No summary available.
ኀዲር 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የሟች አቶ ሰለሞን ሳሙኤል ወራሾች -ቀርቧል እነ ወ/ሮ ማረታ ሰለሞን(ሁለት ሰዎች) - ጠበቃ ታደሰ ጉርሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- ኑረዱን መሐመድ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ተወስኗል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ጣልቃ ገቦች ተጠሪ የሥር ከሣሽ ነበሩ።
የአሁን ተጠሪ በሥር ተከሣሾች በነበሩት አንደኛ ንግድ ኢንደስትሪና ቱሪዝም ቢሮ፣ ሁለተኛ የወረዲ 5 አስተዲደር፣ ሦስተኛ የኪራይ ቤቶች አስተዲደር ላይ ባቀረበው ክስ በድርጅት ቤት፤ የሆቴል ንግድ ሕጋዊ ፈቃድ አውጥቼ በየዘመኑ ፈቃዳን እያሳደስኩ ከኪራይ ቤቶች ተከራይቼ በምሰራው ሆቴል ቤት እየሰራሁ እያለሁ፤የሥር ተከሣሾች ቤቱን ያለአግባብ እንዲልሰራ አሽገውብኛል። ስለዚህ አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሣሾች ቤቱን እንዱያስረክቡኝ ሦስተኛ የሥር ተከሣሽ ከእኔ (ተጠሪ) ጋር የነበረውን ውል ሣያቋርጥ(ሳያፈርስ) ላላ ውል በመፈፀም ያስገባቸውን ግለሰቦች እንዱያስወጣ ውላቸውንም እንዱሰርዝ፣ የቀረብኝን ጥቅምና የደረሰብኝ ጉዲት የመጠየቅ መብቴ ተጠብቆ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
አንደኛ እና ሁለተኛ የሥር ተከሣሾች ለቀረበባቸው ክስ መልስ ሲሰጡ፡- የአሁን ተጠሪ ፍቃዲቸውን ያላደሱ በመሆኑ የጸና የንግድ ፍቃድ የላቸውም ፍቃዲቸው ተሰርዟል።
ከተጠሪ ጋራ ያለን ግንኙነት ስለተቋረጠ የሚጠይቁት ጥቅም ሆነ መብት የላቸውም ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ሲመልስ፤ሁለተኛ የሥር ተከሣሽ በበኩለ የተባለውን ቤት በጋራም ሆነ በተናጥል አላሸግኩም ሲል መልሷል ሦስተኛ የስር ተከሳሽም በተመሣሣይ መልኩ ድርጊቱን እንዲልፈፀመ ክድ ተከራክሯል።
በዚሁ ጉዲይ የሥር ጣልቃ ገብ የአሁን ተጠሪ ይህን ቤት በሕጋዊ መንገድ ከኪራይ ቤቶች አስተዲደር ተረክበው በውላቸው መሰረት ይዘውት እንዲለ ገልጸው የቀረበው ክስ ውድቅ እንዱሆን በመቃወም ተከራክረዋል።
የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ጉዲዩን ከሕግ ጋር በማገናዘብ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ የንግድ ፈቃድ ባለማደሳቸው እና በወቅቱ የቤት ኪራይ ክፍያ ባለመፈፀማቸው ምክንያት በኪራይ ይዘውት የነበረውን ቤት ሕግና ደንብ በሚያዘው መሰረት መብታቸውን አጥተዋል። ስለዚህ ይህን ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 33(2) መሰረት የመክሰስ መብት የላቸውም ሲል ወስኗል።
የአሁን ተጠሪም በተሰጠው ውሳኔ ባለመስማማት ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቅሬታውን አቅርቦ ፍ/ቤቱም ጉዲዩን አስቀርቦ በማከራከር ካየ በኋላ የሥር አንደኛ ተከሣሽ የአሁን ተጠሪን የንግድ ድርጅት ያሸገው ያለ አግባብ ነው፣ ሦስተኛ የሥር ተከሣሽ ከአሁን ተጠሪ ጋር ያደረገው የቤት ክራይ ውል ፀንቶ ባለበት ሁኔታ ከአሁን አመልካቾች ጋር በውል ላይ ውል በመፈፀም ቤቱን ያስረከባቸው በአግባቡ አይደለም፣ የአሁን ተጠሪ እና የሥር ሦስተኛ ተከሣሽ የኪራይ ውላቸውን መቀጠል ይገባል በማለት የሥር ውሳኔን በመሻር ውሣኔ ሰጥተዋል።
በዚህም መሰረት የአሁን አመልካቾች በከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለከተማው ሰበር ሰሚ ለሆነው ፍ/ቤት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ በፍ/ቤቱ ውስጥ ጉዲዩን የማየት ስልጣንን አስመልክቶ የሐሳብ ልዩነት በመፈጠሩ በልዩነት ውሳኔ ተሰጥቶበታል። በመሆኑም አብላጫው ድምጽ ምክንያቱን ሳያስቀምጥ “ምንም እንኳን የፋዳራል መንግስት አካል የሆነው የኪ.ቤ.አ.ድ በዚህ መዝገብ ተከራካሪ ቢሆንም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ነገር የመስተዲድሩ አካላት በነበራቸው የአስፈፃሚነት ስልጣን በመሆኑና እነርሱ የወሰደትን እርምጃን ተከትል የኪ.ቤ.አ.ድ በወሰደው እርምጃ የተከሰሰና ይህም አንድ ድርጊት በመሆኑ ጉዲዩ የዚህ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው” በማለት በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ስህተት የለም በማለት የሰበር አቤቱታውን ሰርዞታል።
አነስተኛ ድምፁም በጉዲዩ የተለየበትን ሐሳብ ሲያስቀምጥ፡- “በክርክሩ ጭብጥ ውስጥ ይህንን ቤት በባለቤትነት የሚያስተዲድረው የኪራይ ቤቶች ድርጅት ቤቱን አላግባብ ለሦስተኛ ወገን አከራየብኝ የሚል በመሆኑ በአዋጅ 25/88 መሰረት መዲኘት የሚኖርበት በፋዳራል ፍርድ ቤት ከመሆኑም በላይ የክርክሩ መነሻ የሆነው ቤትም በአዋጅ 36/95 አንቀጽ 41/1/ረ ላይ መስተዲድሩ በባለቤትነት ከሚያስተዲድራቸው ሥር የማይሸፈን በመሆኑ በከተማው ፍ/ቤት መታየቱ ከሥልጣን አኳያ አግብብ አይደለም” ሲል ልዩነቱን አስፍረዋል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። አመልካቾች ጥር 1 ቀን 2000 ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ በከተማው ይግባኝ ሰሚና በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አቤቱታቸውን አቅርቧል።
ይህ የፋዳራል ሰበር ችልትም አቤቱታውን ምክንያት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምተዋል። ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱታይ የወሰነው የሥር ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ተቀብል ለመወሰን ስልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ነው። በዚህም መሰረት ይህን ነጥብ ከተነሳው ክርክር፣ በአቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከህጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
በዚህ ጉዲይ የአሁን ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ክሱን ሲመሰርት የሆቴል ቤቱ ያለአግባብ በመስተዲድሩ አካላት እና በቱሪዝም ቢሮ የታሸገበት መሆኑን ብቻ ሳይሆን የፋዳራል መንግስት መስሪያ ቤት የሆነውን የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ኪራይ እየከፈልኩ የምሰራበትን የሆቴል ቤት ነጥቆኝ ለሦስተኛ ወገን አከራይቶታል በሚል ምክንያት ነው።
እኛም ተሻሽል የወጣውን የአዱስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁ. 24/1/ረ ስናይ የከተማው ፍ/ቤት ማየት የሚችለው የከተማው አስተዲደር ከሚያስተዲድራቸው የመንግስት ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዲዮችን ነው። ሕጉ ይህን እያለና ዋና የቤት አስተዲደር (ባለቤት) ከተጠሪ ጋራ የውል ግንኙነት እያላቸው በፋዳራለ ሥልጣን ክስ የሚወድቀውን ክርክር በከተማው ፍ/ቤት መታየቱ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለዚህ በሥር ፍ/ቤት በአበላጫ ድምጽ የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮ በአናሳው ደምጽ ጉዲዩ የከተማው ፍ/ቤት ሥልጣን አይደለም ያለው ተቀባይነት አግኝተዋል።
ው ሣ ኔ
የአ.አ.ከተማ የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት መ/ቁ. 2633/91 ሐምል 22 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 02703 ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የከተማው ሰበር በመዝገብ ቁ. 05360 በ4/4/2000 ዓ.ም የሰጡት ውሣኔ ተሽሮአል። ይፃፍ።
የአ/አ/ከተማ መስተዲድር ፍ/ቤቶች ይህን ክርክር የማየት ስልጣን የላቸውም ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጪ እና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.