No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 319ዐ6 ኀዲር 4 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ሑሩት አሥራት ተጠሪ፡- የአቶ መርስኤ መንበሩ ወራሾች - አልቀረቡም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ተጠሪዎች ለዚሁ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ሟች አባታችን በአዱስ አበባ ከተማ በወረዲ 3 ቀበላ 53 ክልል ቁጥር 849 የሆነውን ቤት በ1957 ዓ.ም. ከቀድሞ ባለ ርስት በጭሰኝነት ተመርተው ተገቢው ኪራይ እየከፈለ ሲገለገለ የቆየ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 47/67 ሲታወጅ የባለርስትና የጭሰኛ ግንኙነት በመቋረጡ የአፈር ግብር ለመንግሥት እየከፈለ የቆዩ ቢሆንም የቤት ባለቤትነት ደብተር ለማውጣት በቦታው ላይ ይዞታ እንደነበራቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከፍ/ቤት አስመስክረንና አረጋግጠን እንድንቀርብ የተጠየቅን በመሆኑ የቤት ባለቤትነት ደብተሩን ማግኘት እንድንችል በቦታው ላይ ይዞታ ያለን ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይሰጠን በማለት ጠይቀዋል።
አመልካቾች በተጠሪነት ያጣመሩት ባለመኖሩ ፍ/ቤቱ የአመልካካቾችን ምስክሮች ሰምቶ የአመልካቾች አባት ቦታውን በ1959 ዓ.ም. ከልዕልት ተናኘ ወርቅ ላይ በጭሰኝነት ተመርተው ውሃና መብራት በማስገባት ቤት ሰርተው የጋራዥ ድርጅት አቋቁመው ሲሰሩበት እንደበር አዋጅ ቁጥር 47/67 ከታወጀ በኋላ የቦታና የቤት ግብር ለመንግሥት ሲከፍል እንደነበር በማስረጃ የተረጋገጠ ስለሆነ ይሄው ተገልጾ ለሚመለከተው ክፍል ይፃፍላቸው በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም የአሁን አመልካች የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በወቅቱ የኪራይ ቤቶች አስተዲደር ድርጅት አመልካቾች በይዞታቸው ሥር እንደሆነ ተገልጾ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ትዕዛዝ የተሰጠበት ድርጅት በአዋጅ 47/67 መሰረት የተወረሰና የሚያስተዲድረው መሆኑን ገልጾ በላለበት የተሰጠው ትዕዛዝ መብቱን እንደነካ በመግለጽ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት በተቃዋሚነት ወደ ክርክሩ ለመግባት ጠይቆ በተፈቀደለት መሰረት ወደ ክርክሩ በመግባት ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ ክርክር የተነሳበት ድርጅት በአዋጅ 47/67 መሰረት ተወርሷል አልተወረሰም የሚለውን ጭብጥ ይዞ ጉዲዩን በመመርመር መወረሱ ስለተረጋጠ አመልካቾች ከአዋጅ 47/67 መንፈስ ውጭ ተወስድብናል የሚለ ከሆነ ይህንኑ ጥያቄያቸውን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ከሚያቀርቡ በስተቀር በተያዘው መዝገብ እንደማይስተናገድ ጠቅሶ አስቀድሞ ለአመልካቾች ይዞታ ያላቸው መሆኑ ተጠቅሶ እንዱፃፍላቸው የተሰጠው ትዕዛዝ ሉነሳ ይገባል በማለት አንስቷል።
አመልካቾች በዚህ ውሣኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙ አከራክሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ድርጅት በይግባኝ ባዮች ይዞታ ሥር እንደነበርና በአዋጅም እንዲልተወረሰ የቀረቡት ማስረጃዎች የሚያረጋግጡ እንደመሆኑ መጠን መልስ ሰጭው ድርጅቱ መወረሱን ባላረጋገጠበት ሁኔታ የሥር ፍ/ቤት ድርጅቱ መወረሱ ተረጋግጧል በማለት አስቀድሞ የሰጠውን ትዕዛዝ ማንሣቱ በአግባቡ አይደለም ሲል በመሻር የቀድሞው ትዕዛዝ ሉሰረዝ አይገባም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የከተማው አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ሰበር ችልትም ይሄው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመበትም በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ ሳይቀረበለው ቀርቷል።
ለዚህ ችልትም የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ችልቱም አቤቱታውን መርምሮ በሚያከራክረው ንብረት ላይ ተጠሪዎች የይዞታ ማስረጃ እንዱሰጣቸው በፍ/ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ ተገቢ ነው ተብል የአመልካች መቃወሚያ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውድቅ መደረጉ ለሰበር ቀርቦ ላታይ እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን ጠርቷል። ሆኖም ተጠሪዎች በአድራሻቸው ሉገኙ ባለመቻላቸው በጋዜጣ ተጠርተው ስላልቀረቡ በጽሁፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል። በቃል ክርክርም ጊዜ ስላልቀረቡ ችልቱ የአመልካችን የቃል ክርክር ብቻ አዲምጧል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
በቅድሚያ ችልቱ የተመለከተው አመልካቾች አቤቱታ ያቀረቡበት ጉዲይ ለፍ/ቤት ላቀርብ የሚችልና ዲኝነት የሚያፈልገው /Justicable/ መሆኑን በተመለከተ ነው።
ተጠሪዎች በከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ለክርክሩ ምክንያት በሆነው የንግድ ድርጅት ላይ የይዞታ መብት ያለን መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይሰጠን በማለት ነው። ተጠሪዎች የዚህ ዓይነቱ ማስረጃ ከፍ/ቤቱ እንዱሰጣቸው የጠየቁትም የቤት ባለቤትነት ደብተር ከሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም ለማግኘት እንደሆነም በአቤቱታቸው ላይ ጠቅሰዋል።
የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 ላይ የተመለከተ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን በማወቅ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የሚሰጠው በመንግሥት የአስተዲደር መ/ቤት በኩል እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
እንደዚሁም የምስክር ወረቀት የሚሰጥበት ሥርዓት የአስተዲደር መስሪያ ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት እንደሚወሰንም በዚሁ ድንጋጌ ሥር ተመልክቷል።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም ሰው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ማግኘት የሚችለው ከሚመለከተው የመንግሥት አስተዲደር መስሪያ ቤት በኩል ሲሆን የሚመለከተው የመንግሥት አስተዲደር መ/ቤት የምስክር ወረቀት አሰጣጡን አስመልክቶ በሚያወጣው የምስክር ወረቀትም እንደሚሰጥ መረዲት ይቻላል።
ሕጉ በዚህ መልኩ የባለቤትነት የምስክር ወረቀት እንደሚሰጥ ከደነገገ የምስክር ወረቀቱን ለማግኘት እንዱቻል የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ እንዱሰጥ ፍ/ቤትን መጠየቅ ከነመነሻውም ቢሆን ጉዲዩ በፍ/ቤት ቀርቦ ዲኝነት የሚያስፈልገው /Jusciable matter/ እንዲልሆነ ተገንዝበናል።
ስለሆነም የዚህ ዓይነቱ ማስረጃ ይሰጠኝ በማለት በፍ/ቤት የሚቀርብ አቤቱታ በፍ/ቤት ሉስተናገድ እንደማይችል ግልጽ በመሆኑ ከመነሻውም ቢሆን ፍ/ቤቱ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት መመለስ ሲገባው ጉዲዩን ማስተናገደ አግባብነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህም በኋላ አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ ሲያቀርብ ፍ/ቤቱ የቀድመውን ትዕዛዝ መሰረዙ ከውጤት አኳያ ተቀባይነት ነበረው። ሆኖም ግን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይህንኑ ትዕዛዝ ምክንያቱን ለውጦ ሉያጸናው ሲገባ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ድርጅት መወረሱ አልተረጋገጠም በማለት መሻሩ ጉድለት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የከተማው ይግባኝ ሰማ ሰበር ችልትም መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመም በማለት ይህንኑ ጉድለት ሳያርም መቅረቱ በአግባቡ ሆኖ አላገኘነው።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ ነክ ሰበር ችልት በመ/ቁ. ዐ1998 ሚያዝያ 19 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ እንደዚሁም ይግባኙ ችልቱ በመ/ቁ. ዐዐ682 በ3ዐ/3/97 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት በአብላጫ ድምጽ ሽረነዋል።
ተጠሪዎች የቤት ባለቤትነት የምስክር ወረቀት ለማግኘት እንድችል የይዞታ መብት ያለን መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከፍ/ቤቱ ይሰጠን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ለፍ/ቤት ቀርቦ ዲኝነት ላሰጥበት የማይችል ጉዲይ /Justicable matter/ ስላልሆነ አቤቱታው ከመነሻውም ቢሆን ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም ነበር በማለት ወስነናል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መ/ቤት መልሰናል።
No topics extracted.