No summary available.
የሰ/መ/ ህዲር 9 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ሻምበል አሰፊ በላይ ዘገየ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ወታደራዊ ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
በዚህ መዝገብ ለቀረበው አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የወንጀል ክርክርን ይሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ነው ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው በ1949 ዓ.ም በወጣው የወ/መ/ሕ በቁ. 386 እና 642 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ወንጀል ስለፈጸመ ጥፊተኛ ነው ተብል ቅጣት ሉወሰንበት ይገባል በማለት ነው። ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤቱም አመልካችን አስቀርቦ ከአከራከረ በኋላ አመልካች በተጠቀሱበት የሕግ ድንጋጌዎች የተመለከቱትን የወንጀል ድርጊቶች ለስመፈጸሙ በማስረጃ አረጋግጫለሁ የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በመቀጠልም በአመልካች ላይ የስድስት (6) ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ወስኖአል።
በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለይግባኝ ሰሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ በዚህ ደረጃም ክርክሩ የተሰማ ሲሆን በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው ቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሐምል 30 ቀን 99 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በአመልካች ተፈጽሞአል የተባለው ወንጀል በወታደራዊ ፍ/ቤት የስረ - ነገር የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ስለመሆኑ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ለጉዲዮ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው በዚህ ሰበር ችልት አከራካሪ ሆኖ የቀረበው ጭብጥ በአመልካች ላይ የተመሰረተው ክስ በወታደደራዊ ፍ/ቤት የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው። ጉዲዮ የፍ/ቤቶችን የዲኝነት ስልጣን ምንጭ (በአጠቃላይ) ምንድነው? አንድ ፍ/ቤት ከስልጣኑ ውጪ ጉዲይ ተቀብል ዲኝቷል ማለት ምን ማለት ነው?
የዲኘው ከስልጣኑ ውጪ ሆኖ ከተገኘስ ውጤቱ ምን ይሆናል? የሚለትን መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚያስነሳ በመሆኑ በጥንቃቄ ለመመርመር የሚባው ነው።
እንደሚታወቀው ፍ/ቤቶች በሕግ የሚቋቋሙ እንደመሆናቸው የዲኝነት ስልጣናቸው የሚመነጨውም ከሕግ ነው።
ከዚህ እንግደህ መገንዘብ የሚቻለው የማንኛውም ፍ/ቤት የዲኝነት ስልጣን በሕግ ተወስኖ የተሰጠ (የሚሰጥ) መሆኑን ነው። በመሆኑም ማንኛውም ፍ/ቤት የቀረበለትን ጉዲይ (ክስ) ተቀብል ከማስተናገደ በፉት በጉዲዮ (ክሱ) ላይ በሕግ የተሰጠ የዲኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን የማረጋገጥ ሃላፉነት አለበት። በሕግ የተሰጠ የዲኝነት ስልጣን ሳይኖር የሚሰጥ ውሳኔ የሕግ መሰረት ያለው ነው ወይም ሕጋዊ ውሳኔ ነው ለማለት እንደማይቻልም በአግባቡ መገንዘቡ ተገቢ ነው የሚሆነው።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ የወታደራዊ ፍ/ቤቶች እንደ ላልቹ ፍ/ቤቶች በሕግ የተቋቋሙ እና የዲኝነት ስልጣናቸውም በሕግ ተወስኖ የተሰጠ እንደሆነ እንገነዘባለን። በመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁ.27/1988 በአንቀጽ 25 እንደተመለከተው ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት እና ይግባኝ ሰሚ ወታደራዊ ተቋሙመዋል ለፍ/ቤቶቹ የተሰጠ የዲኝነት ሥልጣን በተመለከተም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 26፣27 እና 28 በዝርዝር ተገልጿአል። በ1949 ዓ.ም በወጣው የወ/መሕግ ከቁ.296 እስከ ቁ.331 በተዘረዘሩት ወንጀልች ተጠያቂ የሚሆኑ ሰዎች ላይ በግዲጅ ላይ ያለ ወታደር በሚፈጽማቸው በማናቸውም ወንጀልች ላይ በውጪ አገር በጦር ሜዲ ግዲጅ ላይ ካለ ወታደር ጋር አብረው በሚዘምቱ ሲቪልች ላይ እና በጦር ምርኮኞች ላይ ከተፈፀመ ወንጀል ላይ የወታደራዊ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን እንዲላቸው አንቀጽ 26 በግልጽ ያመለክታል። ከዚህም በተጨማሪ ተከሣሹ ከቀረቡበት ክሶች መካከል አንደ በወታደራዊ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ወንጀል በሆነ ጊዜ ሁለም ክሶች የሚቀርቡት ለወታደራዊ ፍ/ቤቶች እንደሆነ በአንቀጽ 28 ተመልክቶአል።
በአመልካች በኩል የቀረበው ክርክር ስንመለከት ፍ/ቤቶቹ በዚህ ጉዲይ አመልካች በተከሰሰበት የዲኝነት ስልጣን የላቸውም ለሚለው ክርክሩ በዋቢነት የጠቀሰው ከላይ በተመለከተው አንቀጽ 26/1/ የተቀመጠው ድንጋጌ ነው።
በእርግጥም ይህ ንዐስ አንቀጽ ለብቻው ተወስድ ሲታይ በወ/መ/ሕጉ ከቁ.296 እስከ ቁ.331 ድረስ ያለትን ድንጋጌዎች ብቻ ስለሚጠቅስ በአመልካች ላይ በቀረበው ክስ የተጠቀሱትን ቁ.386 እና ቁ. 642 አያካትትም። ከዚህ የተነሣም የአመልካቹ ክርክር ተገቢነት ያለው ነው ልባል ይችላል። በአንቀጽ ንዐስ አንቀጽ (2)፣(3) እና (4) የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ስንመለከት ግን ለወታደራዊ ፍ/ቤቶች የተሰጠው የዲኝነት ስልጣን በንዐስ አንቀጽ /1/ ከተመለከተው የሰፊ እንደሆነ ነው መገንዘብ የሚቻለው። በንዐስ አንቀጽ /2/ የተመለከተውን ድንጋጌ እንኳን ወስደን ስናየው በንዐስ አንቀጽ /1/ የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ በግዲጅ ላይ ያለ ወታደር በሚፈጽማቸው በማናቸውም ወንጀልች ላይ ጭምር ፍ/ቤቶቹ የዲኝነት ስልጣን እንዲላቸው ነው የምንገነዘበው። የአመልካቹ ክርክር በጽሐፍ ተቀባይነት ሉኖረው ይችላል ብል መደምደምያ የማይቻለውም (ትክክል የማይሆነውም) በዚህ ምክንያት ነው። በልላ በኩል ግን ‹‹ ግዲጅ›› የሚለው ቃል በአዋጁ ባለመተርጏሙ እና አመልካችም የተከሰሰው ከፊይናንሰ አስተዲደር ጋር በተያያዘ ወንጀል በመሆኑ አመልካቹ በአዋጁ አንቀጽ 26 (2) አባባል በግዲጅ ላይ እንዲለ በፈጸመው ወንጀል ነው የተከሰሰው ወይም የተከሰሱበት ወንጀል የተፈጸመው በግዲጅ ላይ ሳለ ለማለትም ይቻላል ወይ የሚለው ነጥብ አከራካሪ ይሆናል።
የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁ.27/88 በመከላከያ ሰራዊት (ማሻሻያ) አዋጅ ቁ.343/95 ተሻሽልአል። ይህ አዋጅ በግልጽ ካሻሻላቸው አንቀጾች መካከል የቃላትን ትርጓሜ በተመለተ የተደነገገ ነው አንቀጽ 2 እና የወታራዊ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን የሚመለከተው አንቀጽ 26 ይገኛለ። በዚህም በቀድሞው በትርጓሜ ውስጥ ተካቶ ያልነበረው ‹‹ግዲጅ›› የሚለው ቃል ‹‹ማንኛውም የሰራዊት አባል ከተቀጠረበት ጊዜ አንስቶ ከሰራዊቱ እስኪሰናበት ጊዜ ድረስ በመከላከያ ውስጥ የሚያከናውነው የውትድርና ተግባር ነው›› በሚል በማሻሻያው አዋጁ ቁ.343/95 አንቀጽ 2(9) ተተርጏሞአል።
አንቀጽ 26(2)ም በትርጓሜ ክፍለ በተተረጏመው ‹‹ግዲጅ›› ከሚለው ቃል በሚስማማ መልኩ ተሻሽልአል። በዚህም የወታራዊ ፍ/ቤቶቹ የዲኝነት ስልጣን ከቀድሞው የበለጠ ሰፍቶአል። አዋጅ ቁ.27/88‹ን› ማሻሻል ካስፈለገበት ምክንያቶች አንደም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በወታደርነት በማገልገል ላይ ያለ የሰራዊቱ አባል የሚፈጽማቸው ወንጀልች በወታደራዊ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን ስር እንዱወድቁ በመታሰቡ እንደሆነ ከአዋጁ ማሻሻያ አዋጅ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
አመልካች የተከሰሰበትን ወንጀል ፈጸመ በተባለበት ጊዜ ሰራዊቱ አባል (ወታደር) ሆኖ ይሰራ እንደነበረ ተረጋግጦአል። ይህም ማለት በማሻሻያው አዋጅ ቁ.343/95 አንቀጽ 2(9) እንደተደነገገው በግዲጅ ላይ ነበር ማለት ነው።
በመሆኑም ፈጸመው የተባለው የወንጀል ድርጊት በአዋጁ አንቀጽ 26/1/ በተመለከቱት የወ/መ/ሕጉ ድንጋጌዎች ስር የማይወድቅ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተቀጥሮ (በውትድርና) የሚያከናውነውን የውትድርና ተግባር ሲሰራ በነበረበት ጊዜ የፈጸመው በመሆኑ ክሱ ለወታደራዊ ፍ/ቤት መቅረቡ ትክክል ነው። ሲጠቃለል የወታደራዊ ፍ/ቤቶች ይህን ክስ ለማስተናገድ በሕግ የተሰጠ የዲኝነት ስልጣን አላቸው። ስለዚህም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልቻልንም።
አቤቱታ የቀረበበት ይግባኝ ሰሚ ወታራዊ ፍ/ቤት የመቁ.014/99 መጋቢት 18 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 195/2/ /ለ/ /2/ መሰረት ፀንቷል።
ክሱ ለወታደራዊ ፍ/ቤት መቅረቡ በሕጉ መሰረት ሆኖ ስላገኘነው የአመልካችን ክርክር አልተቀበልንም።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.