No summary available.
ጥቅምት 25 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ገ/መስቀል ደመወዝ - ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አፀደ መኯንን - ቀረበች።
መዝገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በሁከት ይወገድልኝ የክስ መነሻነት የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረውም የአሁኑ አመልካች ነው። በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው ከቀበላ ተከራይቼ የምኖርበትን ቤት ማእድ ቤት ለማደስ ያደረግሁት እንቅስቃሴ እንዲይሳካ ሁከት ስለፈጠረችብኝ ሁከቱ ይወገድ ዘንድ ይታዘዝልኝ በማለት ነው። ማህበራዊ ፍ/ቤቱ ተጠሪን በማስቀረብ ክርክሩን ከሰማ በኋላ የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካቹ ውሳኔውን በመቃወም ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲዲር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ እንደገና ተሰምቷል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በማህበራዊ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በማጽናቱ አመልካች አሁንም ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ ክርክሩ እንዱሰማ አድርጓል። ፍ/ቤቱም ክርክሩን ከመረመረ በኋላ በአብላጫ ድምጽ በሰጠው ውሳኔ በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። የአሁኑ አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች የካቲት 5 ቀን 2000 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ጉዲዩ በቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ስለመሆን አለመሆኑ ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንደተገለጸው አመልካች ለቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት ክስ ያቀረበው ተጠሪ የማእድ ቤቱ እድሳት እንዲይካሄድ በመከልከል የፈጸመችው ድርጊት ሕገ ወጥ ነው ተብል እንዱወገድ እና እድሳቱን እንዱያካሂድ እንዱወሰንለት በመጠየቅ ነው። የክሱ ምክንያት ሕገ ወጥ ነው የተባለው ድርጊት እንዱወገድ የሚጠይቅ ከመሆን አልፍ የገንዘብ ጥቅም ወይም በገንዘብ ሉተመን የሚችል መብት የሚጠይቅ አይደለም። ጉዲዩ በቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ ሉነሳ የቻለውም በዚህ ምክንያት ነው።
በግልጽ እንደሚታወቀው ማንኛውም ፍ/ቤት አንድን ጉዲይ ተቀብል ሉያስተናግድ የሚችለው በክልልም ሆነ በስረነገር ረገድ የዲኝነት ስልጣን ሲኖረው ነው። የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣንን በሚመለከትም ሕጉ ጥብቅ የሆነ ድንጋጌ አስቀምጦአል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.9/1/ እንደተመለከተው በስረ-ነገሩ ለመዲኝት ስልጣን የላለው ፍ/ቤት የክስ ማመልከቻውን በፍ/ብ/ሕግ ቁ.231 በተደገገው መሰረት ተቀባይነት የለውም ብል መመለስ አለበት። ፍ/ቤቱ ይህን እርምጃ መውሰድ ያለበት ተከራካሪ ወገን መቃወሚያ እንዱያቀርብለት ሳይጠብቅ በራሱ አነሳሽነት እንደሆነም በዚሁ ቁ.9/2/ በግልጽ ተመልክቶአል። በመሆኑም በዚህ ድንጋጌ የተቀመጠውን አስገዲጅ መርህ ለማስከበር ሲባል የቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤቱ በጉዲዩ ላይ የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ነበረው ወይ? የሚለው ጭብጥ መያዙ ተገቢ ነው።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በየቀበላው የቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች እንዲለና የመዲኘት ስልጣንም እንደተሰጣቸው በተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 39 ተመልክቷል።
የፍ/ቤቶቹን የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን በተመለከተ በሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ 50/1/ እንደተመለከተውም ግምታቸው ከብር 5000(አምስት ሺህ) ባልበለጡ የንብረትና የገንዘብ ክርክሮች ብቻ የተወሰነ የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ነው ያላቸው።
በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ክስ በገንዘብ የሚተመን አይደለም። በገንዘብ የማይተመኑ ወይም የገንዘብ ግምት የላላቸው፣ ነገር ግን መሰረታዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የሚያስነሱ ክሶች የሚታዩበትን ሁኔታ ሕጉ በተለየ ሁኔታ ደንግጓአል። በቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች የስረ- ነገር የዲኝነት ስልጣን ስር እንዱወድቁ ግን አልደነገገም። የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አነስተኛ ድምጽ የቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤቱ የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን የለውም በማለት ከአብላጫው ድምጽ የተለየውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ለመገንዘብ ችለናል። በበኩላችንም ትክክለኛ ሆኖ ያገኘነው በአነስተኛው ድምጽ የተሰጠው የሕግ ትርጉም ነው። ከዚህ የተነሣም በአብላጫው ድምጽ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
02897 ታሕሣሥ 25 ቀን 2000 ዓ.ም በተሰጠው ውሳኔ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ጉዲዩ በቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት የዲኝነት ስልጣን ስር የማይወድቅ በመሆኑ ማህበራዊ ፍ/ቤቱ ክሱን ያስተናገደው ከሕግ ውጪ ነው በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ በሚመለከት ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.