No summary available.
ጥቅምት 6 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አስጨናቂ ረጋሣ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ግንቦት 10 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 13 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይሻርልኝ በማለት ኀዲር 9 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የክርክሩ ፍሬ ጉዲይ ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 47/1967 ያልተወረሰና አባታችን ከአዋጁ በፉት በወለድ አግድ አስይዞት የነበረ፣እንዱሁም በቅጽ 004 የተመዘገበ የአባታችን አቶ ነጋሽ መንገሻ ንብረት የሆነ ቁጥሩ 668/669 ቤት አመልካችና የወረዲ 4 ቀበላ 28 አስተዲደር ጽ/ቤት በፍርድ ተገድደው እንዱያስረክቧቸው ለአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። አመልካችና ሁለተኛ ተከሳሽ የነበረው የወረዲ 4 ቀበላ 28 አስተዲደር ጽ/ቤት ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ ነው፤ በማስረጃነት የቀረበው ቅጽ 004 በሚመለከተው የበላይ አካል ያልፀደቀና በቀበላ ደረጃ ብቻ የተሞላና አስተያየት የተሰጠበት ሰነድ በመሆኑ ቤቱ ያልተወረሰ መሆኑን ለማስረዲት አይቻልም የሚል ክርክር አቅርበዋል፤ ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 መሰረት የተወረሰ ነው በማለት የተጠሪዎችን ክስ ውድቅ አድርጓል። ተጠሪዎች ይግባኛቸውን ለከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ቤቱ በቅጽ 004 የተሞላ ተጠሪዎች አውራሽ የምርጫ ቤት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያለ በመሆኑ ለተጠሪዎች መመለስ አለበት በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኛት ለከተማ ነክ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የከተማ ነክ ሰበር ሰሚ ችልት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች ይህ ውሣኔ መሰረታዊ ስህተት አለበት፤ በመጀመሪያም የከተማ ነክ ፍርድ ቤት ይህንን ጉዲይ አይቶ ለመወሰን የሚያስችለው የሥረ-ነገር ስልጣን የለውም፤ ቤቱ የተወረሰ ነው፤ ቅጽ 004 የተባለው በሚመለከተው አካል የፀደቀ ባለመሆኑ ቤቱ ለተጠሪዎች አውራሽ በምርጫ ቤትነት እንዱይዙት የተወሰነ መሆኑን ለማስረዲት ብቃት የለውም፤
የሚል ክርክር ያቀረበ ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለው፤ ቤቱ በቅጽ 004 በወቅቱ ሕጋዊ ስልጣን ባለው አካል ለአውራሻችን በምርጫ ቤትነት የተሰጠ ነው ስለዚህ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ስህተት የለበትም የሚል መልስ አቅርበዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን እንደመረመርነው የከተማ ነክ ፍርድ ቤት ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 መሰረት የተወረሰ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ለማየትና ቤቱን በአዋጅ ቁጥር 47/1967 ያልተወሰረ በመሆኑ ለተጠሪዎች ይመልስ በማለት የመወሰን የዲኝነት ስልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውመሰረታዊ የህግ ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ አንፃር ስንመረምረው የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ስልጣንና ሐላፉነት በአዋጅ ቁጥር 361/1995 በአንቀጽ 41 የተዘረዘረ ሲሆን የከተማ ነክ ፍርድ ቤት ንብረትነቱ የከተማው አስተዲደር የሆነ ቤት ላይ የሚነሱ ክርክሮችን አይቶ የመወሰን ስልጣን እንዲለው በአዋጅ አንቀጽ 41(1)(ረ) በግልጽ ተደንግጓል። ከዚህም የምንረዲው የከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ንብረትነታቸው የከተማ አስተዲዲር ለመሆናቸው ክርክር በማይቀርብባቸው ቤቶች ላይ የሚነሱ የይዞታ የኪራይ እና ላልች ክርክሮችን አይተው የመወሰን ስልጣን ያላቸው መሆኑን ነው።
ሆኖም ክርክር የተነሳበት ቤት የከተማው አስተዲደር ነው ወይስ የላላ ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚል መሰረታዊ ክርክር ያለበት ከሆነ የከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ይህንን የቤት ባለቤትነት ጥያቄ አስመልክቶ በከተማው አስተዲደርና በላልች ሰዎች መካከል የሚደረግ ክርክር በዲኝነት አይተው ለመወሰን የሚያስችል የሥረ-ነገር ስልጣን የላላቸው መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 (1) (ረ) ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ የቤቱን ባለቤትነት አስመልክቶ በተጠሪዎች በኩል ክርክር እያቀረቡበትና የጉዲዩም መሰረታዊ ጭብጥ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 መሰረት ተወርሷል ወይስ አልተወሰረም የሚል በመሆኑ ይህንን ጉዲይ ሰምተውና አከራክረው ውሣኔ ለመስጠት የሚያስችላቸው የሥረ-ነገር ስልጣን ሣይኖራቸው የአዱስ አበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ውሣኔ ሰጥተውበታል። ስለሆነም በየደረጃው ያለ የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማየት የስረ-ነገር ስልጣን ሣይኖራቸው ጉዲዩን ሰምተውና አከራክረው የሰጡት ውሣኔ ህጋዊ አስገዲጅነት የላለውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
ይፃፍ።
ተጠሪዎች ሥልጣኑ ለሚፈቅድለት ፍርድ ቤት ወይም አካል አቅርበው የመጠየቅ መብታቸውን ይህ ውሣኔ አይገድብባቸውም ብለናል።
በትውስት የመጣው መዝገብ ከመሸኛ ደብዲቤ ጋር ይመለስ።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ጉዲዩ በውሣኔ የተቋጨ ስለሆነ ተነስቷል። ይፃፍ።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጥቅምት 6 ቀን 2001 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.