No summary available.
ታህሳስ 16 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አበበ ዓሉ - ቀርበዋል ተጠሪዎች፡-
ይህ አቤቱታ የቀረበው አመልካች ሚያዝያ 07 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠ/ፍ/የፍ/ይ/መ/ቁ. 336/2000፣ ጥር 21/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱሻርላቸው በመጠየቃቸው ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወል መስተዲድር ዞን፣ በቃለ መረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ፣የአሁኑ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል። የአሁኑ አመልካች በስር ፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ የመሰረታዊ ይዘቱ ክርክር የተነሳበትን ቤቴን አንደኛ ተከሳሽ (አከራይ) ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ደግሞ (ተከራዮች) በመሆን አላግባብ ይዘው ስለሚገኙና ቤቴን ሉያስረክቡኝ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ከመስከረም 1998 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 100(አንድ መቶ) ሂሳብ ክስ እስከ ቀረበበት ጊዜ ድረስ ታስቦ በጠቅላላ ብር 500(አምስት መቶ ብር) ከፍለው ተገደው እንዱያስረክቡኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ክስ የቀረበለት ወረዲ ፍርድ ቤትም በፍ/መ/ቁ.02127/98 ጥር 18 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ አከራካሪው ቤት በመንግስት እጅ የሚገኝ በመሆኑና በመንግስት እጅ የሚገኝ የተወረሰ ቤት ደግሞ በአዋጅ ቁ. 110/1987 መሰረት የመወሰን ስልጣን ያለው የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ እንጂ ፍርድ ቤቶች አይደለም በማለት የደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ሥራና ከተማ ልማት ቅ/ጽ/ቤት ጥር 08/1999 ዓ.ም ደብዲቤ እንደፃፈ በመግለጽ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም ብሎል። የደቡብ ወል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዲዩ በይግባኝ ቀርቦለት በፍ/ይ/መ/ቁ. 14649 ካከራከረ በኋላ ጥቅምት 15 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት የወረዲውን ፍ/ቤት ውሣኔ ያጸናው ሲሆን የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ጉዲዩ በይግባኝ ቢቀርብለትም በጠ/ፍ/የፍትሐብሕር ይግባኝ መ/ቁ 336/2000 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ሚያዝያ 07 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ወደዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም ተጠሪዎቹ በውርስ ያገኘሁትን ቤት አላግባብ ይዘዋል፤ቤቱ በመንግስት የተወረሰ አይደለም፤ ይህ አከራካሪ ቤት እንዱመለስልኝ ለቃለ ወረዲ ምክር ቤት አመልክቼ ምክር ቤቱም መፍትሄ እንዱሰጠኝ ወደ የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ደብዲቤ ጽፍልኝ ኤጀንሲውም በበኩለ ዻጉሜ 03 ቀን 1996 ዓ.ም በፃፈው ደብዲቤ አከራካሪውን ቤት በተመለከተ በአዋጁ ከተሰጠው ስልጣን አኳያ ተገናዝቦ ሲታይ በስልጣኑ ስር እንደማይወድቅና የማየት ስልጣን እንደላለው በግልጽ ወስኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶቹ ያቀረብኩትን ክርክር በአግባቡ ሳይመረምሩ በደፈናው ስልጣን የለንም ማለታቸው ተገቢ አይደለም፤የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አከራካሪውን ቤት የመመለስ ጉዲይ በተሰጠው ስልጣን ውስጥ እንደማይካተት በግልጽ አስቀምጦ እያለ ፍ/ቤቶቹ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ያለው የፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ነው ማለታቸው የፍትህ ጥያቄን ያላገናዘበ ነው የሚል ነው።
አንደኛ ተጠሪም በቁጥር ፍ/ደ/ማ 19/421/2000 ሐምል 03 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ሰጥቷል፤ይዘቱም አከራካሪው ቤት በደቡብ ወል መስተዲድር ዞን፣ኮምቦልቻ ከተማ 08 ቀበላ ገበሬ ማህበር ክልል ልዩ ስሙ ሚጢቆል ተብል በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ በምስራቅ የአቶ አብደ ረዱ ቤት፣በምእራብ የ08 ቀ/ገ/ማህበር ጽ/ቤት፣ በደቡብና በሰሜን የመኪና መንገድ የሚያዋስናው ከእንጨትና ከጭቃ የተሰራ ሁለት ክፍል ቤት ሲሆን የአቶ ዓሉ ሙሄ እንደነበር ይታወቃል፣ ቤቱ በአዋጅ ቁ. 47/67 የተወረሰ ነው፣የቤቱ ባለቤት የነበሩት አቶ ዓሉ ሙሄ ቤቱ እንዱመለስላቸው ጥረት እያደረጉ የነበረ ቢሆንም ቤቱ እንደማይመለስላቸው በወቅቱ ተነግሯቸዋል፤የአሁኑ አመልካችም ይህንን ጠንቅቀው ያውቃለ፤አቶ ዓሉ ሙሄ በሞት የተለዩት በ1971 ዓ.ም ስለሆነ አመልካች ከ33 ዓመታት በኋላ አሁን ያቀረቡት ክስ በይርጋ እንደሚታገድ ተቃውሞ አቅርቤበት እያለሁ የስር ፍ/ቤቱ ምንም አይነት ብይን ሳይሰጥበት አልፎል፣ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶቹ በአከራካሪው ቤት የሰጡት ፍርድ ተገቢ ስለሆነ ይጽናልኝ የሚል ሲሆን። ሁለተኛ ተጠሪም ሐምል 16 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው አከራካሪው ቤት በመንግስት የተወረሰ ሆኖ እኔ በኪራይ ይዤዋለሁ፤ተጨማሪ ወጪ አድርጌበታለሁ፤ አመልካች ይህንን ክስ ጊዜውን ጠብቆ ያቀረበው ባለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1000 በይርጋ ይታገዲል ብለዋል፤ሦስተኛ ተጠሪ ስላልቀረቡ የሰጡት መልስ የለም።
አመልካችም በመሰረቱ ከአቤቱታቸው ያልተለየ የመልስ መልስ ያቀረቡ በመሆኑ ደግሞ መዘርዘር ሳያስፈልግ ታልፎል።
ይህ ሰበር ችልትም የክርክሩ አመጣጥ ከላይ በሰፈረው መልኩ ከተገነዘበ በኋላ የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አከራካሪውን ቤት የማየት ስልጣን የለኝም እያለ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም ማለት ነበረበት ወይስ አልነበረበትም? የሚል መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤቱ ባቀረቡት የቤት ይመለስልኝ ክስ የቃል ወረዲ ፍ/ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው ቤቱ በመንግስት የተወረሰ ነው የሚል ክርክር በመቅረቡና የደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ከተማ ልማት በመንግስት የተወረሱ ቤቶች አይቶ መወሰን የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 110/87 መሰረት የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ እንጂ መደበኛ ፍርድ ቤቶች አይደለም ያለውን ነው። በእርግጥ በአዋጅ ቁ. 47/1967 የተወረሱ ቤቶች እንዱሁም ከዚህ አዋጅ ውጭ በደርግ ጊዜ በቀላጤ የተወረሱ ቤቶችን መደበኛ ፍርድ ቤቶች አከራክረው የመወሰን ስልጣን የላቸውም፣ በሚመለከተው የአስተዲደር አካል እንዱሁም በቀላጤ የተወረሱ ከሆነ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 110/1987 መሰረት የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ይታያለ እንጂ በመደበኛ ፍ/ቤቶች አይደለም። አሁን ክርክር የተነሳበት ቤት በሚመለከት ግን ቤቱ የተወረሰ ነው ከሚል ግምት ውጭ የግራ ቀኙ ወገኖች ማስረጃዎች በዝርዝር አልተመዘኑም፣ የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አከራካሪውን ቤት የማየት ስልጣን የለኝም ብል ደብዲቤ ጽፎል የተባለው በተገቢው ሁኔታ ተገናዝቦና ተተንትኖ ፍርድ ያረፈበት አይደለም፤የዞኑ የስራና ከተማ ልማት ቅ/ጽ/ቤት ደብዲቤ ስለፃፈ የሚለው ምክንያት በማስቀመጥ ክርክሩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የተሰጠው ፍርድ የተሟላ አይደለም፤ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁ. 47/1967 የተወረሰ ቤት ወይም ከዚሁ አዋጅ ውጭ በደርግ ስርአት ጊዜ በቀላጤ የተወረሰ ቤትን በሚመለከት አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የለኝም ለማለት ይህ መሆኑ በተከራካሪ ወገኖች ወይም በልላ አካል ስለተጠቀሰ ብቻ ሳይሆን የቀረቡለት ማስረጃዎችና አጠቃላይ የክርክር አቅጣጫዎች በመመዘን ይህ መሆኑ የሚያመላክቱ ሆነው ሲያገኛቸው ነው፤በአሁኑ ክርክር ግን የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ጉዲዩ ስልጣኑ እንዲልሆነ ገልጿል እየተባለ ነው፤በአጠቃላይ የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክርና ማስረጃ እንዱሁም ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ ተቃውሞዎች ሳይመዝኑና ሳይበይኑ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የተሰጠው ፍርድ በመሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
336/2000
No topics extracted.