No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3444ዐ ጥቅምት ዐ6 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- መንበረ ፕትሪያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ቀሲስ መሰረት አፈወርቅ ተጠሪ፡- መጋቢ ሚስጢር መዝገቡ በላይነህ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የአሁኑ ተጠሪ ተከሣሽ ደግሞ የአሁኑ አመልካች ነበር።
የሥር ከሣሽ ጥር 26 ቀን 1999 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የክስ ይዘት ሲታይም ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ በቅኔ እና አቋቋም መምህርነት ሲያገለግለ ቆይተው የተከሣሽ መ/ቤት አስተዲደር ጉባዔ ሰኔ 29 ቀን 1986 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሰረት ይሰሩበት ከነበረው ከደቡብ ወል ሀገረስብከት ወደ አዱስ አበባ ተዛውረው እየሰሩ መሆናቸውን፤ ሆኖም ከሐምል ዐ1 ቀን 1986 ዓ.ም ጀምሮ የተቋረጠ ደመወዝ መኖሩን በመግለጽ የተቋረጠው ደመወዝ ከኪሣራ ጋር እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የስር ተከሣሽም በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርቦ መጋቢት 14 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመከላከያ መልሱን አቅርቧል። ይዘቱም በአጭሩ ሲታይ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላለው መሆኑንና የከሣሽ የክፍያ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ የሚሆን መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥብነት አንስቶ በፍሬ ነገር ረገድም ከሣሽ አዱስ አበባ መጥተው በልላ ቤተክርስቲያን አገልግልት እየሰጡና ደመወዝ እየተከፈላቸው ከመሆኑም በላይ ቀድሞ ይሰሩበት ከነበረው ቦታም ላላ ሰው ተተክቶ ደመወዝ እየተከፈለ መሆኑን በመጥቀስ የከሣሽ ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት መከራከሩን የሚያስረዲ ነው። የሥር ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን በቃል ከአከራከረና ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ በተከሣሽ በኩል የቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦች በከፉል ውድቅ በማድረግ የከሣሽን ጥያቄ በከፉል በመቀበል የተቋረጠ ደመወዝ ሉከፈለው ይገባል በማለት ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም በዚሁ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ባለመስማማት በመቃወም ነው።
የአመልካች ነገረፈጅ ታህሣሥ 15 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ የበታች ፍ/ቤቶች ፈፀሙ ያሎቸውን የሕግ ስህተቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላለው መሆኑን፣ ይኸው ቢታለፍ እንኳ የደመወዝ ጥያቄው ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ የቀረበ በመሆኑ በይርጋ ቀሪ ላሆን የሚገባው መሆኑን በመዘርዘር የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪን ያስቀርባል ተብል መጋቢት ዐ1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን አቅርበዋል። ይዘቱም መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ያለው መሆኑንና የደመወዝ ጥያቄውም ውዝፍ ደመወዝ ይከፈለኝ ባለመሆኑ በይርጋ የሚታገድበት የሕግ አግባብ አለመኖሩን በመዘርዘር እና የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ ተገቢነት በመግለጽ ሉፀና ይገባል ሲለ መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች ነገረፈጅ በበኩላቸው የተጠሪን መልስ በመንቀፍና የሰበር አቤቱታ ይዘቱን ተገቢነት በማጠናከር መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ከሕጉ ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ጉዲዩ በመደበኛ ፍ/ቤት መታየቱን በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የተቋረጠው የደመወዝ ክፍያ ጥያቄን ሉያቀርቡ የቻለት በአመልካች መ/ቤት ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ በቅኔ መምህርነት ተቀጥረው ሲያገኙት የነበረው ደመወዝ ከ1/11/86 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጧል በሚል ነው። አመልካች ተጠሪ የቅኔ መምህር በመሆናቸውና አገልግልቱም መንፈሣዊ በመሆኑ በስራ ክርክር ሰሚ ላታይ እንደማይገባው በመግለጽ ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤት ይህንኑ የአመልካች መከራከሪያ ነጥብ ያለፈውም የተጠሪ አገልግልት ከኃይማኖት ተቋሙ ጋር የተያያዘ ቀጥተኛ መንፈሣዊ ስራ አይባልም በሚል ነው። አመልካች በበኩለ የተጠሪ ስራ ለተማሪዎች አገልግልት የሚሰጥ የቅኔ መምህርነት ነው በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ ለዚህ ለሰበር ችልቱ በሰጡት መልስም የቅኔ መምህርነት ከኃይማኖት ተቋሙ ጋር የተያያዘ ቀጥተኛ መንፈሣዊ ስራ አይደለም በማለት ያነሱት ክርክር የለም። በመሆኑም የተጠሪ የቅኔ መምህርነት ስራ ቀጥተኛ የሆነ መንፈሣዊ ስራ መሆኑ የሚያከራከር ሆኖ አልተገኘም።
በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤት የደረሰበት ድምዲሜ የግራ ቀኙን ክርክር ያላገናዘበ ነው።
No topics extracted.
ይህ ችልት በመዝገብ ግንቦት ዐ4 ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ የኃይማኖት ድርጅት ሰራተኞችን በሁለት ከፍል በማየት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ተፈፃሚነትን ወስኗል። በዚህም መሰረት ከኃይማኖት ድርጅቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለውና ከእምነት ተነጥል ላታይ የማይችል ስራ የሚሰሩ ሰራተኞች እንደ ቄስ፣ ካህን፣ ዱያቆን --- ወዘተ ከኃይማኖት ድርጅታቸው ጋር የሚያነሡት ክርክር በአሰሪና ሰራተኛ ሕግ መሰረት ሉዲኝ የማይገባው መሆኑ ተወስኗል። ሰበር ችልቱ ወደዚህ ድምዲሜ የደረሰውም መንፈሣዊ ስራ የሚሰሩት ግለሰቦች ቀጥተኛ ከእምነቱ ወይም የኃይማኖት ድርጅቱ ከሚከተለው እምነት የሚመነጭና ከእምነቱ ጋር ጥብቅ ትስስር ያለው በመሆኑ፣ መንፈሣዊ አገልግልቱን ለመስጠት ብቁ ሆኖ ለመገኘትም በእምነቱ መሰረት መሟላት የሚገባቸው ልዩ ነጥቦች መኖራቸው ይታወቃል በሚል ምክንያት ነው። ከዚህም የምንገነዘበው ተጠሪ የቅኔ መምህር ሆነው ሉቀጠሩ የቻለት የአመልካች እምነት የሚጠይቀውን ልዩ መመዘኛ አሟልተው በመገኘታቸውና ይህንኑ መንፈሣዊ አገልግልት ለተማሪዎች ለመስጠት ነው። ተጠሪ የሚሰጡት አገልግልት በባህርይው ቀጥተኛ የሆነ መንፈሣዊ ትስስር ያለው መሆኑ እየታወቀ በኃይማኖት ተቋሙ እንደሚሰሩ ላልች እንደ ሂሣብ ሰራተኛ፣ ንብረት ክፍል ሰራተኛ የስታትስቲክስ ሰራተኛ --- ወዘተ ተቆጥሮ የቅኔ መምህርነት ቀጥተኛ መንፈሣዊ አገልግልት ልባል አይገባም መባለ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
የተጠሪ ስራ ቀጥተኛ የሆነ መንፈሣዊ አገልግልት ነው ከተባለ ደግሞ ከአመልካች ጋር የሚኖሩት አለመግባባት በስራ ክርክር ሰሚ ቀርቦ ላታይ የማይገባ፣ ይልቁንም በኃይማኖት ተቋሙ አለመግባባቶች በሚፈቱበት መንገድ ላታይ የሚገባው መሆኑን ከላይ የተጠቀሰው የሰበር ችልት ውሣኔ ያስረዲል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ 1/ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2ዐ228 ግንቦት ዐ8 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 55548 ህዲር 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
2/ የተጠሪ ጥያቄ በኃይማኖት ተቋሙ አለመግባባቶች በሚፈቱበት መንገድ ከሚታይ በስተቀር በስራ ክርክር ሰሚ አካል ቀርቦ የሚዲኝበት የሕግ መሰረት የለም ብለናል።
3/ ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
4/ መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ።