No summary available.
ጥቅምት 06 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡- እነ ወ/ሮ እመቤት መክብብ - ጠበቃ አስቴር አርአያ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ በድለ መክብብ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ አመልካች፣የአሁኑ አመልካቾችና ወ/ሮ አልታየወርቅ መክብብ ደግሞ ተጠሪዎች ነበሩ።
የስር አመልካች አቤቱታ ይዘት ሲታይም የሟች ወንድማቸው የአቶ መለጌታ መክብብ ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን፣ ከስር ተጠሪዎች ጋር በመሆን የውርስ ሐብቱን ለማጣራት ቢፈልጉም ተጠሪዎች ፈቃደኛ ሆነው ውርሱን ለማጣራት ያልቻለ መሆናቸውን በመግለጽ ውርሱ ይጣራ ዘንድ ፍ/ቤቱ የውርስ አጣሪ እንዱሾምላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚገልጽ ነው። የስር ተጠሪዎችም በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርበው ፍ/ቤቱ የውርስ አጣሪ ለመሾም በሕግ የተሰጠ ስልጣን የላለው መሆኑን፤ የውርስ አጣሪን መሾም የማያስፈልግ መሆኑን የሚያሣዩ ምክንያቶች መኖራቸውን በመዘርዘር የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ላሆን እንደሚገባ ተከራክረዋል። ከዚህም በኋላ የስር ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር በማድመጥ እና አግባብነት አላቸው ያላቸውን ጭብጦች በመመስረት ፍ/ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41(1)(ሸ) መሰረት ጉዲዩን የማየት ስልጣን እንዲለው በመዘርዘር የተጠሪዎችን ተቃውሞ ካለፈ በኋላ የውርስ አጣሪ በመሾም የውርስ ሐብቱ ተጣርቶ ሪፕርቱ ላቀርብ ይገባል በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል። የአሁኑ አመልካቾች በዚህ የስር ፍ/ቤት ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን እና የሰበር አቤቱታቸውን እንደየቅደም ተከተለ ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚና ሰበር ሰሚ ችልቶች ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሣያገኙ ቀርተዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የበታች ፍ/ቤቶች ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ነው።
አመልካቾች የካቲት 12 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የቅሬታ ነጥቦችንና በበታች ፍ/ቤቶች ተፈፀሙ ያሎቸውን የህግ ስህተቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአዋጁ የተሰጠው ስልጣን የወራሽነት የምስክር ወረቀት ለመስጠት እንጂ ውርስ አጣሪ ለመሾም አይደለም፤ የሚልና የውርስ አጣሪ መሾም ለጉዲዩ አስፈላጊ አለመሆኑን በመዘርዘር የበታች ፍ/ቤቶች ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ተብል በሰበር ችልቱ ተሽሮ በቂ ወጪና ኪሣራ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው።
የአመልካቾች አቤቱታ ተመርምሮም የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍ/ቤቶች የውርስ ክርክርን አስመልክቶ በቀረበ ጉዲይ ላይ የውርስ አጣሪ የመሾም ስልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ ይቅረብ ተብል ተጠሪ እንዱቀርቡና መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል። በዚህም መሰረት ተጠሪ ሚያዝያ 28 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት በሕግ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን በመዘርዘር የአመልካቾች አቤቱታ ውድቅ ሆኖ የበታች ፍ/ቤቶች ትእዛዝ ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አመልካቾች የተጠሪ መልስ ተቀባይነት የላለው መሆኑን በመጥቀስና የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ግንቦት 28 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ ከሕጉ ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል። እንደመረመርነውም በተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 39 ስር የከተማው አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶችና የቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች የሚኖሩት ስለመሆኑ፤ በአዋጁ አንቀጽ 41 መሰረትም የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን መዘርዘሩን ተገንዝበናል። የአዋጁ አንቀጽ 41(1)(ሸ) ድንጋጌም የወራሽነት የምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ አቤቱታን የማየት የዲኝነት ስልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን መሆኑን በማያሻማና ግልጽ በሆነ ቋንቋ ይገልፃል። የስር ፍ/ቤት የውርስ አጣሪን የመሾም ስልጣን አለኝ ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው ከላይ የተጠቀሰውን አዋጅና የፍ/ብ/ሕ/ቁ.996/1/ ድንጋጌን መሰረት በማድረግ የውርስ ሐብቱ ሣይጣራ የወራሽነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ላይ የወራሽ ድርሻ ሉገለጽ አይችልም በሚል ምክንያት ነው።
ይሁን እንጂ ይህ ትርጓሜ አዋጁ ላይ የተመለከተው ድንጋጌ ግልጽ ከመሆኑ እና የወራሽነት የምስክር ወረቀት ከውርስ ማጣራት ሂደት ጋር ተያያዥነት ያለው ቢሆንም ሉያስነሣ ከሚችላቸው ሕጋዊ ክርክሮች አኳያ ሲታይ ከውርስ ማጣራት ሂደት ያነሰ የውስብስብነት ባሕርይ ያለው መሆኑን ያላገናዘበ ነው።
በመሰረቱ የተፃፈ ሕግ የሚተረጏመው ግልጽነት ሲጏድለው ነው። ህጉ ግልጽ በሆነበት ሁኔታ ግን ትርጉም አላስፈላጊ ስለመሆኑ የሕግ አተረጓጏም መርሆዎች ያስገነዝቡናል። ግልጽ ህግን መተርጏም ፍ/ቤት በትርጉም ሰበብ የሕግ አውጪውን ስልጣን ተክቶ እንደሰራ የሚያስቆጥር ነው። ስለሆነም የወራሽነት የምስክር ወረቀት የማግኘትና የውርስ ማጣራት ሂደት ሁለት የተለያዩ ሂደቶች መሆናቸው እየታወቀ፣ ህግ አውጪውም የምስክር ወረቀት የማግኘት አቤቱታን በሚመለከት ብቻ ለአስተዲደሩ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን በግልጽ ለይቶ ሰጥቶ እያለ፣ የወራሽነት የምስክር ወረቀት ማግኘትና የውርስ ማጣራት ተያያዥነት አላቸው በሚል ምክንያት ብቻ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን ማየቱ የሕግ አተረጓጏም መርህን በተከተለ መንገድ ሣይሆን ይህንኑ ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 678/99 የካቲት 08 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰጥቶ በአስተዲደሩ ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 04083 ሐምል 12 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት፣እንዱሁም በአስተዲደሩ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 04951 ጥር 16 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት በትእዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በአብላጫ ድምጽ ተሽሯል። ይፃፍ።
በአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41(1(ሸ)) መሰረት የተሰጠው የዲኝነት ስልጣን የወራሽነት የምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ አቤቱታን በተመለከተ እንጂ የውርስ አጣሪ የመሾም የዲኝነት ስልጣን አይደለም ብለናል።
በአዱስ አበባ መስተዲድር ውስጥ የውርስ አጣሪ ይሾምልኝ ጥያቄ የማየት የዲኝነት ሥልጣን የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.