዋ አመልካችና ተጠሪው መስርተውት የነበረው ጋብቻ በህጋዊ መንገድ ሳይፈርስ በነበረበት ሁኔታ ነው ወይስ አይደለም? የሚል መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ አንደኛዋ ተጠሪ ከእርሳቸው ጋር ያላት ጋብቻ በሸሪዓ ህግ ሳይፈርስ ሁለተኛው ተጠሪ እንዲገባትና ይህ አድራጏትም በጋብቻ ላይ ጋብቻ መፈጸም ስለሆነ አመልካቾች እንዱቀጡለት የሚጠይቅ ሲሆን አመልካቾቹ ደግሞ ቀደም ብል በተጠሪው እና በአንደኛ አመልካች መካከል የነበረው ጋብቻ በአግባቡ ከፈረሰ በኋላ እንጂ ጋብቻው ሳይፈርስ እንዲልተጋቡ መልሰዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያከራከረው የኢልባቦር ዞን ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ጉዲዩ የወንጀል ክርክር ስለሆነ ስልጣን የለኝም ቢልም ጉዲዩን በይግባኝ ያስተናገደው የኦሮሚያ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ግን በአንደኛዋ አመልካችና በተጠሪው መካከል ቀደም ብል የተመሰረተው ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ሁለተኛው ተጠሪ አንደኛዋን ተጠሪ በማግባት በጋብቻ ላይ ጋብቻ መፈፀሙን በማስመር በብር 1700(አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር) እንደቀጣቸው ነው። ሽማግላዎች አፊትተውናል ፍርድ ቤትም ተቀብልታል፣ቀጥልም የኢልባቦር ዞን የእስልምና ጉዲዮች ጉባኤ አንደኛዋ አመልካች የፈለገችውን ማግባት እንደምትችል በደብዲቤ ገልፆላታል የሚል ክርክር ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የላቸውም በማለት አልፍታል። ይሁን እንጂ ቀደም ብል በተጠሪውና በአንደኛዋ አመልካች መካከል የነበረው ጋብቻ እንዱፈርስ ጥያቄ የቀረበለት የዱደ ላል ወረዲ ፍ/ቤት ጉዲዩ ወደ ሸማግላዎች መርቶት ሽማግላዎቹ ተጋቢዎቹን ለማስታረቅ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ በመቅረቡ ጋብቻው እንዱፈርስ አስተያየታቸውን ተመልሰው ለወረዲ ፍ/ቤቱ ካቀረቡለት በኋላ የተጠቀሰው ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 48/94፣ሚያዚያ 28 ቀን 1990 ዓ.ም በዋለው ችልት የሽማግላዎቹን አስተያየት ተቀብል ፍቺውን እንዲፀደቀ መዝገቡ ያስረዲል፤የመጀመሪያው ጋብቻ የፍቺ ሂደት በዚህ መልክ ከተጠናቀቀ በኋላ እና የኢልባቦር ዞን እስልምና ጉዲዮች ጉባኤ በቁ. DHIILU 62/3/3-1/93 ጥቅምት 01/1993 ዓ.ም በፃፈው ደብዲቤ አንደኛዋ አመልካች ከዚህ በኋላ የፈለገችውን ሰው ማግባት እንደምትችል ገልጿል። የአሁኑ ሁለተኛው አመልካች እነዚህ ሂደቶች ማለትም የመጀመሪያው ጋብቻ ስልጣን ባለው የወረዲ ፍ/ቤት አማካኝነት መፍረሱን አረጋግጠው አንደኛዋ አመልካች እንዲገቡ ነው። የእስልምና ተከታይ የሆኑ ተጋቢዎች ጋብቻቸው እንዱፈርስ ወደ መደበኛ ፍ/ቤት ወይም ሁለቱም ከፈቀደ ደግሞ ወደ ሸሪዓ ፍ/ቤት አስቀርበው እንደምርጫቸው ሉያፈርሱት እንደሚችለ እየታወቀ የኦሮሚያ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት የዱደ ላል ወረዲ መደበኛ ፍ/ቤት ቀደም ብል የሰጠውን የፍቺ ውሳኔ ወደ ጏን በመተው በአንደኛዋ አመልካችና በተጠሪው መካከል የነበረው ጋብቻ አልፈረሰም፤አመልካቾች በጋብቻ ላይ ጋብቻ ፈጽመዋል ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፤ ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 26/98፣ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
አመልካቾቹ ጋብቻ የፈጸሙት ቀደም ብል በአንደኛዋ አመልካችና በተጠሪው መካከል የነበረው ጋብቻ በዱደ ላል ወረዲ ፍ/ቤት በአግባቡ ከፈረሰ በኋላ በመሆኑ አመልካቾቹ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ባለመፈጸማቸው የተላለፈባቸው የገንዘብ ቅጣት ተገቢ አይደለም ብለናል።
ግራና ቀኙ ወገኖች በዚህ ፍ/ቤት ላካሄደት ክርክር ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.