No summary available.
ጥር 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው በላቸው አንሺሶ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ንግሥት ኃይላ - ተወካይ አቶ ኃይላ በልሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ለገሰ ዓለሙ ጠበቃ - አቶ ብስራት መኯንን ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለመርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው አመልካች የፋዳራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቀ ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች በከፍተኛው ፍርድ ቤት በከሣሽነት ቀርባና ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሣሥረው ሲኖሩ በአገር ውስጥና በአሜሪካን ሀገር የጋራ ሀብት ያፈሩ መሆኑን በመግለጽ፣ ጋብቻችን በፍች ፈርሶ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአገር ውስጥ ያለንን የጋራ ሀብት አስመልክቶ ክርክራችንንና ማስረጃችን በመመርመር ውሣኔ የሰጠ ሲሆን በአሜሪካን አገር የሚገኘው ንብረት በተመለከተ ስልጣኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው በማለት ጥያቄን ያልተቀበለኝ ለመሆኑ በውጭ ያለንን የጋራ ንብረት አስመልክቶ አከራክሮ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርባለች። ተጠሪ በተከሣሽነት ቀርቦ የሁለታችንም በዜግነት ኢትዮጵያዊያን ነን። ንብረቱ በአሜሪካን አገር መኖሩ የዓለም አቀፍ የግል ሕግ ጥያቄ የማያስነሣና የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የሥረ-ነገር ስልጣን የማያሣጣ ነው በማለት ተከራክሯል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ጉዲዩ የዓለም አቀፍ የግል ሕግ ጥያቄ አያስነሣም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት እንደላለው ከገለፀ በኋላ በአሜሪካን አገር የተገኘ ንብረት ብቻ ተነጥል በዚህ ፍርድ ቤት የሚያስተናግድበት ሥርዓት የለም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን ይግባኝ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባታል። አመልካች ያቀረብነው የጋራ ንብረት ጥያቄ በተመለከተ በአገር ውስጥ የሚገኘውን ሀብት በተመለከተ አከራክሮ ከወሰነ በኋላ በአሜሪካን አገር የተጠራቀመውን 9713.12 ድላር /ዘጠኝ ሺ ሰባት መቶ አስራ ሶስት ድላር ከአስራ ሁለት ሣንቲም/ የክፍፍል ጥያቄ በተመለከተ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ ጥያቄ የሚያስነሣ በመሆኑ ስልጣን ባለው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይታይ በማለት መዝገቡን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልኳል። ሆኖም ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን የተላከለትን የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ በመዝጋት ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ አድርጓል። እኔም አዱስና ራሱን የቻለ ክስ ውጭ ያለውን ገንዘብ አስመልክቶ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ሣቀርብ አላግባብ ውድቅ ሆኖብኛል። በዚህ አይነት ሁኔታ ያቀረብኩትን የመብት ጥያቄ ውሣኔ ሣይገኝ እየተጉላላሁ ያለሁ በመሆኑና ይኸም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ጠይቃለች።
ተጠሪ በበኩለ አመልካች ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡትን መዝገብ ዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ሲመልስ ይግባኝ ማቅረብ ሲገባት እንደ አዱስ ክስ ማቅረቧ ተገቢ አይደለም ሕጋዊ ሥርዓትን የተከተለ አይደለም። ስለዚህ የመጨረሻ ውሣኔ ባገኘ ጉዲይ ላይ እንደገና ክስ ማቅረቧ ተገቢ ባለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ፍርድ ቤቶቹ ሥልጣኑ የአንተ ነው እየተባባለ ጉዲዩን አንጠልጥለው ከማስቀረታቸው ውጭ በጉዲዩ ላይ የተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ የለም። እንደ አዱስ ክስ ማቅረቤ ተገቢ ነው በማለት በመልስ መልሱ ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ መነሻና አመጣጥ በሰበር አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው ፡ 1.ጉዲዩ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ ነው ወይስ አይደለም?
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ የአመልካችና የተጠሪ ጋብቻ በፍች እንዱፈርስ የወሰነው የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ በአገር ውስጥ ያላቸውን የጋራ ሀብት አስመልክቶ ያቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ ውሣኔ የሰጠ ሲሆን በአሜሪካን አገር አለ ስለተባለው ሀብት ሥልጣኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ውሣኔ ይሰጥበት በማለት መዝገቡን ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልኮታል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት በበኩለ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የላከለትን መዝገብ አመልካችን ሣይጠራ በከፉል በሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ያገኘ ጉዲይ ተቀብዬ የማስተናግድበት ሥርዓት የለም በማለት መዝገቡን ዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት የመለሰው መሆኑ ፍርድ ቤቱ ጥር 16 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ለመረዲት ይቻላል። አመልካች በውጭ አገር አለ ያለትን የጋራ ሀብት አስመልክቶ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 በተሰጠው ስልጣን መሰረት እንዱወሰንላቸው አዱስ ክስ ያቀረቡ ሲሆን ይህንንም ፍርድ ቤቱ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በግማሽ ጉዲይ ላይ አይቶ ውሣኔ የሰጠ በመሆኑ እኔ ከፉለን ጉዲይ አይቼ የምወስንበት ሥርዓት የለም በማለት ዘግቶታል።
ከዚህም የምንረዲው አመልካች በአሜሪካን አገር ያለው የጋራ ሀብት እንዱካፈል ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበችው ክስና ጥያቄ የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ጉዲዩ ዓለም አቀፍ የግለሰብ ሕግ ጥያቄ ሉያስነሣ ስለሚችል ይህንን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገቡን የላከው መሆኑንና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ በአገር ውስጥ ስላለው ሀብት ውሣኔ በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የተሰጠ በመሆኑ በውጭ አገር የሚገኘውን ሀብት ብቻ አይቼ በከፉል የምወስንበት ሥርዓት የለም በማለት በመወሰኑ ጉዲዩ በእንጥልጥል ላይ ያለና የመጨረሻ ውሣኔ ያላገኘ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑም ተጠሪ ጉዲዩ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ ነው በማለት የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካች በውጭ አገር ያለው የጋራ ሀብት እንድትካፈል ያቀረበችው ጥያቄ አይቶ የመወሰን የሥረ ነገር ስልጣን እንደላለው የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ብይን ከሰጠ በኋላ የአመልካችንና የተጠሪን ክርክር የተሰማበትን የመዝገብ ቁጥር ዐዐ289 ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ልኮለታል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንን የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ በሆነ ፊይል ከሸፈነ በኋላ በአመልካች ጥያቄ በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ትእዛዝ የተላለፈለትን ጉዲይ አመልካችን ሣይጠራ ጉዲዩ የሚያስተናግድበት ሥርዓት የላለ መሆኑን በመግለጽ የሥር ፍርድ ቤትን መዝገብ የራሱ መዝገብ አካል በማድረግ ወደ መዝገብ ቤት እንዱመለስ ትእዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ሑደት ያልተጠራችው ተጠሪ ያቀረበችውን ክስም ውድቅ አድርጓል።
ከዚህም የምንረዲው ሁለቱ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን እኔ አላየውም የሚለበትን የተለያዩ ምክንያቶች በመጥቀስ በሰጡት ትእዛዝ የአመልካች ጥያቄ በእንጥልጥል የቀረ መሆኑን ነው። ማንኛውም ሰው በዲኝነት ሉወስን የሚገባው ጉዲይ በዲኝነት እንዱታይለትና ፍትህ የማግኘት መብት ያለው መሆኑ በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 37 ተደንግጓል። አመልካች በውጭ አገር አለ የምትለው የጋራ ሀብት ጥያቄ በዲኝነት እንዱታይለትና ፍትህ እንዱሰጣት የመጠየቅ ሕገ-መንግሥታዊ መብቷ ነው። ሆኖም የሥር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን አንደኛው ለላላው በመግፊት ይህንን ሕገ-መንግሥታዊ መብቷን የሚጥስ ውሣኔ ሰጥተዋል። ስለሆነም አመልካች ያቀረበችው የዲኝነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘትና መስተናገድ ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአመልካች ጥያቄ በየትኛው ፍርድ ቤት ይስተናገድ የሚለውን ነጥብ በተመለከተ ጉዲዩ የዓለምአቀፍ የግል ሕግ ጥያቄ የሚያስነሣ መሆኑን የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ብይን አረጋግጧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበችው ክስ የዓለም አቀፍ የግል ሕግ ጥያቄ የሚያስነሣ ነው የሚለው መደምደሚያ ላይ ከደረሰ፣ አመልካች ተጠሪ በአገር ውስጥ ያፈሩት የጋራ ሀብት ጉዲይ የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አከራክሮ መወሰኑን እንደከፍተኛ ስህተት በመቁጠር ጉዲዩ በከፉል ለመጀመሪያ ፍርድ ቤት የታየ ስለሆነ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጠው ውሣኔ በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጠውን የአመልካችን ፍትህ የማግኘት መብትና ለፍርድ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 4 የተሰጠውን ሥልጣን የሚጥስ ስህተት ያለበት ሆኖ እያለ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማጽናቱ ተገቢነት የላለውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ብይን ተሽሯል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች በውጭ አገር አለ የሚለትን የጋራ ሀብት ጥያቄና ማስረጃ የተጠሪን መልስና ማስረጃ ሰምቶ እንዱወስን ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል ይፃፍ።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭ ራሣቸው ይቻለ ብለናል።
በትውስት የመጣው የከፍተኛው ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ፣ ይፃፍ።
ይኸ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጥር 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.