No summary available.
የካቲት 3 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን - ነ/ፈጅ አቶ ዲንኤል ጥበቡ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- እነ ወ/ር አስረሳች ወርቅነህ (87 የጉምሩክ ፕሉሶች) ጠበቃ ሙለጌታ ወንድማገኘሁ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው የጉምሩክ ፕሉሶች ወደ ስራ እንመለስ የሚል ክርክርን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሳሾች የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ሲሆኑ አመልካች ተከሳሽ ነበር። እሱም በድርጅቱ ከተራ ወታደርነት እስከ መኮንንነት ተመድበን ከምንሰራበት በማይታወቅ ሁኔታ ሰኔ 15 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ያሰናበተን ከጉምሩክ ፕሉሶች መተዲደሪያ ደንብ ቁጥር 4/96 ውጪ በመሆኑ ሕገ-ወጥ ነው እንዱባልና ወደ ስራ እንድንመለስ እንዱወሰን የሚል ነው። አመልካች በሰጠው መልስ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን የመዲኝት ስልጣን የለውም በጉምሩክ አዋጅ የመዋቀር ማስተካከያ በማድረግ የሰው ኃይል ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ስልጣን ተሰጥቷል።
መመሪያው የዱስፑሉን እርምጃን የሚመለከት እንጅ የመዋቅር ማስተካከልን የሚከለክል አይደለም በማለት ስንብቱ ሕጋዊ መሆኑን በማስመልከት የመቃወሚያና በአማራጭ የፍሬ ነገር ክርክር በማቅረብ ተከራክሯል። ግራ ቀኙን ያከራከረው የመጀመሪያ ፍ/ቤት ወደ ቀድሞ ስራቸውና ደመወዛቸው እንዱመለስ ሲል ወስኗል። ከፍተኛ ፍ/ቤትም በመ/ ሐምል 1 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የመጀመሪያ ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናቱ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ሐምል 7 ቀን 2000 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው አቤቱታ መሰረት በማድረግ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት የዲኝነት ስልጣን አለው ወይንስ የለውም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ታዝዞ ተጠሪዎች ቀርበው እንዱከራከሩ ተደረጓል። በዚህ መሰረት ግራ ቀኙ ክርክር አካሄደዋል።
እኛም የግራ ቀኙን ክርክር አግባብ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
የአመልካች ዋና ክርክር በአዋጅ ቁጥር 60/1989 አንቀጽ 8/2/መ እና በአዋጅ ቁጥር 368/1995 በተሻሻለው መሰረት የጉምሩክ ፕሉሶች የሚተዲደሩት የፋዳራል ፕሉስ ኮሚሽን በሚተዲደርበት አኳኋን ነው። በዚህ ዓይነት በተሰጠው ውሳኔ ላይ ፍ/ቤት ማየቱ ተገቢ አይደለም በማለት ነው። ተጠሪዎች ደግሞ ለሚደርሰው የመብትና የፍትህ መጓደል አቤቱታ የሚቀርብበት በሕግ ስልጣን የተሰጠው አካል ባለመኖሩ መብትና ጥቅማችን የሚያስከብርና ሕጏችን በመተርጏም የሚወሰንልን መደበኛ ፍ/ቤት ብቻ ስለሆነ ክሱን ተቀብል መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት ተከራክረዋል።
በአዋጁ ቁጥር 368/95 እንደተመለከተው የጉምሩክ ፕሉስ ኃይል የሚተዲደረው የፋዳራል ፕሉስ ኮሚሽን አዋጅና ደንብ ተከትል በሚወጣው መመሪያ መሰረት እንደሆነ በግልጽ ተመልክቷል። በእነዚህ ድንጋጌዎች በግልጽ ባልተመለከቱ ጉዲዮች ስንብት ቢፈፀም በፍ/ቤት እንደሚታይም አልተመለከቱም። የበታች ፍ/ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው በመመሪያ ቁጥር 4/1996 ከተመለከተው የጉምሩክ ፕሉስ አገልገልት ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ውጪ በሆነ ሁኔታ ከመዋቅር ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ከመጣው የጉምሩክ ፕሉስ ኃይል አደረጃጀትን የሚመለከት ጉዲይ እንጂ በመመሪያው ላይ ስለስንብት የተመለከተውን ምክንያት የሚሽር ባለመሆኑ ስንብቱ ከመመሪያው ውጪ ነው በማለት ነው። በመመሪያው ከተመለከቱ ምክንያቶችም ሆነ በመመሪያው ከተመለከቱ ምክንያቶች ውጪ የጉምሩክ ፕሉስ የስራ ስንብት ጉዲይ ላታይ የሚችለው የፋዳራል ፕሉስ በሚተዲደረው ስርአት እንደሆነ በአዋጁ በግልጽ ተመልክቷል። ይህ ከሆነ ዘንዲ የጉምሩክ ፕሉሶች የስንብት፣በስራ ላይ ማሰማራትም ሆነ የዱስፑሉን ውሳኔ ጉዲዮች በቀጥታም ሆነ በይግባኝ በፍ/ቤት በዲኝነት ላታይ የሚችልበት ስርአት በአዋጅ ወይም በመመሪያው ባልተመለከተበት ስንብቱ ሕጋዊ ነው ወይንስ ከሕግ ውጪ ነው በማለት በፍ/ቤት ጭብጥ ተይዞ ክርክር ሉካሄድበትና ውሳኔ ላሰጥ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም።
በመሆኑም የበታች ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ብቸኛ ስልጣን ያለው ፍ/ቤት ነው በማለት ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክስና ክርክር ተቀብል ስንብቱ ከሕግ ውጪ ነው ወደ ስራ መልሷቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ በአዋጅ በግልጽ የፋዳራል ፕሉስ በሚተዲደረው ስርአት (executive provocative) የሚታየውን ጉዲይ ያለስልጣኑ ለጥጦ በመተርጏም በፍ/ቤት የሚታይ ጉዲይ በማድረግ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ማረም ሲገባው በማጽናት የሰጠው ውሳኔ ከላይ በተመለከቱ ምክንያቶች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ14/5/2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ1/11/2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጡ ውሳኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም ብለናል።
ተጠሪዎች ወደ ስራ ሉመለሱም ሆነ ደመወዝ ሉከፈላቸው አይገባም ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የቻቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል።
No topics extracted.