No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 37ዐ16 የካቲት 3 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ማሞ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በተከሣሽ ድርጅት በበላይ ገንዘብ ያዥነት /senior teller/ በማገልገል ላይ ሳለሁ በ1ዐኛው ኀብረት ስምምነት መሰረት የሥራ መደቡ መጠሪያ ስያሜ ተለውጦ ኦፉሻል 3 የሚል መጠሪያ በመሰጠቱ ምክንያት ለሥራ መደቡ ማግኘት የሚገባኝን ልዩ ጭማሪ ብር 219 /ሁለት መቶ አሥራ ዘጠኝ ብር/ ተከሣሽ ከልክልኛል። ስለሆነም ተከሣሽ ከ24/5/99 ዓ.ም. ጀምሮ ማግኘት የሚገባኝን ልዩ ጭማሪ በመክፈል ወደ ቀድሞው የበላይ ገንዘብ ያዥነት የሥራ መደብ እንዱመልሰኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተከሣሽም /የአሁን አመልካች/ ቀርቦ በሰጠው መልስ ከሣሽ የሚሰሩበት የሥራ ደረጃ 14 ሲሆን በዚህ ደረጃ የሚከፈለው ደመወዝ አሁን እየተከፈላቸው ካለው ደመወዝ የሚያንስ ሲሆን የተሻለ ደመወዝ እየተከፈላቸው ባለበት ሁኔታ ልዩነት ብር 219(ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ብር) ሉከፈለኝ ይገባል ያለት በተገቢው አይደለም። በከሣሽ ላይ የሥራ ለውጥ ያልተደረገ ሲሆን ተደርጓል ቢባል እንኳን የከሣሽ የትምህርት ዝግጅት ማነስ የሥራ አፈፃፀም ዝቅተኝነት፣ የደንበኞች ቅሬታና የቅርብ ኃላፉዎች ግምገማ ተጨምሮበት በባንኩ የአደረጃጀት የአሰራር ለውጥ /BPR/ መሰረት ከሣሽ እንዱሰሩ የታመነበት አሁን እየሰሩ ያለበት የሥራ መደብ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ማስረጃ ሰምቶ በተከሣሽ መ/ቤት ሥራ የተቋቋመው የመሰረታዊ የአሰራር ለውጥ /BPR/ ኮሚቴ አባላት ቀርበው በሰጡት የምስክርነት ቃል ከሣሽ ለነበሩበት የሥራ መደብ ብቃት እንደላላቸው የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ ቢሆንም የግል ማኀደራቸውን ፍ/ቤቱ አስቀርቦ እንደተመለከተው መልካም የሥራ አፈፃፀም እንደነበራቸው ስለሚያሳይ የኮሚቴው ውሣኔ በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ባመሆኑ ከሣሽ ወደ ቀድሞ ከፍተኛ ገንዘብ ያዥነት የሥራ መደብ ሉመለሱ እና የመደቡ የደመወዝ ልዩነትም ሉከፈላቸው ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሣሽ በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የላለው ነው በሚለት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ ተጠሪ ወደ ቀድሞው የሥራ መደብ ሉመለሱ ይገባል ተብል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ አግባብነቱ ተጠሪ ባለበት ሉጣራ እንደሚገባ በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤቱታው እንደሚከተለው ተመርምሯል።
በቅድሚያም ችልቱ የተመለከተው የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው መሆኑን በተመለተ ነው።
ተጠሪ በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በክስ አቤቱታቸው ዲኝነት የጠየቁት ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ቀድሞ ስሰራበት ወደነበረው የሥራ መደብ እንድመለስና ለመደቡም የተሰጠው ልዩ ጭማሪ እንዱከፈለኝ በማለት ነው።
የአሰሪና ሰራተኛን ግንኙነት በሚገዛው በአዋጅ ቁጥር 377/96 ለወልም ሆነ ለግል የሥራ ክርክር የተሰጠ ትርጉም ባይኖርም ነገር ግን አንድ የሥራ ክርክር የወል የሥራ ክርክር ወይንም የግል የሥራ ክርክር ነው ለማለት የሰራተኛው ቁጥር እንደ መለያ መስፈርት ሉያገለግል እንደማይችል ከአዋጁ አንቀጽ 138 እና 142/1/ ዝርዝር ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ክርክሩ የወል ነው ለማለት የጋራ የሆነን የሰራተኞችን መብትና ጥቅም ጋር ግንኙነት ያለው ማለትም የደመወዝም ሆነ የላላ ጥቅም፣ የቅጥርም ሆነ የዕድገት አሰጣጥ፣ የዝውውርም ሆነ የሥልጠና ከመሣሰለት ጋር ግንኙነት ኖሮት በጋራ በሆነ ሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አዎንታዊም ሆነ አለታዊ ውጤት በሚያስከትል ጊዜ እንደሆነ ከፍ ብል ከተጠቀሰው አንቀጽ 142/1/ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ የተጠሪ ጥያቄ ወደ ቀድሞ የሥራ መደቤ እንድመለስና ለመደቡም የተሰጠው ልዩ ጭማሪ እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል እንደመሆኑ መጠን የዚህ ዓይነቱ ጥያቄ በአንቀጽ 142/1/ሀ/ እና /ሰ/ ሥር የሚሸፈንና የወል የሥራ ክርክር ተብል የሚመደብ ነው። ክርክሩ የወል ከሆነ ደግሞ ጉዲዩ የሚታየው በአስማሚ ወይም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ አማካኝነት እንጂ በፍ/ቤት በኩል ስላልሆነ የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በዚህ ሁኔታ ጉዲዩን ተቀብል ውሣኔ መስጠቱ በአንቀጽ 138/1/ ሥር ከተሰጠው የሥረ-ነገር ሥልጣን ውጭ እንደሆነ መገንዘብ ተችሎል።
ስለሆነም የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በዚህ መልኩ የሰጠው ውሣኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 21652 በ5/5/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እንደዚሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 63054 በ26/7/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም ተብል ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.